Apostolic generation

Apostolic generation

Share

05/03/2026

ጥምቀት ያድናል።
በእኛ ቤት ሁሉ ከእግዚአብሔር ቃል ነው🙏

በመጀመሪያ ጥምቀት የኢየሱስ ክርስቶስ ትዕዛዝ መሆኑን እውቁ ኢየሱስ ክርስቶስ ያዘዘውን ትዕዛዝ ወደ ጎን ትቶ ኢየሱስን እወዳለሁ ማለት አይቻልም።

የእርሱ አዳኝነት ሁላችንም የምናውቀው እና የምናምነው ሆኖ ሳለ እርሱ ራሱ በየዘመናቱ ሰው ልጆችን ለማዳን ትዕዛዝ ይሰጣል።

ለምሳሌ በ ጥፋት ውኃ ግዜ መርከብ እንድሰራ ኖኄን አዘዘ ለምን መርከቡን ሳይሠራ አላዳነም? መርከብ ሰርቶ በመርከቡም የሚያድነው ራሱ እግዚአብሔር ነው።

ኖኄም እግዚአብሔር የጥፋት ውኃ እንዲያመጣ ተናግሯል እኔም አምኛለሁ ያድናል በማለት ቁጭ አላለም ከራሱ የሚጠበቀውን እያደረገ መርከቡን እየሠራ ነው የጠበቀው እግዚአብሔርም አዳነ።

በአድስ ክዳን በጥምቀት አሮጌውን ማንነት በክርስቶስ ተቀየረ መነሳቱ ለአንተ/ች መቼ ጎዳ እና የኢየሱስን ትዕዛዝን ትንቃለህ
ይህኮ ለአሕዛብ ያልተሰጠ ዕድል ነበረ ነገር ግን የወደደን ለአድስ ልደት በሚሆን በመታጠብ ያዳነ ኢየሱስ ይመሰገን።

እንደ ምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን እንጂ፥ እኛ ስላደረግነው በጽድቅ ስለ ነበረው ሥራ አይደለም።
ቲቶ 3:5

አብዛኞቹ ይህን ላለመቀበል ኢየሱስ ያድናል እንጂ ጥምቀት አይድንም ይላሉ ኢየሱስ አንተን በ አድስ ልደት በሚሆነው በመታጠብ ዳግመኛ ተወልድ ክርስቶስን ልበስ ይላል አለበለዚያ መዳን አታገኘውም ይላል።

የተኛው ሐዋርያ ወይም ነቢይ በመጽሐፍ ቅዱስ አድስ ኢየሱስ ክርስቶስን ያላመነ ሰው አግኝቶ እጅ አንሳ እና መዳን አገኝታል ያለው የለም።

👉 ያመነ ሁሉ ወደ ጥምቀት እንጂ እጅ አላነሳም

ጥምቀት የመዳን አሠራር እንደሆነ

👉 ይህም ውኃ ደግሞ ማለት ጥምቅት ምሳሌው ሆኖ አሁን ያድነናል፥ የሰውነትን እድፍ ማስወገድ አይደለም፥ ለእግዚአብሔር የበጎ ሕሊና ልመና ነው እንጂ፥ ይህም በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ነው፤
1ኛ ጴጥሮስ 3:21

ጥምቀት ክርስቶስን ሞትና ትንሳኤ ማጋራት ነው።

👉 እንግዲህ ምን እንላለን? ጸጋ እንዲበዛ በኃጢአት ጸንተን እንኑርን?: አይደለም። ለኃጢአት የሞትን እኛ ወደ ፊት እንዴት አድርገን በእርሱ እንኖራለን? ወይስ ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ የተጠመቅን ሁላችን ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ እንደ ተጠመቅን አታውቁምን?
ሮሜ 6:1_3

የእግዚአብሔር ቃል መስክሮ ያመነ ሰውን ሁሉ ወደ ጥምቀት ይወስዳሉ እንጂ እጅ አንሳ አላሉም በእኛ ቤት ሁሉ ከእግዚአብሔር ቃል ነው። አሜን 🙏

ከታች ያለውን የ Telegram channel join አድርጉ በየቀኑ single መዝሙሮች በኮንፈረንስ የተሰበኩ ስብከቶች እና የፅሁፍ ትምህርት ይለቀቃል
join አድርጉ
👉https://t.me/ApostolicchurchofAreka
👉https://t.me/ApostolicchurchofAreka

01/03/2026

ሰላም ለቅዱሳን በሙሉ!

የኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ኦዲዮቪዥዋልና ስነ-ጽሑፍ ክፍል በዘማሪት ኢየሩሳሌም መዝገቡ የተዘጋጀውንና “እንደገና ታነሳለህ” የተሰኘውን የዝማሬ ሰንዱቅ ሲያቀርብላችሁ በታላቅ ደስታ ነው።

የበጎ ስጦታ ፍጹምም በረከት ባለቤት የሆነው እግዚአብሔር በቤተክርስቲያን በኩል ለራሱ ክብር እና ለቅዱሳን መታነጽ በሚሆኑ የዝማሬ ስጦታ እየባረከ ስላለ እናመሰግነዋለን። ዝማሬዎቹንም በታላቅ መስዋእትነት የሚያዘጋጁትንም ቅዱሳን እንባርካለን።

በዚህ አድካሚ የዝማሬ አልበም መዝሙሮቹን በመቀበል በስጦታ ለቤተክርስቲያን ያበረከተችውን እህት ኢየሩሳሌምን ጨምሮ በተለያየ መንገድ የተሳተፉትን ሁሉ የቤተክርስቲያን አምላክ ኢየሱስ በማያልቀው በረከት እንዲባርክ ጸሎታችንም ምኞታችንም ነው።

አልበሙ በቅርብ ቀናት ውስጥ በApostolic Songs መተግበሪያ ላይ ዝግጁ የሚሆን ሲሆን ቅዱሳን ሁሉ ዝማሬዎቹን በተለያዩ የግዢ አማራጮች በማውረድ ጸጋውን፣ ቤተክርስቲያንን እና አገልግሎቱን ትደግፉ ዘንድ በኢየሱስ ፍቅር እናስታውሳለን።

የኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን
ኦዲዮቪዥዋልና ስነ-ጽሑፍ ክፍል
የካቲት 2018 ዓ.ም

ከታች ያለውን የ Telegram channel join አድርጉ በየቀኑ single መዝሙሮች በኮንፈረንስ የተሰበኩ ስብከቶች እና የፅሁፍ ትምህርት ይለቀቃል
join አድርጉ
👉https://t.me/ApostolicchurchofAreka
👉https://t.me/ApostolicchurchofAreka

Want your place of worship to be the top-listed Place Of Worship in Sodo?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address


Areka
S**o
AREKA