Gulele Radio

Gulele Radio

Share

Photos from Gulele Radio's post 04/30/2025

በኮንትራክተር አቅም ማነስ ምክንያት ተቋርጦ የቆየው የታርጫ ጪዳ አስፋልት መንገድ ሥራ ተጀመረ::

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በ4 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ወጪ የሚገነባው የ64 ነጥብ 8 ኪ.ሜ የታርጫ ጪዳ ሎት 3 አስፋልት መንገድ ፕሮጀክት ግንባታ በዛሬው ዕለት ተጀምሯል።

በፕሮጀክቱ ማስጀመር ሥነሥርዓት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) እና የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒን ጨምሮ የፌዴራልና ክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ተጀምሯል።

የመንገድ ፕሮጀክቱ ከዚህ በፊት ተጀምሮ በኮንትራክተሩ አቅም ማነስ ምክንያት ተቋርጦ የመልካም አስተዳደር ችግር ሆኖ መቆየቱን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ የሺዋስ ዓለሙ ለፋና ዲጂታል ገልጸዋል።

ለክልሉ ህዝቦች ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ከፍተኛ ፋይዳ ያለው ፕሮጀክቱ በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ የክልሉ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።

የታርጫ ጪዳ አስፋልት መንገድ ግንባታ ከዳውሮና ኮንታ ዞኖች ባለፈ ከአጎራባች ጅማና ወላይታ ዞኖች ጋር ያለውን ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ትስስር እንደሚያጠናክርም ተናግረዋል።

የመንገዱ መገንባት ለገበያ ልውውጥ፣ ለቱሪዝም ዕድገት፣ ለክልሉ ኢኮኖሚ መነቃቃትና ለአካባቢው ነዋሪዎች አዳዲስ ዕድሎችን የሚፈጥር እንደሆነም ተመላክቷል።

ለመንገዱ ግንባታ 4 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ከፌደራል መንግስት እንደተመደበና በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ባለቤትነት በመሳይ ኦሊ ጠቅላላ ተቋራጭና በዩኒኮን አማካሪ እንደሚሰራም ተገልጿል።

የታርጫ ጪዳ አስፋልት መንገድ በ2 ዓመት ከ6 ወራት ጊዜ ውስጥ ተገንብቶ እንደሚጠናቀቅ መገለጹንም የቢሮው ኃላፊ አመላክተዋል።

04/30/2025

የአማራ ክልልን የማተራመስ እቅዱ የከሸፈበት ጽንፈኛ ቡድን መንግስት ሰላማዊ ዜጎች ላይ ጉዳት ያደረሰ በማስመሰል የሀሰት መረጃ በማሰራጨት ተጠምዷል ሲሉ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ ተናገሩ።

የክልሉን የጸጥታ ተቋማት መልሶ በማደረጃትና በማጠናከር ረገድ ውጤታማ ስራ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸው፥ ሀገር የማፍረስ ተልዕኮ ይዞ የሚንቀሳቀሰው ጽንፈኛ ቡድን ሰላማዊ ዜጎች ላይ ጥቃት በመፈጸም የህዝብ ጠላት መሆኑን በተግባር አሳይቷል ብለዋል፡፡

በክልሉ እየተወሰደ ካለው ህግ የማስከበር እርምጃ ጎን ለጎን ጽንፈኛ ቡድኑ የጥፋት መንገዱን እንዲተው በመንግስት ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪ መቅረቡን ያስታወሱት ኮሚሽነሩ፥ በርካታ ታጣቂዎች የሰላም ጥሪውን በመቀበል ወደ ሰላማዊ ህይወት መመለሳቸውን ተናግረዋል።

በአሁን ወቅት በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች በተገኘው ሰላም ህብረተሰቡ ሲያነሳቸው ለቆዩ የልማትና የሰላም ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ ለመመለስ እየተሰራ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

04/30/2025

በኦሮሚያ ክልል በህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ ምሬት በፈጠሩ 198 የዘርፉ ተዋናዮች ላይ እርምጃ ተወሰደ
*****************

በኦሮሚያ ክልል በህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ ምሬት በፈጠሩ 198 የዘርፉ ተዋናዮች ላይ እርምጃ መውሰዱን የክልሉ መንገዶችና ሎጂስቲክስ ቢሮ አስታውቋል።

ከታሪፍ በላይ ማስከፈል፣ ትርፍ መጫን፣ ከሾፌሮች ጋር ተመሳጥሮ ጉቦ መቀበል፣ ተሳፋሪውን ማንገላታት በዋናነት ከተገልጋዮች ለክልሉ መንገዶችና ሎጂስቲክስ ቢሮ የሚቀርቡ ቅሬታዎች ናቸው።

ይህን ተከትሎ የኦሮሚያ መንገዶችና ሎጂስቲክስ ቢሮ ባለፉት 3 ወራት በ198 አካላት ላይ እርምጃ መውሰዱን የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ሀጂ በተለይ ለኢቢሲ ዶትስትሪም ተናግረዋል።

የሥነ-ምግባር ጥሰት በፈጸሙ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎችና አሽከርካሪዎች፣ የትራንስፖርት ተቆጣጣሪ ሰራተኞች፣ የትራፊክ ፖሊሶችና ሌሎች አካላት ላይ ከሥራ እስከ ማሰናበት የሚደርስ ሕጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዷል ብለዋል።

ወደ ፊትም ቢሆን ከመናኸሪያ ከወጡ በኋላ የመኪና መለዋወጫ ዋጋ ጨምሯል፣ ነዳጅ ተወዷል፣ ወዘተ በማለት በሕገ-ወጥ መንገድ ከታሪፍ በላይ የሚያስከፍሉ አሽከርካሪዎችና ባለንብረቶችን ተገልጋዮች በ8556 ነጻ የስልክ መስመር ቢጠቁሙን ተመሳሳይ እርምጃ እንወስዳለን ብለዋል።

እንደ ኦሮሚያ ክልል ችግሩን በዘላቂነት ለመቅረፍ ክልሉ በ6 ክላስተሮች ተከፍሎ በመናኸሪያዎች ዘመናዊ የኢ-ቲኬቲንግ አገልግሎት ተዘርግቶ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው፤ ይህን አሰራር ተሻግረው የሚመጡ ችግሮችን ለመፍታትም የክትትልና ቁጥጥር ሥራው በመጠናከር ላይ መሆኑን ተናግረዋል።

ክልሉ ከተለያዩ ክልሎች ጋር የሚዋሰን እንደመሆኑ ድንበር ተሻጋሪ የትራንስፖርት ችግሮችም እንደሚያጋጥሙ የጠቆሙት ምክትል ቢሮ ኃላፊው፤ ከአዲስ አበባ ሸገር ሲቲን እና ሌሎች የኦሮሚያ አካባቢዎችን አቋርጠው ወደ ቡታጂራ፣ ወራቤ፣ ሆሳዕና እና ሌሎች ቦታዎች የሚጓዙ ተገልጋዮችም ቅሬታ እንደሚያሰሙ መረጃው አለን ነው ያሉት።

ችግሩን ለመፍታት ከደቡብ ክልል ጋር በቅንጅት እንደሚሰራም የኦሮሚያ መንገዶችና ሎጂስቲክስ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ሀጂ ጠቁመዋል።

በመሀመድ ፊጣሞ

04/30/2025

ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅትን በአባልነት እንድትቀላቀል አሜሪካ ድጋፍ ታደርጋለች - የአሜሪካ የንግድ ፅ/ቤት
***********************************

ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅትን በአባልነት እንድትቀላቀል አሜሪካ ድጋፍ እንደምታደርግ ገለጸች።

ከ2025 የዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋም እና የዓለም ባንክ የጸደይ ስብሰባዎች ጎን ለጎን የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) በአሜሪካ የንግድ ፅ/ቤት የዓለም ንግድ ድርጅት እና የባለብዙ ወገን ጉዳዮች ረዳት ተወካይ ከሆኑት ኒል ጄ ቤክ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይቱ ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅትን በአባልነት ለመቀላቀል እያደረገች ያለውን ከፍተኛ ጥረት አስመልክቶ ሚኒስትር ዴኤታው ገለጻ አድርገዋል።

በቀጣይ ዓመት መጋቢት ወር በሚካሄደው ጉባዔ ላይ፤ ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን የሚያስፈልጉትን መስፈርቶች ለማሟላት ቁርጠኛ መሆኗንም አስረድተዋል።

በአሜሪካ የንግድ ፅ/ቤት የዓለም ንግድ ድርጅት እና የባለብዙ ወገን ጉዳዮች ረዳት ተወካይ የሆኑት ኒል ጄ ቤክ በበኩላቸው ኢትዮጵያ የዓለም የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን እያከናወነች ያለውን ከፍተኛ ጥረት የሚደነቅ ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅትን በአባልነት እንድትቀላቀል አሜሪካ ድጋፍ እንደምታደርግ፤ እንዲሁም የኢትዮጵያ በተሳካ ሁኔታ ከዓለም አቀፉ የግብይት ሥርዓት ጋር መዋሃድ የአሜሪካ ፍላጎት መሆኑንም ገልጸዋል።

ሁለቱ ወገኖች ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን በምታደርገው ጉዞ ላይ ትብብራቸውን ለመቀጠልና አጋርነታቸውን ለማጠናከር ተስማምተዋል።

Want your business to be the top-listed Media Company in Washington D.C.?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address


Washington D.C., DC