TkusNeger
የንጉስ ሚስት ትጨፍረው የለ እንዴ
05/31/2026
"ግሉኮስ እየተነቀለልኝ ካሜራ ፊት እቆም ነበር... አደራ የተሰጠኝ ፊልም ነው::"
ተዋናይት ፅናት ተረፈ (ህዶቴ)
ተዋናይት ፅናት በቅርቡ ተመርቆ ለእይታ በበቃው "ህዶቴ" በተሰኘው አዲስ ፊልም ላይ ባሳየችው አስደናቂ ብቃት የብዙዎችን ቀልብመግዛት ችላለች።
የሴት ልጅ ግርዛትን ማጠንጠኛ ባደረገው በዚህ ፊልም ላይ ስላጋጠማት ፈተና፣ ስለከፈለችው የጤና መስዋዕትነትእና ስለ ገፀ-ባህሪዋ ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 'መሰንበቻ' ፕሮግራም አግኝቶ አነጋግሯታል።
✍️ ያልጠበቀችው እውነት እና አደራው፦
"ዳይሬክተር ሳሚ ስክሪፕቱን ሲሰጠኝ በማንበቤ በጣም ደስ ብሎኝ ነበር። ሆኖም የሴት ልጅግርዛት አሁን ላይ የቆመ ይመስለኝ ስለነበር መጀመሪያ ላይ አላመንኩም ነበር። ዳይሬክተሩ ግን "አደራሽን፣ ጥሩ አድርገሽ
እንድትወጪው እፈልጋለሁ" ብሎ ትልቅ ሀላፊነት እና አደራ ነው የሰጠኝ።"
✍️ በግሉኮስ የታጀበው ከባዱ ቀረፃ፦
"ስራው እጅግ ከባድ ነበር። መሀል አካባቢ ላይ በጣም ታምሜ አልጋ ይዤ ነበር። ግሉኮስ እየተሰጠኝ ነበር ቀረፃውንያካሄድነው።
✍️ ስሜትን የሚፈትነው ትዕይንት፦
"የፊልሙ ስራ ከባድ የስሜት መለዋወጦችን የሚጠይቅ ነበር። በተለይ ደግሞ የግርዛቱ ሲን ላይ
ስሰራ ሙሉ ጉልበቴን እና ኢነርጂዬን አሟጦ ነበር የጨረሰው።"
✍️ የአንድ ወር ጥብቅ ልምምድ ፦
"ማንኛውንም ስክሪፕት ስቀበል የወረቀት ላይ ስራን በጥንቃቄ መስራትእወዳለሁ። ለዚህ ፊልምም ለአንድ ወር ያህል ከዳይሬክተሩ ጋር ጥብቅ ልምምድ አድርገናል። አለባበሷን፣አረማመዷን፣ ምን ትወዳለች፣ ምን ትጠላለች የሚለውን በጥልቀት አጥንተን ነው ወደ ቀረፃ የገባነው።"
✍️ የነገው የ"ህዶቴ" ጉዞ፦
"ፊልሙ አለም አቀፍ ደረጃን ጠብቆ የተሰራ በመሆኑ የተነሳየተለያዩ አለም አቀፍ የፊልም ፌስቲቫሎች ላይ ይሳተፋል ብዬ ትልቅ ተስፋ አደርጋለሁ።
05/28/2026
ሮሚዮ እና ጁሌት ተጣሉብን እኮ 🙈
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Website
Address
San Jose, CA