Wolaita Post

Wolaita Post

Share

Photos from Wolaita Post's post 18/01/2026

#የወላይታ ንጉሥ የነበሩ የካዎ ጦና ሐውልት መጪው ማክሰኞ ዕለት ጥር 12/2018 ዓ.ም ይመረቃል።

Photos from Wolaita Post's post 18/01/2026

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የገበታ ለትውልድ የመጀመሪያውን መዳረሻ ደንቢ ኢኮ ሎጅን በይፋ መረቁ

📍በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የተገነባው ይህ ሎጅ በ36.7 ሄክታር ጥብቅ ደን ላይ ያረፈ ነው፡፡

🔊 የደንቢ ኢኮ ሎጅ የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት፤ ከገበታ ለሸገር እና ገበታ ለሀገር መርኃ-ግብሮች የቀጠለ እና ሥራዎቹን ወደ አዳዲስ አካባቢዎች የወሰደ ነው ተብሏል፡፡

💬 “ሥራው ከአካባቢው በተገኙ የግንባታ ቁሳቁሶች እና በአካባቢ አቅም የተገነባ በመሆኑ ዘላቂነትን እና ባለቤትነትን ያንፀባርቃል” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ተናግረዋል።

Photos from Wolaita Post's post 16/01/2026

ዜና ዕረፍት

ተወዳጁ አርቲስት ነጻነት ወርቅነህ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

ተወዳጁ የኪነ-ጥበብ ባለሙያ ነጻነት ወርቅነህ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

በፊልም እና ቲያትር ተዋናይነት፣ በቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢነት እና በሌሎች የጥበብ ስራዎች ውስጥ ስመጥር እና ተወዳጅ ከሆኑ የጥበብ ሰዎች አንዱ የሆነው ነጻነት ወርቅነህ ባደረበት ህመም በድንገት ህይወቱ ማለፉ ነው የተገለፀው።

ለበርካታ ዓመታት በኢቢኤስ ቴሌቪዥን የሚተላለፈው የቤተሰብ ጨዋታ ፕሮግራም አዘጋጅና አቅራቢ የሆነው ነጻነት ወርቅነህ ባለትዳርና የ3 ልጆች አባት እንደነበር ከኢቢስ ቴሌቪዥን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Photos from Wolaita Post's post 05/01/2026

ከወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር የተሰጠ የአድራሻ ለውጥ ማሳሰቢያ!!

የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት፣የወላይታ ሶዶ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት እና በከተማ አስተዳደር ግቢ የሚገኙ መምሪያዎች በሙሉ በአዲሱ የከተማ አስተዳደር ህንጻ ግንባታ ምክንያት ከዚህ በፊት ለክቡራን ተገልጋዮች አገልግሎት ሲሰጥ የቆየበትን የአድራሻ ከታህሳስ 27/2018 ዓ.ም ጀምሮ ዋዱ ተብሎ በሚታወቀው ሠፈር ከእንያት ሆስፒታል ወረድ ብሎ ታፍ የነዳጅ ማደያ ፊት ለፊት በሚገኘው ህንፃ አገልግሎት እንደሚሰጥ አሳውቋል ።

በመሆኑም አገልግሎት ፈላጊዎች በሙሉ በተጠቀሰው ቦታ ተገኝተው መስተናገድ የሚችሉ መሆኑን ገልጿል ።

Want your business to be the top-listed Media Company in Sodo?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Address


Gununo
S**o