Sidama Media Network-SMN
Nearby non profit organizations
1620 Elton Road #204
03/30/2026
የሲዳማ ብሄር አዲስ ዓመት – ፍቼ-ጫምባላላ በዋሽንግተን ዲሲ በድምቀት ተከበረ ።
*****************//*****************
ማርች 29, 2026
SMN ዲሲ
የሲዳማ ህዝብ የዘመን መለወጫ በዓል ፍቼ-ጫምባላላ በዓል በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በታላቅ ድምቀት ተከብሯል።
በዝግጅቱ ላይ በዲኤምቪ (DMV) አካባቢ የሚኖሩ የሲዳማ ማህበረሰብ አባላት፣ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች የተገኙ ሲሆን፤ በዓሉም የባህልና የአንድነት መንፈስ የታየበት ነበር።
የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዲኤምቪ አካባቢ የሲዳማ ማህበር ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጸጋዬ ጊምቦ፤ ለምክትል አምባሳደሩ፣ ለዲፕሎማቶችና ለታዳሚዎች ሞቅ ያለ አቀባበል ካደረጉ በኋላ፣ ስለ ባህላዊ እሴቶችና ስለ ማህበረሰቡ ጥንካሬ ገልጸዋል።
የኤምባሲው ምክትል አምባሳደር ባስተላለፉት መልዕክት፣ ባህልን ጠብቆ ማቆየትና ከሀገር ውጭ የሚኖረውን ማህበረሰብ ትስስር ማጠናከር ያለውን ፋይዳ አብራርተዋል።
የበዓሉ ልዩ ድምቀት የሆነውና የሲዳማን ማንነት የሚወክለው ባህላዊው ቀጣላ (Qexaala) የቀረበ ሲሆን፤ ታዳሚዎች ተወዳጁን የሲዳማ ባህላዊ ምግቦችን ሻፌታ እና ቡሪሳሜ ተጋርተዋል።
ከዕለቱ ዝግጅቶች መካከል ሁሉንም ያሳተፈው በምልክት ቋንቋ የመግለጽ ጫዎታና የጥያቄና መልስ መርሃ-ግብር ለታዳሚው ልዩ ደስታንና ፈገግታን የፈጠረ ነበር።
በመጨረሻም፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙርና የሲዳማ ክልል መዝሙር ተዘምሮ በዓሉ በታላቅ የአገር ፍቅርና የማንነት ኩራት ተጠናቋል።
አይዴ ጫምባላላ።
03/28/2026
AYIDDE CAMBALAALLA!
**********//*************
በዋሽንግተን ዲስ ለሚከበረው የሲዳማ ብሔር ዘመን መለወጫ ፍቼ ጫምባላላ በዓል በአክብሮት ተጋብዘዋል::
Date: March 29, 2026
Time: 1 - 5 PM EST
Address: 3506 International Dr NW,
Washington, DC 20008
03/20/2026
ፍቼ-ጫምባላላ በዓልን በሲያትል ዋሽንግተን በጋራ እናክብር!
**************//**************
SMN, ዲሲ
ማርች 2026.
በዩኒስኮ በዓለም ቅርሰነት የተመዘገበውና የሲዳማ ህዝብ የዘመን መለወጫ የሆነው ፍቼ-ጫምባላላ በዓል በሰሜን አሜሪካ ደረጃ ዘንድሮ በሲያትል ዋሸንግተን እንዲከበር በተወሰነው መሰረት ቅዳሜ March 28 ይከበራል::
ሁላችንም የጋራችን የሆነውን ድንቅ ፍቼ-ጫምባላላ በዓልን በጋራ እንዲናከብር ዘንድ በመላው አሜሪካ፣ ካናዳ እንድሁም በሲያትል ዋሸንግተን አቅራቢያ የምትገኙ አትዮጵያውያን በክብር ተጋብዛችኋል::
ፍቼ-ጫምባላል ስናከብር ስለሀገራችን ሰላም ፈጣሪን እንማፀናለን፤ አንድ የሚያደርጉንን ሰብዓዊ እሴቶችን እናስታውሳለን።
ቀን:- ማርች 28፣ 2026
ሰዓት:- ከቀትር በኋላ 12፡00 PM (ማምሻ ሰዓት)
ቦታ:- 7201 E Green Lake Dr. N, Seattle, WA 98115
እርሶና እና ቤተሰቦ በታላቅ ክብር ተጋብዘዋል!
አዘጋጅ ኮሚቴ ከሲዳማ ዲያስፖራ አለም አቀፍ ኮሚቴ ጋር በመተባበር።
Ayidde Chambalaalla!! 🎉 !!
03/14/2026
ኣይዴ ጫምባላላ!
*******//******
በዋሽንግተን ዲሲ፣ ቬርጅኒያ እና ሜሪላንድ አካባቢ የሚንኖር የሲዳማ ኬሙይኒቲ የ2026 ዓ ም የፍቼ-ጫምባላላ በዓልን በማርች 29, 2026 ከታች በተጠቀሰው ቦታና ሰዓት ስለምናከብር በዚህ ዓለማቀፋዊና ደማቅ ሀገር በቀል በዓል ከቤተሰብ፣ ወዳጅ እና ጓደኛ ጋር እንድትገኙልን እያልን ለአካባቢው ኢትዮጵያውያንን እና ወዳጆቻችን ጥሪ እናደርጋለን።
ቦታ:- 3506 International Dr. NW, Washington DC 20008
ቀን:- March 29, 2026
ሰዓት:- 1PM EST
አስፈላጊ ዝግጅቶችን ለማድረግ ያመቸን ዘንድ መገኘቶን በስልክ ቁጥር 202-556-0899 ቀድመው እዲያሳውቁን በአክብሮት እንጠይቃለን።
ከፕሮግራሙ አስተባባሪዎች
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the organization
Website
Address
DMV
Silver Spring, MD
20902