T KDM

T KDM

Share

02/09/2020

አንደኛው በር ሲዘጋብህ አላህ ሌላኛውን በር ይከፍትልሀል።

02/09/2020

አስተማሪ #ታሪክ

@ለሌሎች ሰዎች በምትቆፍረው ጉድጓድ
እንዳትወድቅ ጥንቃቄ አድርግ !!

ከሚስቱ ጋር በተፈጠረ አለመግባባት የተነሳ ሚስቱን
በያዘው ዱላ ይመታት ጀመር እርሷን መግደል ሳይፈልግ
በአጋጣሚ ሂወቷ አለፈ
በተከሰተው ነገር በእጅጉ ተደናገጠ ፍርሀት ተሰማው
ከቤተሰቦቿ ከሚደርስበት ቅጣት ለማምለጥ ምክኛት ቢፈልግም ሊያገኝ አልቻለም

ከቤቱ በፍጥነት ወጣ ወደ አንድ የሚያውቀው ሰው ዘንድ ሄደና የሆነውን ነገር አጫወተው ሚስቱን ለመግደል ሳያስብ እንደገደላት ነገረው ከገባበት አጣብቂኝ ውስጥ እንዲያስወጣው መላ ይዘይድለት ዘንድ ጠየቀው

ሰውየውም አንድ መልከ መልካም ወጣት ሰው ፈልግና ለእንግድነት ወደ ቤትህ ጋብዘው

ከዚያም አንገቱን ቆርጠህ የሚስት አስክሬን አጠገብ ጣለው
ለሚስትህ ቤተሰቦቿ ይህን ወጣት በሚስቴ ላይ ዝሙት ሲሰራ አገኘሁት ራሴን መቆጣጠር አቅቶኝ ሁለቱንም ገደልኻቸው በል አለው

ሰውየው በመፍትሄው ሀሳብ ተስማምቶ በር ላይ ቁጭ ብሎ የሰውን መምጣት ይጠባበቅ ጀመር አንድ መልከ መልካም ወፈር ያለ ወጣት ሲመጣ ለእንግድነት ቤቱ እንዲገባ ጠየቀው
ቤቱ ሲገባ ወዲያው ገደለው እንደተባለው አደረገ

የሚስቱ ቤተሰቦች ሲመጡ ሁለት አስክሬን ተመለከቱ
ሚስቴ ላይ ዝሙት ሲሰራ አገኘሁት ራሴን መቆጣጠር አቅቶኝ ገደልኻቸው አላቸው
በእጅጉ አዘኑ ትተውት ሄዱ

መፍትሄውን የነገረው ሰው ልጅ ነበረው

የዛን ቀን ወደ ቤቱ አልመጣም ነበር አባት ተጨንቆ ሚስቱን ወደ ገደለው ሰው ቤት ሄደ
የነገረውን ማምለጫ ዘዴ መተግበሩን ጠየቀው
ሚስቱን የገደለውም ሰው ምክሩን ተግባራዊ እንዳደረገ ነገረው
የገደልከውን ወጣት አሳየኝ አለው የተገደለውን ወጣት ጀናዛ ሲመለከት የራሱ ልጅ ነበር አባቱ የመፍትሄ የማምለጫ መንገድ ብሎ ሚስቱን ለገደለው ሰው በመከረው ምክር ሰበብ ተገድሎ ነበር

======================

ኢማም አልይ ቢን አቡ ጧሊብ ረዲየላሁ አንህ እንዲህ ብሎ ነበር ድንበር አላፊ የሆነችን ሰይፍ የሳለ ሰው በሳለው ሰይፍ ይገደላል ለወንድሙ ጉድጓድን የቆፈረ ሰው በቆፈረው ጉድጓድ ይወድቃል የሌሎች ሰዎችን ነውር የከፈተ ሰው የቤቱ ነውር ይከፈታል::

Want your school to be the top-listed School/college in Jeddah?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Website

Address


Jeddah