Addis Monitor

Addis Monitor

Share

ለ21 ቀናት በእስር ላይ የቆየችው የአሃዱ ሬድዮ ጋዜጠኛ፤ በዋስትና ተፈታች - Ethiopia Insider 11/12/2021

ለ21 ቀናት በእስር የቆየችው የአሃዱ ሬድዮ ጋዜጠኛ፤ በዋስትና ተፈታች
21 ቀናት በእስር ላይ የቆየችው የአሃዱ ኤፍ ኤም ጋዜጠኛ ሉዋም አታክልቲ፤ በአስር ሺህ ብር ዋስትና ዛሬ አርብ ከእስር ተፈታች። የጣቢያው ዜና አርታኢ የሆነው ጋዜጠኛ ክብሮም ወርቁም፤ በ15 ሺህ ብር ዋስ እንዲፈታ በፍርድ ቤት መወሰኑን የጋዜጠኞቹ ጠበቃ አቶ ጥጋቡ ደሳለኝ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ይግባኝ ሰሚ ችሎት፤ ጋዜጠኛ ሉዋም በዋስትና እንድትፈታ የወሰነው ከሶስት ቀን በፊት ማክሰኞ ጥቅምት 30፤ 2014 ነበር። ሆኖም “በአሰራር አለመናበብ ችግር ምክንያት” እስከ ዛሬ ስድስት ሰዓት ድረስ ሳትፈታ በእስር መቆየቷን ጠበቃዋ አቶ ጥጋቡ ገልጸዋል።
ጋዜጠኛዋ በእስር ወደ ቆየችበት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ዛሬ ጠዋት የሄዱት ጠበቃዋ፤ “የፌደራል ፖሊስ በሌላ ጉዳይ ይፈልጋት እንደሆነ ማጣራት እንዲደረግ” በሚል ወደዚያው መላኳ እንደተነገራቸው ጠቅሰዋል። የፌደራል ፖሊስ ጋዜጠኛዋን በሌላ ጉዳይ እንደማይፈልጋት ካሳወቀ በኋላ፤ ሉዋም ዛሬ ምሳ ሰዓት ገደማ ከእስር ተፈትታ ከቤተሰቦቿ ጋር መቀላቀሏን አቶ ጥጋቡ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።
ዝርዝር ዘገባውን ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ፦

ለ21 ቀናት በእስር ላይ የቆየችው የአሃዱ ሬድዮ ጋዜጠኛ፤ በዋስትና ተፈታች - Ethiopia Insider – የጣቢያው ዜና አርታኢም በዋስትና እንዲፈታ በፍርድ ቤት ተወስኖለታል በሃሚድ አወል ለ21 ቀናት በእስር ላይ የቆየችው የአሃዱ ኤፍ ኤም ጋዜጠኛ ሉዋም አታክልቲ፤ በአስር ሺህ ብር ዋስትና...

11/05/2021

ደቡብ ጎንደር ወደ ግንባር ከተተ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ጎንደር ሕዝባዊ ሠራዊት የቀረበለትን የክተት ጥሪ ተቀብሎ ወደ ግንባር ከቷል።
የአማራ ሕዝብ የመኖር ሕልውና አደጋ ላይ ወድቋልና ለቀረበለት የክተት ጥሪ ፈጣን ምላሽ ሰጥቷል። ሕዝባዊ ሠራዊቱ የአማራ ሕዝብን አዋርዶ፣ ዘርፎና ገድሎ ኢትዮጵያን ለመበታተን የተነሳውን አሸባሪ ህወሓት ሳያጠፋ ወደ ቤቱ ላይመለስም ተማምሏል።
በመርኃ ግብሩ የአማራ ክልል የገጠር መሬት አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ ሲሳይ ዳምጤ፥ የሕልውና ዘመቻው የአማራ ክልልን ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያን እስከመጨረሻ ነጻ ለማውጣት እንደሆነ አብራርተዋል።
አቶ ሲሳይ እንዳሉት ጠላትን ማጥፋት የዘመቻው መዳረሻ ነው።
በሁሉም ግንባሮች ጠላት ዳግም በማያንሰራራበት ደረጃ ለመምታት ዝግጅት መደረጉን በመግለጽም መንግሥት ለዘማቾች አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።
የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኀላፊ ቀለመወርቅ ምህረቴ በበኩላቸው ዘማቾች ታሪክ እየሠሩ ካሉት የመከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኀይል፣ የፋኖ፣ የሚሊሻ አባላት እና የአማራ ሕዝብ ጋር ተሰልፈው ተልዕኳቸውን በጀግንነት እንዲወጡም አስገንዝበዋል።
ሀገርን እና የአማራን ሕዝብ ነጻ ለማውጣት የሚያጋጥሙ ፈተናዎችን ተቋቁሞ በጽናት መዋጋትና ማሸነፍ ብቸኛው አማራጭ ነው ያሉት ደግሞ የዞኑ ዋና አሥተዳዳሪ ይርጋ ሲሳይ ናቸው።
የሁሉም ወረዳ የፖለቲካ መሪዎች፣ ሚሊሻዎች፣ የፖሊስ አባላት እና ልምድ ያላቸው ምልስ የሠራዊት አባላት የመሪነት ሚናውን በአግባቡ እንደሚወጡ ተናግረዋል።
የሚሰጡ መመሪያዎችን አክብረው እንዲንቀሳቀሱ መልዕክት ማስተላለፋቸውን አሚኮ ዘግቧል።

10/21/2021

ስለ ሐይቅ ከተማ መረጃ!
ትናንት ማምሻውን ሐይቅ ከተማ በጠላት እጅ እንደወደቀች ተደርጎ በአንዳንድ የጠላትን አጀንዳ በሚያራግቡ ቅጥረኛ ኃይሎች ሲቀርብ የነበረው የበሬ ወለደ አሉባልታ ሀሰት ነው።
ሐይቅ ከተማ አሁንም በሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ በፌደራል ፖሊስ፣ በአማራ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ ቁጥጥር ሥር ስትሆን የደቡብ ወሎ ዞን፣ የተሁለደሬ ወረዳና የሐይቅ ከተማ አስተዳደር አመራሮች ከጸጥታ ኃይሉ ጋር ተቀናጅተው አመራር በመስጠት ላይ ይገኛሉ።
አሸባሪው፣ ጨፍጫፊው፣ ዘራፊውና ወራሪው የትግራይ ኃይል በውጫሌ፣ ተሁለደሬ፣ ወረባቦና ደላንታ ግንባሮች ጦርነት የከፈተብን ቢሆንም ህዝባችን ከጸጥታ ኃይሉ ጋር በመቀናጀት ሰርጎ ለመግባት እየሞከረ ያለውን ወራሪ ኃይል ወደ ቀሪ አካባቢዎች እንዳይገባ በአንድነት በመዝመት መመከት እንዲሁም አካባቢውን ከጸጉረ ልውጥ በመጠበቅ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ እናቀርባለን።

Want your business to be the top-listed Media Company in Washington D.C.?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Address


4853 7th Street NW
Washington D.C., DC