Saron Endale

Saron Endale

Share

05/13/2026

፣ ሶፋ ላይ ቁጭ እንዳልኩኝ ባለቤቴ በብርጭቆ ውሃ ሰጠችኝ፣ ልጄ አንድ ወረቀት ሰጠኝ ወረቀቱ ላይ የተፃፈው እንዲህ ይነበባል።😏

እንግሊዝኛ .......17 ከመቶ
ባዮሎጂ ...........35 ከመቶ
ሒሳብ ..............40 ከመቶ
ፊዚክስ .............37 ከመቶ
ኬሚስትሪ ..........42 ከመቶ
ኢኮኖሚክስ ........12 ከመቶ😏
እርሻ...................19 ከመቶ🤭
ጂኦግራፊ ...........22 ከመቶ

ንዴቴን መቆጣጠር አቅቶኝ " ይሄ ምንድነው? ሁልግዜ ሞባይል እና ቴሌቪዥን ላይ ነህ። እንዴት ይህን ማርክ ውጤት ብለህ ለማሳየት ደፈርክ?" በጩኽት ልጄን ተቆጣውት።🤔

ባለቤቴ " ትእግስት ይኑርህ አዳምጠኝ.... " ስትለኝ ። 🥺

ንግግሯን ሳትጨርስ "ዝም በይ ልጁን ያበላሸሽው አንቺ ነሽ! ከዚህ በኋላ መቼም ሰው አይሆንም " አልኳት ።🤧

ሚስቴ"ይገርማል! አለች።🤔😬

"በቤተሰባችን እንደዚህ አይነት የወረደ ውጤት ያመጣ የለም" በንዴት እና በጩኽት ተናገርኩኝ።🤭

ልጄ አጠገቤ መጣና " አባዬ ንዴት ውስጥ እንድትገባ ስለአደረኩህ አዝናለሁ ፤ ቁምሳጥኑን ሳፀዳ በ1977 ዓ.ም የአንተ የፈተና ውጤት ሪፖርት ነው"አለኝ ።😏

ስሙን ሳየው የእኔ የድሮ የትምህርት ቤት ውጤት ካርድ ነው፣ ስሜ በትልቁ የትፃፈበትን የፊት ለፊት ካርዱን አላየሁትም ነበር።🤣😬🤲

⬇️➡️ይላል ቀልዱ ደህና ሁኑልኝ🙌🙌🙌

05/12/2026

🌱ከ30-40 አመት ውስጥ ያላችሁ ሰዎች ልታነቡት የሚገባ!

🌱ይህ እድሜ ለጊዛዊ ስሜት፣ ለጊዛዊ ግንኙነት ፣ለጊዛዊ ስራና ለጊዛዊ ደስታ ብለህ ክርክር፣ ጭቅጭቅ፣ ፉክክር ፣ ስድብና ቁጣ ፣ንደትና ብስጭት ውስጥ የማትገባበት ለሆነው ላልሆነው ሁሉ አስተያየትና ቦታ የማትሰጥበት ውድ ጊዜ ነው።

🌱ይህ እድሜ ስለሰዎች አብዝተህ መጨነቅ አቁመህ ራስህን ብቻ ማየት የምትጀምርበት ልዩ እድሜ ነው። ምክንያቱም በማህበራዊም ሆነ በቤተሰባዊ ህይወትህ ከሰዎች ጋር ባለህ ግንኙነት አምነህ ብዙ መከዳቶችን ቀምሰህ አይተኸዋል።

🌱ይህ እድሜ ለስራህ ካልተከፈለህ ከአልጋህ አለመነሳትን የምትመርጥበት እድሜ ነው። ምክንያቱም እስከዛሬ በብዙ ሰዎች ጊዜህን አባክነው፣ ልብህን አቁስለው፣ ስሜትህን ጎድተው፣ ደግነትህን ተጠቅመው፣ ቅንነትህን እንደ ሞኝነት ቆጥረው በብዙ ሰዎች የጉልበት መበዝበዝ ደርሶብህ አይተኸዋል።

🌱ይህ እድሜ ሁሉንም ነገር በገንዘብ የምታሰላበት ጊዜ ነው። ምክንያቱም ከፈጣሪ በታች ገንዘብ ሀያል መሆኑን አግኝተህና አጥተህ አይተኸዋል።

🌱ይህ እድሜ ከብዙ ሰዎች የምትርቅበትና ብቻህን መሆንን የምትመርጥበት ጊዜ ነው። ምክንያቱም በቀረብካቸው የውሸትና ድራማ በሚያበዙ ሰዎች ተገፍተህ፣ ተንቀህ፣ ተጠልተህ፣ ተዋርደህ፣ ተጎድተህ፣ ተከድተህ፣ ተሰባብረህ ማገገም አቅቶህ አይተኸዋል።

🌱ይህ እድሜ ፈጣሪህን እንጅ ሰዎችን ማመን የምታቆምበት፣ በፈጣሪህ እንጅ በሰዎች መደገፍ የምትተውበት ጊዜ ነው። ምክንያቱም በአጉል ተስፋ የሞሉህ፣ ያታለሉህ፣ የተጠቀሙብህ፣ የበዘበዙህ ሰዎች ዛሬም በማስመሰላቸው ቀጥለው አይተሃቸዋል።

🌱ይህ እድሜ ባለፈው ብዙ የመሸወድ ፣ ብዙ የመታለል፣ ስለ ሰው ስትል ራስህን ያጣህበት፣ ማንነትህን ለማስረዳት ብዙ የደከምክበትን ማንነት ላይ ተስፋ በመቁረጥ አዲስ ማንነትን የምትወልድበት ጊዜ ነው።

🌱በዚህ እድሜ ክልል ያላችሁ ሁሉ የሰበሯችሁን በቃችሁ የምትሉበት፣ የበዘበዟችሁን ወግዱ የምትሉበት፣ የጎዷችሁንና ያቆሰሏችሁን ሰዎች ከህይወታችሁ ቆርጣችሁ የምትጥሉበት፣ የማይጠቅሙ ህመሞችን ከህይወታችሁ ነቅላችሁ የምታባርሩበት፣ አላስፈላጊ ድራማ ውስጥ የማትገቡበት ውድ ጊዜ ነው።

🌱ይህ እድሜ ቀልድ ቀንሰን ቁም ነገር የምንሰራበት፣ ከጥላቻ፣ ከቂምና ከበደል ወጥተን ፍቅርን፣ ደግነትን፣ ይቅርታን፣ ምስጋናን፣ መቻቻልን፣ መከባበርን፣ መተሳሰብን በእምነት የምንኖርበት ወርቃማ ጊዜ ነው።

🤌🏾ሁሉም ሰው ይማርበት ዘንድ ሸር አድርጉት🫶🏽




゚viralシfypシ゚viralシalシ

05/09/2026

👉 አንድ አዛውንት ሁለት ትኩስ ዳቦ ገዝቶ ወደ ቤቱ ይዞ እየሄደ እያለ በመንገድ ላይ ሦስት ድሆችና የተራቡ ልጃገረዶች በፍጥነት ወደ አዛውንቱ ቀረቡ። ሆዳቸው ዳቦውን ናፈቀ።

"እባክህ ጌታዬ፣ በምግብ እርዳን" ልጃገረዶቹ ሽማግሌውን ዳቦ እንዲሰጣቸው ለመኑ።

አዛውንቱ ከሶስቱ አንዷ ሴት ልጅ መስማትና መናገር የተሳናት እንደሆነች አስተዋለ፤ ምክንያቱም በምልክት ቋንቋ በግልጽ እየተናገረች ነበር።

"ሁለት ዳቦ ብቻ ነው ያለኝ። እንዴት ከሦስታችሁ ጋር ላካፍላችሁ ?" ሽማግሌው ጠየቀ።

ድንገት፣ አንዷ ልጅ በሹክሹክታ እንዲህ ብላ ተናገረች:-

"መናገርና መስማት የምንችል ሁለታችንም ዳቦውን መካፈል እንችላለን ። መስማትና መናገር የተሳናት ልጅ ምንም ማግኘት አትችልም"

"ግን ለምን ድርሻዋን አትወስድም?"አዛውንቱ ጠየቀ።

"ምክንያቱም እሷ ከእኛ የተለየች ስለሆነች"ልጅቷ መለሰች።

አዛውንቱ ለአንድ ሰከንድ ዝም አለና እንዲህ አለ:-
"እሺ... መናገርና መስማት የምትችሉት ሁለታችሁም አንድንድ ዳቦ ታገኛላችሁ። መስማት የተሳናት እና መናገር የማትችለው ልጅ ግን ምንም አታገኝም።"

በፍጥነት ሁለቱን ዳቦዎች ለሁለቱ ልጃገረዶች ሰጠና ሄደ። ልጃገረዶቹ በደስታ ዘለሉ።

መስማት እና መናገር የተሳናት ልጅ አዝና እና ተስፋ ቆርጣ ነበር። ሁለቱ ልጃገረዶች በደስታ ሲሄዱ ስትመለከት እንባዋን መቆጣጠር አልቻለችም።

ከጥቂት ሰዓታት በኋላ፣ አዛውንቱ የምግብ ከረጢት እና ትኩስ ወተት ይዞው ወደ ጎዳና መጣ። እንደገና አዛውንቱን ሲያዩ፣ ሦስቱም ምስኪኖቹ ልጃገረዶች ወደ እሱ ሮጡ።

በሚገርም ሁኔታ የምግብ ከረጢቱን እና ትኩስ ወተቱን መስማት እና መናገር ለተሳናት ልጅ ሰጠ። በጣም ተደነቀች። አዛውንቱም አንድ ወረቀት ሰጣት።

አዛውንቱ የሰጣት ወረቀት ስታነበው እንዲህ ይላል:-

"ምናልባት የምትፈልጊውን ካላገኘሽ የተሻለ ነገር ይጠብቅሻል!"
----------
----------

05/03/2026

🌀✅ የሶቅራጠስ 3ቱ ጠቃሚ ጥያቄዎች ✅🌀

አንድ ሠው ሶቅራጠስ ወዳረፈበት እልፍኝ ሄዶ እንዲህ አለው፡፡

‹‹ሶቅራጠስ ወዳጄ፣ እገሌ ስለተባለው ወዳጅህ ዛሬ የሠማሁት ነገር ምንም ደስ አይልም›› አለው፡፡

ሶቅራጦስ መከዳው ላይ እንደተደገፈ መልስ ሳይሰጠው ዝም አለ፡፡

ሠውየውም እንደገና ‹‹ይገርማል ከእርሱ አይጠበቅም፤ በጣም ገርሞኛል›› ሲል ተናገረ፡፡

ሶቅራጦስ፣ ይህ ሠው በቀላሉ እንደማይፋታው ስለተረዳ አንድ መደራደሪያ አቀረበለት፡፡ ‹‹ስለ ወዳጄ ልትነግረኝ የፈለግከውን እንድሠማህ ከፈለግህ ሶስት ጥያቄዎች አሉኝ፤ እነርሱን በቅድሚያ ልትመልስልኝ ይገባል! ይህ ሲሆን ብቻ ነው የምሰማህ›› አለው፡፡

ሠውየው ለወሬው ቢቸኩልም አማራጭ ስላልነበረው በሶቅራጠስ ሀሳብ ተስማማ፡፡

‹‹የመጀመሪያው ጥያቄዬ የእውነት ጥያቄ ነው" አለ ሶቅራጠስ። "ስለወዳጄ የሠማኸው መቶ በመቶ እውነት ነው ወይ?›› ሲል ጠየቀ፡፡

ሠውየውም፡- ‹‹መቶ በመቶ እንኳን እርግጠኛ መሆን አልችልም›› ሲል እያመነታ መለሰለት፡፡

‹‹በጣም ጥሩ! ልትነግረኝ የፈለግከው እርግጠኛ ያልሆነ ነገር ነው ማለት ነው፡፡ እሺ ሁለተኛው ጥያቄዬ የመልካምነት ነው፡፡ የምትነግረኝ መልካም ነገር ነው ወይ?›› ሲል ሶቅራጠስ አቀረበ ጥያቄውን፡፡

ሠውየውም፡- ‹‹እርሱማ መልካም አይደለም›› አለ ቱግ ብሎ፡፡ የሶቅራጠስ ጥያቄዎች ለማውራት የቋመጠለትን ወሬ እንዳያወራ እንቅፋት መስለው ታዩት።

ሶቅራጦስም ‹‹እውነትነቱ ያልተረጋገጠና መልካም ያልሆነ ነገር ልትነግረኝ ፈልገሃል፡፡ እሺ ሶስተኛውና የመጨረሻው ጥያቄዬን ልጠይቅህ?›› አለው፡፡

ሠውየውም ጥያቄውን ለመስማት ፈጥኖ ‹‹እሺ›› አለ፡፡

ሶቅራጦስ ጠየቀ፤ ‹‹የምትነግረኝ ነገር ለእኔ የሚጠቅመኝ ነገር አለው ወይ?››

‹‹የለም! የለም! መጥቀም እንኳን አይጠቅምህም። ብቻ ብትሰማኝ...›› ብሎ ሰውዬው መቅለስለስ ጀመረ።

ይሄን ጊዜ ሶቅራጦስ ‹‹ታዲያ እንደምን አድርጌ እውነትነቱ ያልተረጋገጠ፤ መልካም ያልሆነ እና ለእኔ ምንም ጥቅም የሌለው ነገር ልንገርህ ስትለኝ እንዴት እሰማሃለሁ። ዞር በል ካጠገቤ አልሰማህም!!›› አለው ይባላል፡፡

ስንቶቻችን ነን ሰው የሚነግረን ነገር እውነት፣ መልካምና ጠቃሚ መሆኑን አጣርተን የምንሰማው? ስንቶቻችን ነን ለሰው ቁምነገር ብለን ልንናገር ስንል ከሶስቱ አንዱን ማሟላቱን የምናረጋገጠው? አሁን እኮ ሰው ዝም ብሎ የተነገረውን ስለሚሰማ በቀላሉ እንደ እንስሳ የሚነዳ ሆኗል፡፡ በየሶሻል ሚዲያው ላይ ፖስት የሚደረጉት ብዙዎቹ መረጃዎች እውነት ያልሆኑ፣ መልካምነት የሌላቸው እና ለእኛ ምንም ጥቅም የማይሰጡ ናቸው፡፡ በተቃራኒው የውሸት መረጃዎች ሆነው ስንቱን ያጭበረበሩ፣ ሰይጣናዊ ርምጃ ለመውሰድ የሚገፋፉ ሆነው ሳለ ያለማቅማማት እንሰማቸዋለን፡፡

አሁን አሁን እውነት ከሚናገሩት ሰዎች በላይ በመርዝ የተለወሰ ውሸት የሚናገሩ ሰዎች የተሻለ ብዙ ተከታይ አላቸው፡፡ መልካም መልካሙን ከሚሰብኩ ሰዎች ይልቅ የጥፋት ሰባኪዎች ብዙ ደጋፊ አላቸው፡፡ ፍለጠው/ቁረጠው ባዮች ናቸው የጀገኑት፡፡ እነሱን ማስቆም አይቻል ይሆናል፤ ነገር ግን እነሱን አለመስማት/አለመከተል ቀላል ነው፡፡ እነዚህን የሶቅራጠስ 3ቱ ጥያቄዎችን እንደ ወንፊት ተጠቅመን ማጣራት ብቻ በቂ ነው፡፡ ✳✴✳

🚺🚹 ፅሁፉን ፣ጠቃሚ ሆኖ ካገኛችሁት ሼርርርር አድርጉት

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Washington D.C.?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address


Washington D.C., DC