Joni.Te

Joni.Te

Share

01/11/2023

ዮሐ4: 12 በእውኑ አንተ ይህን ጕድጓድ ከሰጠን ከአባታችን ከያዕቆብ ትበልጣለህን?

የሰው ልጅ ውስጣው ፍላጎት ሁልጊዜ የሚበልጠውን :የተሻለውን : አዲስን ነገር ይፈልጋል ይህንን ፍላጎቱን ለማርካት የሚሄድበት እርቀት ሌላ ባዶነትን ሸምቶ ይመለሳል ምክኒያቱም ውስጣዊ ጥያቄውን ለመመለስ የሄደበትና የመረጠው ነገር ውስጣዊውን ጥያቄ መመለስ ሳይችል ሲቀር የህይወት ትርጉሙ እየጠፋበት ተስፋው እየተሟጠጠ ያዘግማል :

ለዚህ ነው ኢየሱስ ክርስቶስ ዮሐ 7: 37 ከበዓሉም በታላቁ በኋለኛው ቀን ኢየሱስ ቆሞ፡— ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ።

የሰው ልጅ በእርካታ ህይወት መመላለስ የሚችለው መንፈስ ቅዱስ በውስጡ ሲኖር ብቻ ነው መንፈስ ቅዱስ ደግሞ እግዚአብሔር ለሰው ልጅ በክርስቶስ አማካኝነት የሰጠው ልዩ ስጦታ ነው

ሉቃ 11: 13 እንኪያስ እናንተ ክፉዎች ስትሆኑ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠት ካወቃችሁ፥ በሰማይ ያለው አባት ለሚለምኑት እንዴት አብልጦ መንፈስ ቅዱስን ይሰጣቸው?

ወዳጆቼ ዓለም መቼም የሰውን ልጅ የውስጥ ጥያቄ መልሳ አታውቅም መመልስም አትችለም ምክኒያቱም የሰው ልጅ እንዲረካ ተደርጎ የተፈጠረው በቁሳዊው አለም ሳይሆን በራሱ በእእግዚአብሔር ነው :

ጠቢቡ ሰለሞን እንዲህ አለ መክ 1:8 ዓይን ከማየት አይጠግብም፥ ጆሮም ከመስማት አይሞላም።

9 የሆነው ነገር እርሱ የሚሆን ነው፥ የተደረገውም ነገር እርሱ የሚደረግ ነው፤ ከፀሐይም በታች አዲስ ነገር የለም።

ወገኖቼ ከፀሐይ በታች የሰው ልጅ የፍላጎቱን ጥያቄ ለመመለስ ምን ያልሆነው ያልያዘው ያልጨበጠው ነገር አለ
ገንዘብን ፈልጎ አገኘ ነገር ግን እርካታና ጥጋብ እዛ ውስጥ የለም
መክ 5: 10 ብርን የሚወድድ ሰው ብርን አይጠግብም፤ ባለጠግነትንም የሚወድድ ትርፉን አይጠግብም፤ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው።

ነገር ግን ከፀሐይ በላይ ይኖር የነበር የሰውን ሁለንተና ጥያቄ ሊመልስ ባዶነትን ሊያሶግድ ሸክፍም ሊያራግፍ የመንፈስ የነፍስ የስጋን እረፍት ለሰው ልጅ ሊሰጥ ሰው ሆኖ የሰውን ልጅ ከእግዚአብሔር ለመጣላት ሰላምን ለማጣት ግራ ለመጋባት ተስፋ ቢስ ለመሆን የዲያብሎስ ፈቃድ ተገዥ ለመሆን የዳረገውን የዲያብሎስን ሥራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ :

ኃጢአት የሚያስከፍለውን ዋጋ ሁሉ ክፍሎ የእጉሞችን ሞት በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ሞቶ ተቀብሮ ደግሞም በሶስተኛው ቀን ሞትን ድል ነስቶ በክብር አረገ ደግሞም በክብር እመለሳለው አለ

ስለዚ ወገኖቼ
የፅድቃችን ጥያቄ ተመልሷል
የሰላማችን ጥያቄ ተመልሷል
የእርካታችን........
የደስታችን
የእረፍታችን
የተስፋችን
የነጋችን
የዘላለማችን
ከተመለሱልን ጥያቄዎች ጥቂቱን ነው የዘረዘርኩትኝ
ኢየሱ
ስ ምን ያልመለሰው ጥያቄ አለ ምንም::

ስለዚህ በማንኛውም የህይወት ጥያቄ ውስጥ ያለችው
ኢየሱስ ክርስቶስ ያልመለሰው ምንም የለምና ህይወታችሁን ለኢየሱስ አሳልፋችሁ ስጡት እርሱ እውነተኛ እረኛ ነው

1ኛ የጴጥሮስ 2:25 እንደ በጎች ትቅበዘበዙ ነበርና፥ አሁን ግን ወደ ነፍሳችሁ እረኛና ጠባቂ ተመልሳችኋል።

ኢየሱስ ይወዳችኃል

አገልጋይ ጆን
ሰላማችሁ በክርስቶስ ይብዛ :: 01/11/2023

ሉቃ 11:31 እነሆም፥ ከሰሎሞን የሚበልጥ ከዚህ አለ።

17/10/2023
Want your place of worship to be the top-listed Place Of Worship in Port Elizabeth?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address


58 Pearson Street
Port Elizabeth
6001