Merr Queen

Merr Queen

Share

06/23/2026

"የጀመርናቸው ለውጦች በራሳቸው የመጨረሻ ግብ አይደሉም"
ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

የጀመርናቸው ለውጦች በራሳቸው የመጨረሻ ግብ አይደሉም፤ ይልቁንም ከእኛ በኋላ ለሚመጡት ተከታታይ ትውልዶች የምንጥለው ጠንካራ መሠረት ነው።‎ሀገርን መገንባት በአንድ ትውልድ ብቻ የሚያበቃ ሳይሆን የሁላችንም የጋራና ቀጣይነት ያለው ሥራ በመሆኑ፤ በዚህ ጽኑ እምነት እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ይህንን መንፈስ ይዞ ወደፊት እንዲጓዝ፣ የተቀበለውን ወረት አግዝፎ ይበልጥ ወደ ላቀ ከፍታ እንዲያመራ ጥሪዬን አቀርባለሁ!

#ኢትዮጵያ

06/23/2026

ሀገራችን በራሷ አቅም ያልተሞከሩ ግዙፍ ልማቶችን በማከናወን በየጊዜው ወደ ላቀ ደረጃ እየተሸጋገረች ትገኛለች
ጠ/ሚ/ር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ

‎“ኢትዮጵያ ታከናውናለች” በተሰኘው ብሔራዊ ጉባኤ ላይ በመገኘቴ ታላቅ ክብር ይሰማኛል። “ከለውጥ ወደ ዘላቂ ሽግግር” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ባለው ጉባኤ ላይ፣ በየደረጃው የተጓዝንበትንና አሁን የደረስንበትን መንገድ መለስ ብዬ እንድቃኘው አድርጎኛል። ሀገራችን በራሷ አቅም ታላቁን የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በመገንባት፣ ያልተሞከሩ ግዙፍ ልማቶችን በማከናወን በየጊዜው ወደ ላቀ ደረጃ እየተሸጋገረች ትገኛለች። እነዚህ ሁሉ በአጋጣሚ የተገኙ ድሎች ሳይሆኑ በመደመር መንፈስ ላይ ተመስርተው፣ ዘላቂ ለውጥ የሚመጣው በጋራ በመቆም ነው፤ በሚል ጽኑ እምነት የተወሰዱ፣ በቆራጥ ውሳኔዎች የተገኙ ውጤቶች ናቸው።

‎የጀመርናቸው ለውጦች በራሳቸው የመጨረሻ ግብ አይደሉም፤ ይልቁንም ከእኛ በኋላ ለሚመጡት ተከታታይ ትውልዶች የምንጥለው ጠንካራ መሠረት ነው።
‎ሀገርን መገንባት በአንድ ትውልድ ብቻ የሚያበቃ ሳይሆን የሁላችንም የጋራና ቀጣይነት ያለው ሥራ በመሆኑ፤ በዚህ ጽኑ እምነት እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ይህንን መንፈስ ይዞ ወደፊት እንዲጓዝ፣ የተቀበለውን ወረት አግዝፎ ይበልጥ ወደ ላቀ ከፍታ እንዲያመራ ጥሪዬን አቀርባለሁ!

#ኢትዮጵያ

06/20/2026

ከጦርነት እፎይታ ወደ አዲስ ስጋት፡ የትግራይ ህዝብ እና የህወሃት ውሳኔዎች

የትግራይ ህዝብ በፕሪቶሪያው ስምምነት ከግጭት ወጥቶ እፎይታ አግኝቷል። የመሰረታዊ አገልግሎቶች ተጠቃሚ ሆኗል። ስምምነቱ የመልሶ ግንባታ ስራ እንዲጀመር እና ኢኮኖሚው እንዲነቃቃ አድርጓል። ተፈናቃዮችን ወደ ቤታቸው መመለስ እንዲጀምሩም አድርጓል። ይሁን እንጂ ህወሃት የስምምነቱን ትግበራ ሲያደናቅፍ ቆይቶ በመጨረሻም ህገወጡን የክልሉን ምክር ቤት በመመለስ ስምምነቱን ሙሉ በሙሉ አፍርሶ ግጭት ቀስቅሶ ህዝቡን ለሌላ መከራ ሊዳርግ እየተዘጋጀ ነው።

06/20/2026

"በዘመን ውስጥ ተወዳድረን የሚገባንን ለማግኘት ቴክኖሎጅ በጣም ወሳኝ ነው"
‎ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

‎የአገልግሎት ዘርፉን ይበልጥ በማፋጠን፣ የህዝባችንን ፍላጎት ለማሟላት ሁላችንም በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜት መስራት ይጠበቅብናል።

06/20/2026

‘መሶብ’ አንድ ሰው ሁሉንም ወሳኝ የመንግሥትና የፋይናንስ አገልግሎቶች በአንድ ማዕከል እንዲያገኝ የሚያስችል የዲጂታል እመርታ ነው"
ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

Want your business to be the top-listed Media Company in Miami?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address


Zambia
Miami, FL