Highway Star
21/04/2021
በሃገራችን የስቶክ ማርኬት ሊጀመር ነው!
ስቶክ ማርኬት ምንድን ነው?
ስንት አይነት ስቶኮች አሉ? ጥቅሙስ ምንድን ነው?
እንዴትስ ልንገበያይ እንችላለን?
24/03/2021
ስራ እና አዎንታዊ አስተሳሰብ (Positive thinking)
ወደ ስራ
በስራም ሆነ በትምህርት አለም ውስጥ አዎንታዊ አስተሳብ እንዲኖረን ይመከራል፡፡ይሄ ማለት አእምሯችንም ሆነ ስሜታችንን ተቆጣጥርን በቻልነው አቅም ጥሩ እና መልካም ነገሮች ላይ ብቻ ማተኮር እና ማሰብ እና በስራችንም ሆነ በትምህርታችን ላይ መልካም ነገር ያጋጥመናል ብሎ ማመን ነው፡፡ ስለዚህ አስተሳሰባችን በአዎንታዊነት ከተቃኘ የምናስበው ስኬትን ማግኘትን ብቻ ነው፡፡
ስለዚህ በስራ ቦታችን ይሄንን አዎንታዊ አስተሳሰብ ብንይዝ ስራችን ቀለል ብሎን መስራት እንችላለን ማለት ነው፡፡
ለምሳሌ፡-
1. ስራችንን ስንጀምር፤ ጠዋት ላይ መልካም ነገሮችን በማሰብ እና በመናገር ብንጀምር ይመከራል፡፡
ብዙ ቢሮዎች ውስጥ የምትለጠፍ አንድ ጥቅስ አለች፡፡ ዛሬ ቀኑ ደስ ይላል ወይም ዛሬ ደስ የሚል ቀን ነው ይላል ጥቅሱ፡፡ ይሄ እንግዲህ ጠዋት ሲገቡ ያንን ጥቅስ በማየት ቀኑን ደስ በሚል ስሜት ለመጀመር ነው፡፡ ስለዚህ ስራችንን እና ቀኑን መልካም ነገር በማሰብ እና በመናገር መጀመር ይቻላል፡፡
2. በስራ ቦታ ላይ አብረውን የሚሰሩ ሰዎች ፖዘቲቭ (ቀና አስተሳሰብ) ያላቸው ቢሆኑ ይመረጣል፡፡ አብረውን የሚሰሩ ሰዎችን መምረጥ ባንችልም ከነሱ ጋር የምናሳልፈውን ጊዜ ግን መገደብ እንችላለን፡፡ ስራ ቦታ ላይ አብረናቸው የምንሰራ ሰዎች ለነገሮች ቀና አመለካከት ያላቸው እና ለስራ ፍቅር ያላቸው ቢሆኑ ይመረጣል፡፡ እንደዚህ አይነት ሰዎች ለስራ ተነሳሽነት እንዲኖረን ያደርጉናል ያ ቀና አስተሳሰብ ይጋባል፡፡
3. የሚሰራ ሰው መሳሳቱ አይቀርም ስለዚህ ስራ ላይ ስህተት ሊፈጠር ይችላል፡፡ እንዲህ አይነት አጋጣሚዎች ሲፈጠሩ ስህተቱን ለመማር እና እራሳችንን ለማሻሻል ብንጠቀምበት ጥሩ ነው፡፡
ስህተት ስንሰራ ሌላ ሰው ላይ ስህተቱን ለማላከክ ከመሮጥ፤ ወይንም ደግሞ እኔ አላረኩትም ብሎ ከመከራከር ከዚህ ስህተት ምን መማር እችላለሁ፤ በሚቀጥለው ጊዜ ይሄን አይነት ሁኔታ ሲያገጥመኝ ምን ማስተካከል እችላለሁ የሚለውን ማሰብ ጥሩ ነው፡፡
4. ሌላው ነገር ደግሞ ከራሳችን ጋር ስናወራ አሉታዊ የሆነ እና ጨለምተኛ የሆነ ወሬዎችን ማውራት ማቆም አለብን፡፡ ለምሳሌ፡- አሁን የተሠጠኝን አዲስ ስራ እያበላሸሁት ነው፡፡ ዝም ብዬ እኮ ነው ከበድ ስራ ማን ተቀበይ አለኝ፡፡ እኔን ብሎ ታታሪ ሰራተኛ አይነት ወሬዎች ከራሳችን ጋር የምንጨዋወት ከሆነ ይሄ ለራሳችን ጨለምተኛ አመለካከት ያዝን ማለት ነው፡፡ ከውጪ ወይም ከሌላ ሰው ማበረታቻ ወይም አድናቆት ከመጠበቃችን በፊት ራሳችንን ማበረታት እና የተሻለ ስራ ለመስራት ማነሳሳት አለብን፡፡
09/03/2021
ኢንቨስትመንት ግን ምንድን ነው?
ዩሴን ቦልት በሶስት ኦሎምፒኮች ተሳትፎ 8 የወርቅ ሜዳሊያ አሸንፏል፡፡
በኦሎምፒክ ውድድሮች ላይ 115 ሰከንዶችን ብቻ ሮጧል፡፡ በዚህ ግዜ ግን ከ110 ሚሊየን ዶላር በላይ ለማግኘት በቅቷል፡፡ ለነዚህ 2 ደቂቃዎች ሲል ግን ከ20 አመታት በላይ በልምምድ አሳልፏል፡፡
ኢንቨስትመንት ሩቅ ማሰብ ማለት ነው፡፡ አለመታከት እና ትእግሰት ሁሌም ዋጋቸው ትልቅ ነው፡፡
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Telephone
Website
Address
Riyadh