Habesh in DMV

Habesh in DMV

Share

10/14/2024
01/20/2019

እህታችን ትእግስት ኩምሳ ወደ ሀገር አሜሪካ የመጣችው በ ዲቪ ሎተሪ ነው ህይወት እንዳሰበችው አሜሪካን አልጠበቀቻትም የተቀበለቻት ስፖስንሰሩዋ በደል ስላደረሰችባት ከቤት ወጣ ሆምለስ ወይም በረንዳ አዳሪ እንደሆነች የሚያቁዋት ይናገራሉ በመሆኑም በረንዳ እያለች አንድ ነጭ ሊደፍራት ሲሞክር ጩቤም እንደያዘ ስታቅ ህይወቱዋን ለማትረፍ ጩቤውን ታስጥለዋለች ሆኖም ይህ ግለሰብ ልትገለኝ ነው በሚል ሰበብ ፖሊስ ጋ ይደውላል እነሱም እሱን በማመን እሱዋን ለ እስር ይዳርጉዋታል እህታችን ያለ ጠያቂ ያለ ተከራካሪ በኬንታኪ ሉዝቬል ስቴት ከታሰረች ዘመን ተቆጠረ ባለፈው ለ ፀበል ሄጀ በነበረበት ወቅት እናቱዋን የሚያውቁ አንድ እናት እኔንም በዚህው እንዳስታውቅ ይተዋወቁኝ እና ታሪኩን አጫውተውኝ እናትየዋ ጋ በስልክ አገናኝተውኝ ነበር እናትም ማውራት ተስኖዋቸው በእለቅሶ ልጀ ልጀን ታደግልኝ ለኢትዮጵያውያን ንገርልኝ ብለው ተማፅነዋል ስለሆነም የህግ ባለሙያወች እንድትረድዋት አደራ ላለሁ ኬንታኪ የምትገኙ ኢትዮጵያውያን እስር ቤት ሄዳችሁ አለንልሽ በሉዋት በቅርብ አንድ መፍትሄ ከ እግዚአብሔር ጋር እናመጣለን እህታችንን ከ እስር ያስፈታልን አሜን።የምትገኝበትን እስር ቤት እና ሙሉ መረጃው አብሬ አታች አድርጌዋለሁ

Want your business to be the top-listed Media Company in Silver Spring?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address


13th Eastern Avenue
Silver Spring, MD
20910