Intelligent Group

Intelligent Group

Share

Photos from Intelligent Group's post 03/31/2024

ኢንተሊጀንት ግሩፕ በጎ አድራጎት ማህበር ለአንዲት እህት የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።
******************************
ኢንተሊጀንት ግሩፕ መጋቢት 22/07 /2016 ዓ. ም ሐዋሳ
ኢንተሊጀንት ግሩፕ በጎ አድራጎት ማህበር በትላንትናው እለት በይርጋዓለም ከተማ 05 ቀበሌ ለአንዲት እህት የቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል። ማህበሩ ከተቋቋመ ወዲህ የመጀመሪያውን ድጋፍ ያደረገ ሲሆን በቀጣይም መጠነ ሰፊ የበጎ አድራጎት ስራዎችን ለመስራት በይፋ ወደ ተጠናከረ እንቅስቃሴ መግባት ችሏል።

በትላንትናው እለት ወደ ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን በመሄድ ድጋፍ ያደረግንላት እህታችን ትርፌ ኢሳይያስ የምትባል ሲሆን ባለቤቷ ልጅ ከወለደች በኋላ እቤት ያለውን እቃ ሽጦ ጥሏት እንደጠፋና በአራስነት ጊዜዋ ብዙ አይነት ችግር እንደተፈራረቅባት ለራሷና ለልጇ የእለት ጉርስ እና ቤት ኪራይ ስትል የቀን ስራ እስከመስራት ደርሳ እንደነበር አጫውተናለች በዚህም ወቅት ስራው ከብዷት መታመሟንና በብዙ ስቃይ ውስጥ እንዳሳለፈች ከአንደበቷ መስማት ችለናል።
በአሁኑ ወቅት ደጋግ ቤተሰቦች በረንዳቸውን ተጠቅማ ሻይ ቡና አስጀምረዋት በመስራት ላይ ትገኛለች።
ማህበራችን ባለው አቅም ለሻይ ቡና መሰረታዊ የሆኑ ቁሳቁሶችን በድጋፍ መልክ የለገሳት ቢሆንም ይህ በቂ ባለመሆኑ ደጋግ ኢትዮጵያዊያን ድጋፍ እንዲያደርጉላት ማህበራችን ጥሪውን እያስተላለፈ ለጊዜው ለሻይ ቡና እንትድትጀምር የተፈቀደላት የሰው በረንዳ ከመሆኑም ባሻገር ቦታው የሰው እንቅስቃሴ የማይኖርበት መሆኑን ተከትሎ ወደተሻለ ቦታ እንዲትቀይር የገንዘብ እና የቁሳቁስ ድጋፍ እንዲታረጉላት እንማጸናለን።
#ለጊዜው በአዋሽ ባንክ የተከፈተ አካውንት አያይዘን አስቀምጠናል።
ስም ትርፌ ኢሳያስ 013561322627500 Awash Bank
ስልክ 0944353542
አድራሻ ይርጋዓለም 05 ቀበሌ ጋሽ ዛላ ጊቢ ፊትለፊት።
በተጨማሪም በማህበሩ አስተባባሪዎች በኩል እህታችንን ለመርዳት ከፈለጉ 0913657098/0946556549/ 0916407479/0926967865/0916551797

Want your organization to be the top-listed Non Profit Organization in Southern Pines?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address


Southern Pines, NC