AbichoEthio

AbichoEthio

Share

Photos from AbichoEthio's post 10/07/2023

ልብ ሰባሪ መረጃ❗

በሀዋሳ ከተማ በታቦር ተራራ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዋን ዘርፈው፤ ወደ ገደል ወረወሯት።
*****

ወጣት ሄለን ታሊሞስ ሁሉም የሚያቃት የሚመሰክርላት የዋህ ቅን ለታናናሾቿ ሳይቀር የምትታዘዝ እግዚአብሔርን የምትፈራ በቤተሰቦቿም በጓደኞቿም የተወደደች የተመሠገነች ልጅ ናት።

ሄለን በ2013 ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በኤሌክትሪካል ምህንድስና እና በጤና መኮንንነት የመጀመሪያ ዲግሪዋን ጨርሳለች።

ሁለተኛ ዲግሪዋን በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ እየተማረች ሳለ፥ አንድ ቀን ለመዝናናት ከተማሪ ጓደኞቿ ጋር ሀዋሳ ታቦር ተራራ በሄደችበት የቀን ጎዶሎ፥ በዘራፊዎች እጅ ትወድቃለች።

ያላትን ሁሉ ወስደው፤ ከታቦር ተራራ ወደ ታች ገፍትረው ጣሏት። ከፍተኛ ጉዳት ደረሰባት፥ ሀዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ገባች። ሁለት ጊዜ ጭንቅላቷን ኦፒራሶን እንደተደረገች አባቷ ተናግሯል።

አሁን ሄለን ኮማ ውስጥ ናት።

ከሰኔ 4 ቀን 2015 ጀምሮ ለቤተሰቦቿ የህክምና ወጪ ከአቅማቸው በላይ ሆነ።

እናንት ደጋግ ኢትዮጵያዊያን
ይህችን ቅን ወጣት ለማዳን እንረባረብ።

Talimos Tadesse Gebeyo (አባት)
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
የሂሳብ ቁጥር
1000270955828

Photos from AbichoEthio's post 07/07/2023

Kylian Mbappé አባቱ በተወለደበት ሀገር ካሜሩን ሲያርፍ በአድናቂዎች አቀባበል ተደርጎለታል 🇨🇲

06/07/2023

አርባምንጭ ከተማ ወደ ከፍተኛ ሊግ ወርዷል!

2014 ላይ ዳግም ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተመልሶ ሲሳተፍ የነበረው አርባምንጭ ከተማ ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ለገጣፎ ለገዳዲን ተከትሎ ከሁለት ተከታታይ የተሳትፎ ዓመታት በኋላ ወደ ከፍተኛ ሊግ መውረዱ ተረጋግጧል።

https://t.me/joinchat/QHDEnL36tPdttINg

👆👆 መረጃዎቻችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻነላችንን ይቀላቀሉ

06/07/2023

እሱ እድሜው 87 ነው
እሷ ደግሞ 85 አመቷ

ከተማ ውስጥ በየመንገዱ ዳር የሚታዩት እጇን በእጁ ይዞ ሲሄዱ ነው

"ለምንድነው ሁልጊዜ እጇን ይዘሃት የምትዞረው?" ሰዎች ይጠይቁታል

"የመርሳት በሽታ አለባት" ይመልሳል

"ታዲያ እጇን ለቅቀሃት ትተሃት ብትሄድ ታውቃለች?"

"ኧረ በጭራሽ አታውቅም! እኔ እንኳ ምኗ እንደሆንኩኝ ረስታኛለች" ባል ይመልሳል

"ጭራሽ አንተንም አታስታውስህም?" መንገደኛ ይጠይቃል

"አዎን ለ53 አመታት አብረን ኖረናል! አሁን ግን አታውቀኝም"

"ታዲያ የማታውቅህ ከሆነ ለምን አትተዋትም? ለምን እጇን ይዘህ ትዞራለህ ታዲያ?"

"እሷ ላታውቀኝ ትችላለች🤷🏽‍♂️እኔ ግን አውቃታለሁ! እሷ ረስታኝ ሊሆን ይችላል እኔ ግን አልረሳኃትም!"

❤️🙌🏼

በዘመለአክ እንድሪያስ

05/07/2023

«በስልክ ደውሎ 200ሺ ብር አዘጋጅ ሲሉ ቀልድ ነበር የመሰለኝ»

አንዱ በስልክ ደውሎ 200ሺ ብር አዘጋጅ አለኝ! ቀልድ ስለመሰለኝ "ብሩን እንዴት ላቀብላችሁ?" ብዬ መለስኩለት "አንተ ብቻ ብሩን አዘጋጅ እኛ እንዴት እንደምንቀበል እናውቃለን፣ በአምስት ቀን ውስጥ አዘጋጅ" ብለው ስልኩ ተዘጋ።

እኔ ቀልድ ስለመሰለኝ ረስቼዋለሁ እነሱ የገቢ ምንጬን ሁሉንም ነገር አጥንተው ነበር እኔ ግን ስለ እነሱ ምንም አላውቅም። በስድስተኛው ቀን ጠዋት ከቤት እንደወጣው አምቡላንስ የሚመስል መኪና መጥቶ አጠገቤ ቆመ ከመኪናው ውስጥ ሰዎች ወረዱ "ይቅርታ፣ ይቅርታ" እያሉ የኋላ በር ከፍተው አሰገቡኝ ራሴን ለማዳን ብሞክርም አልቻልኩም ይላል።

ቀዝቃዛ ከነበረችው ከተማ ወስደው በጣም ሞቃማ ወደ ሆነ ስፍራ ወስደው በአንድ ቆርቆሮ ቤት አስገቡኝ ይላል ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈለገ ባለታሪኩ ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ሲናገር የባንክ ATM ተቀበሉኝ ፓስወርዱን ወሰዱ ከዛ የቤት እና የመኪና ቁልፌን ተቀበሉኝ ብሏል።

እዛ በቆየውበት ወቅት አፋኞቹ የፖለቲካም ይሁን የብሄር ነገር አልነበረም እነሱ ሲጠይቁኝ የነበረው 200ሺ ብሩን እንድሰጣቸው ነበር ብሏል።

በመጨረሻም ፊቴን እና አፌን አፍነው የከተማ መግቢያ ላይ ጥለውኝ ሄዱ በቆየውበት 10 ቀናት ዳቦ እና ሙዝ ነበር የሰጡኝ ውሃ ብዙ ስላላገኘው ደሜ ወርዶ ነበር።

ታፍኜ በተወሰድኩ ጊዜ ወንዝ ውስጥ ሲፈልጉኝ ነበር ሌላው ታፍኖ ነው ነው ተብሎ ከእኔ ጋር ግኑኝነት የነበራቸው ሰዎች ታስረው ነበር የጠበቁኝ ይላል። አፋኞቹ ምንም አይነት መረጃ እንዳልናገር ከተናገርኩ እንደሚገድሉኝ ነበር አስጠንቅቀው የለቀቁኝ በአሁኑ ጊዜ ከሚኖርበት ከተማ ለቆ በሌላ ከተማ እንደሚገኝ ነው የተናገረው።

Want your business to be the top-listed Media Company in Rustenburg?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

https://youtube.com/@abichoethio5228

Address


Rustenburg