Sata Media Service
17/04/2026
ሐገሪቷ እርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ እንድትገባ በገንዘብና በአረቄ ቤት እንጉርጉሮ ስደግፍና ስያቀላጥፍ የከረመ ወመኔ ሰው "ዳስጣል" ባለው እንጉርጉሮ እንዲህ ብሏል ቡሌ የማይሰለቸው ው*ሻ
👇
"አክሱም ላሊበላን በአንድ አለት አፅንቶ
አልራመድ አለ ሐገር ተለያይቶ
ምሰሶው ዘመመ ጣራው ያፈሳል
ሐገር የሞተበት የት ሄዶ ያለቅሳል
ባሳደገኝ ቀዬ ባደኩበት መንደር
ባይተዋር ሰው ሆኜ እንደለለው ሐገር
ያቆምኳትን ሰንደቅ ተፈትኜ በእሳት
እንዴት አቀርቅሬ ባንድራዬን ላንሳት..."
24/02/2026
የአባይ(ናይል) ወንዝ አስገራሚ እውነታዎች
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
1. ርዝመቱና መገኛ ቦታው
* የዓለም ረጅሙ ወንዝ፦ ናይል በግምት 6,650 ኪሎ ሜትር ይረዝማል። በአጠቃላይ በ11 የአፍሪካ ሀገራት (ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ግብፅ፣ ኬንያ፣ ታንዛኒያ፣ ኡጋንዳ፣ ሩዋንዳ፣ ብሩንዲ እና ኮንጎ) ውስጥ ያልፋል።
* መጋቢዎቹ፦ ናይል ሁለት ዋና ዋና መጋቢዎች አሉት። እነሱም ጥቁር ዓባይ (Blue Nile) ከኢትዮጵያ የሚነሳው እና ነጭ ዓባይ (White Nile) ከመካከለኛው አፍሪካ (ቪክቶሪያ ሐይቅ) የሚነሳው ናቸው።
2. የኢትዮጵያ ድርሻ (ጥቁር ዓባይ)
* የውሃ መጠኑ፦ ለናይል ወንዝ ከሚገብረው አጠቃላይ የውሃ መጠን ውስጥ ከ85% በላይ የሚሆነው የሚመነጨው ከኢትዮጵያ ተራሮችና ከጣና ሐይቅ ነው።
* ደለል፦ ዓባይ ከኢትዮጵያ ተራሮች ተነስቶ ወደ ሱዳንና ግብፅ ሲጓዝ እጅግ ለም የሆነ ጥቁር አፈር (ደለል) ይዞ ይሄዳል። ይህ አፈር ለሺህ ዓመታት የግብፅ ግብርና መሠረት ሆኖ ቆይቷል።
3. ታሪካዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳው
* የስልጣኔ መገኛ፦ ጥንታዊው የግብፅ ስልጣኔ ሊገነባ የቻለው በናይል ወንዝ ምክንያት ነው። ግብፃውያን ወንዙን እንደ አምላክ ያዩት ነበር፤ ምክንያቱም ያለ ናይል ግብፅ በረሃ ብቻ ትሆን ነበር።
* ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ (GERD)፦ በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ የምትገነባው ግድብ በአፍሪካ ግዙፉ የኃይል ማመንጫ ሲሆን፣ ለሀገሪቱና ለቀጣናው ትልቅ የኤሌክትሪክ ብርሃን ተስፋ ነው።
4. አስገራሚ እውነታዎች
* ወደ ሰሜን መፍሰሱ፦ አብዛኞቹ የዓለም ወንዞች ወደ ደቡብ ወይም ወደ ጎን ሲፈሱ፣ ናይል ግን ከአፍሪካ ልብ ተነስቶ ወደ ሰሜን አቅጣጫ በመጓዝ ሜዲቴራኒያን ባሕር ውስጥ ይገባል።
* የወቅት መለዋወጥ፦ በክረምት ወቅት በኢትዮጵያ ዝናብ ሲበዛ የዓባይ ውሃ መጠን እጅግ ይጨምራል። ይህ ወቅታዊ ሙላት ለዘመናት "የናይል ጎርፍ" ተብሎ ይታወቅ ነበር።
22/02/2026
የአሜሪካ እና የኢራን ወቅታዊ ሁኔታ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖
በአሁኑ ወቅት በኢራን እና በአሜሪካ መካከል ያለው ግንኙነት እጅግ ውጥረት የነገሰበት እና ወታደራዊ ግጭት ሊቀሰቀስ ይችላል የሚል ስጋት ያደረበት ነው። ዋና ዋናዎቹ ወቅታዊ ሁኔታዎች የሚከተሉት ናቸው፦
1. የኑክሌር ድርድር እና የአሜሪካ ማስጠንቀቂያ
* የጊዜ ገደብ፦ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን አዲስ የኑክሌር ስምምነት እንድትፈርም ከ10 እስከ 15 ቀናት የሚቆይ ጥብቅ የጊዜ ገደብ ሰጥተዋል።
* ጥገኛው ድርድር፦ በኦማን እና በጄኔቫ በኩል በተዘዋዋሪ መንገድ ንግግሮች ቢደረጉም፣ አሜሪካ ኢራን የዩራኒየም ማበልጸግን ሙሉ በሙሉ እንድታቆም እና የሚሳኤል ፕሮግራሟን እንድትገድብ በጽኑ እየጠየቀች ነው።
* የኢራን አቋም፦ የኢራን ባለስልጣናት ለሰላማዊ ጥቅም ዩራኒየም የማበልጸግ መብት አለን በማለት ድርድሩ ላይ ጥብቅ አቋም ይዘዋል።
2. ወታደራዊ ዝግጅት
* የአሜሪካ ወታደራዊ ኃይል፦ አሜሪካ በመካከለኛው ምስራቅ መጠነ ሰፊ የሆነ የጦር መርከቦች፣ የአውሮፕላን ተሸካሚዎች እና የጦር ጄቶች ክምችት እያደረገች ትገኛለች። ይህም ኢራን ድርድሩን ካልተቀበለች ወታደራዊ ጥቃት ሊሰነዘር እንደሚችል የሚያመላክት ነው።
* የኢራን ምላሽ፦ ኢራን ወታደራዊ ጣቢያዎቿን በማጠናከር ላይ ስትሆን፣ ማንኛውም ጥቃት ቢሰነዘርባት የአጸፋ እርምጃ እንደምትወስድ በማስጠንቀቅ ላይ ናት።
3. የኢራን ውስጣዊ ሁኔታ እና ማዕቀቦች
* ተቃውሞዎች፦ በኢራን ውስጥ በኢኮኖሚ ቀውስ እና በፖለቲካዊ ጫናዎች ምክንያት ከፍተኛ የህዝብ ተቃውሞዎች በመካሄድ ላይ ናቸው። አሜሪካ እነዚህን ተቃዋሚዎች እንደምትደግፍ በግልጽ አስታውቃለች።
* አዳዲስ ማዕቀቦች፦ አሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረት በኢራን የነዳጅ ንግድ እና በጸጥታ ኃይሎች ላይ ተጨማሪ ማዕቀቦችን ጥለዋል።
4. የቀጠናው ሁኔታ
* እንደ ኳታር እና ኦማን ያሉ ሀገራት ጦርነት እንዳይቀሰቀስ ለማስታረቅ ጥረት እያደረጉ ቢሆንም፣ የእስራኤል እና የኢራን ቀጥተኛ ግጭት ስጋት ሁኔታውን ይበልጥ ውስብስብ አድርጎታል።
ባጠቃላይ ሁኔታው በዲፕሎማሲያዊ ስምምነት ወይም በከፋ ወታደራዊ ግጭት ሊጠናቀቅ በሚችልበት ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ይገኛል።
Sata Media Service
12/11/2025
ግንባታው ብጠናቀቅም ነዳጅ የተከለከሉ ጋዴዎች ቅሬታ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
በሐገር አቀፍ ደረጃ ያለውን የነዳጅ አቅርቦት ችግር ለመቅረፍ በተለያዩ አከባቢዎች ማለትም በተለያዩ ክልሎች ከሚመለከተው መንግሥት አካል የችርቻሮ ነዳጅ መሸጫ ፈቃድ ወስደው የነዳጅ የማደያ ግንባታ ማጠናቀቃቸውን እነዚህ ቅሬታ አቅራቢዎች ገልፀዋል።
በተለይም ከደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግሥትና በየደረጃው ከሚገኙ ከመንግሥት አካላት የግንባታ ፈቃድ ተሰጥቷቸው በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ በዚሁ ሥራ ማዋላቸውን የገፁት ቅሬታ አቅራቢዎች ከፕሮጀከት ግምገማ እስከ ግንባታ አፈጻጸም የመንግሥት ተቆጣጣሪ አካላት ክትትልና ቁጥጥር እንዳልተለያቸውም አስረድተዋል።
በክልሉ በዚሁ ዘርፍ የመሥራት ፈቃድ ተስጥቷቸው ግንባታ ያከናወኑ ከ171 በላይ ነጋዴዎች እንዳሉም ያገኘነው መረጃ የሚመላክት ስሆን እነዚህ ሁሉ የክልሉ መንግሥት ባደረገው ፍተሻ ያለፉና በሙሉ አቅም ወደ ሥራ የመግባት ብቃት ያላቸው መሆናቸውንም ጠቁመዋል።
ነገር ግን በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ መድበው ግንባታውን ካጠናቀቁ በኋላ ምንም ሕጋዊና አሳማኝ የሆነ ምክንያት ሳይቀርብ በፖለቲካ ውሳኔ ብቻ ከአቅራቢዎች ነዳጅ እንዳይረከቡ በመንግሥት አካላት መከልከላቸውን ቅሬታ አቅራቢዎች ገልፀዋል።
ሆኖም ከዚህ ቀደም በዘርፉ ተሰማርተው ላሉና ለመንግሥት ባለሥልጣናት ቅርበት ላላቸው ጥቂት ግለሰቦች ነዳጅ የመረከብ ፈቃድ ግልፅ ባልሆነ መንገድ መሰጠቱን የጠቆሙት እነዚህ ቅሬታ አቅራቢዎች ቦታዎቹም አሁን ካለው ከትራስፖርት ፍሰትና ከተገልጋዩ ሕብረተሰብ ፍላጎት አንፃር በቂ የሚባል ማጣራት ያልተደረገቢቸው እንደሆኑም ነው።
ከእነዚህም ከዎላይታ ዞን ለ3 እና ከጋሞ ዞን ለ5 ግለሰቦች ብቻ ሥራውን የመጀመር ፈቃድ መሰጠታቸውን ያገኘነው መረጃ የሚያመላክት ስሆን ማደያዎቹ ሥራ እንድጀምሩ የተፈቀደባቸው ቦታዎች በረሃዎች፣ ብዙ የተሽከርካሪና የሕዝብ ፍሰት የለለባቸው፣ ለኮንትሮባንድ ንግድ ምቹና እንደመተላለፊያ የሚያገለግሉ፣ ሕብረተሰቡ እንድጠቀሚበት የሚመጣውን ነዳጅ ያለከልካይ ለማዘዋወር የሚመቹና መሰል ችግሮች ያሉባቸው ናቸው።
በሚሊሺያዎችን የሚቆጠር መድበው ግንባታውን ካጠናቀቁ በኃላ ይህ ዱብዳ የሆነ የፖለቲካ ውሳኔ የተላለፈባቸው እነዚህ ቅሬታ አቅራቢዎች፣ ፈቃድ የሰጣቸው የክልሉ መንግሥት ጉዳዩን እንዲያጠነውና ተገቢ ምላሽ እንድሰጥ በዘርፉ የተሰማሩ ነጋዴዎች ተደራጅተው ጥያቄ ብያቀርቡም የክልሉ መንግሥት ባለሥልጣናት "ያገድነው እኛ ሳንሆን የፌዴራል መንግሥት ነው" የሚል ምላሽ መስጠታቸውንም አስረድተዋል።
በእጃቸው የነበረውን ገንዘብ በዚሁ ሥራ አውለው ሠርተው ለመተካት አልመው፣ ባልተጠበቀ መንገድ ተስፋቸው የተመናመነባቸው እነዚህ ነጋዴዎች የክልሉ እና የፌዴራል መንግሥታት ይህን ያልተጠበቀና ብዙ ኪሳራ ያመጣባቸውን ውሳኔ እንድያጠኑ፣ ፍትሃዊና ሕጋዊ አሰራር እንድከተሉ፣ በፍጥነት ወደ ሥራ የሚገባበት ሁኔታ እንድያመቻቹ ስሉም ተማፅነዋል።
Kenyans communication culture and its value to minimize conflict
BREAKING NEWS : UN GENERAL ASSEMBLY (140+ member countries) Recognized Palestinian State
SMS WOLAITA DICHA FC vs AL ITTIHAD FC replay
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
Kenya
Nairobi
00000