Soddo Christian Hospital

Soddo Christian Hospital

Share

19/05/2026

ማስታወቂያ
ቀን፡ 11-09-2018
የሶዶ ክርስቲያን ሆስፒታል ኃላ.የተ.የግ.ማህበር የጠቅላላ ሐኪም ባለሙያዎችን አወዳድሮ ለመቅጠር ባለው ፍላጎት በቁጥር SCH-586-10-18 በቀን 30-8-2018 ዓ.ም ባወጣው ማስታወቂያ መሠረት የተመዝገባችሁና ፈተና የተፈተናችሁ-

ጠቅላላ ድምር 75 እና ከዚያ በላይ ያመጣችሁ ተወዳዳሪዎች ያለፋችሁ ስለሆነ በቀን 13/09/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ወደ ሆስፒታሉ ቅጥር ግቢ አስተዳደር ቢሮ ቀርባችሁ የቅጥር ፎርማሊቲ እንድታሟሉና ስትመጡ ከ8ኛ ክፍል ጀምሮ ያሉትን የትምህርት ማስረጃ original እና softcopy ይዛችሁ እንድትቀርቡ ማስፈለጉን ጭምር እንገልፃለን፡፡

ሁሌም ለላቀ የሕክምና አገልግሎት እንተጋለን!
ሶዶ ክርስቲያን አጠቃላይ ሆስፒታል
አድራሻችን፦ ወ/ሶዶ ከጉታራ በስተጀርባ እንገኛለን
ለበለጠ መረጃ: 0465511164 ይደውሉ
ጤና ነክ የሆኑ መረጃዎችን በየጊዜው ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይከታተሉ
https://t.me/soddochristiangeneralhospital
በጤና ይቆዩ !

08/05/2026

ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ፤

የሶዶ ክርስቲያን አጠቃላይ ሆስፒታል ኃላ/የተ/ግ/ማ ባለው ክፍት የሥራ ቦታ ጠቅላላ ሐኪም (General Practitioner) አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል፤

ብዛት = 03
ፆታ = ወንድ/ሴት
የሥራ ቦታ = ሶዶ ክርስቲያን አጠቃላይ ሆስፒታል ቅጥር ግቢ

መስፈርት፤

1ኛ/ ከታወቀ ዩኒቨርስቲ ወይም ኮሌጅ በጠቅላላ ሐኪምነት (General Practitioner) ሙያ ሠልጥኖ/ና ስለመመረቃቸው የሰለጠኑበት ዩኒቨርሲቲ/ኮሌጅ ዲግሪና ትራንስክርፕት ኮፒ ያለው/ያላት፤
2ኛ/ የሥራ ልምድ 0 ዓመትና ከዚያ በላይ ያለው/ያላት፤
3ኛ/ እንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታ ያለው/ያላት፤
4ኛ/ ጊዜው ያላለፈ የሙያ ፈቃድ ምዝገባ ማስረጃ ኮፒ የሚያቀርብ/የምታቀርብ፣
5ኛ/ የመግቢያ የቃለ መጠይቅ ፈተና ላይ የሚቀርብ/የምትቀርብ፡፡
6ኛ/ ሆስፒታሉ በሥራው አስገዳጅነት የሚያወጣውን የሥራ ፕሮግራም ተቀብሎ ለመሥራት ፈቃደኛ የሚሆን/የምትሆን፤
7ኛ/ በእነዚህ መስፈርቶች መሠረት በወጣው ማስታወቂያ ተወዳድሮ ለመቀጠርየሚፈልግ ማመልከቻና በማመልከቻቸው ላይ ስለራሱ/ሷ ምስክርነት ሊሰጡ የሚችሉ 3 ሰዎች ስም ዝርዝር ስልክ፡- (ሞባይል/መደበኛ) ጋር ጠቅሶ/ጠቅሳ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ07 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ወደ ሆስፒታሉ መዝገብ ቤት ድረስ ቀርቦ/ባ መመዝገብ የሚችል/የምትችል መሆኑን እናስታውቃለን፡፡
8ኛ/ ደመወዝ በሆስፒታሉ ስኬል መሠረት ይሆናል፤

ማሳሰቢያ፡-
የሥራ ልምድ ያላቸው በፈተና ሲያልፉ ከሚሠሩበት መ/ቤት መልቀቂያ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡

ሁሌም ለላቀ የሕክምና አገልግሎት እንተጋለን!
ሶዶ ክርስቲያን አጠቃላይ ሆስፒታል
አድራሻችን፦ ወ/ሶዶ ከጉታራ በስተጀርባ እንገኛለን
ለበለጠ መረጃ: 0465511164 ይደውሉ
ጤና ነክ የሆኑ መረጃዎችን በየጊዜው ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይከታተሉ
https://t.me/soddochristiangeneralhospital
በጤና ይቆዩ

Photos from Soddo Christian Hospital's post 16/04/2026

ከሁለት ሺህ አንድ መቶ ዘጠና አምስት (2,195) በላይ ሕጻናትን ከትበናል!

በሆስፒታላችን የሕጻናት ክትባት መርሃ-ግብር የተጀመረበትን ጊዜ በማስመልከት ዛሬ 08/08/2018ዓ.ም አንደኛ ዓመት ምስረታ አክብረናል።

ይህንን መርሃ-ግብር በሆስፒታላችን ለማስጀመር ላለፉት አስር ዓመታት ያክል ብዙ ጥረቶች ሲደረጉ የቆየ ሲሆን ካለፈው አንድ ዓመት ጀምሮ በተሳካ ሁኔታ ለሕጻናት ክትባቶችን ስንሰጥ ቆይተናል። ይህን ማድረጋችን የምንሰጠውን የላቀ የሕክምና አገልግሎት አንድ እርምጃ ወደፊት የሚያስኬድ ሲሆን የክትባት መርሃ-ግብሩ እዚሁ እንዲጀመር የተለያዩ ቁሳቁሶችን በማበርከት የበኩላቸውን ኃላፊነት የተወጡትን የመንግሥት ባላድርሻ አካላት በተለይም የዞኑ ጤና መምሪያ እና የሶዶ ከተማ ክትባት ክፍል አስተባባሪዎች፣ የሆስፒታሉ ማኔጅመንት እንዲሁም ዶ/ር ሚሼል ዬትስ እና አቶ በቃሉ ቶማስ ያላሰለሰ ጥረት በማድረጋቸው ይህ ሥራ በሆስፒታላችን እውን መሆን ችሏል።

ይህ በመሆኑ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ከሁለት ሺህ አንድ መቶ ዘጠና አምስት (2,195) በላይ ሕጻናትን ከዜሮ እስከ ዘጠኝ ወር ድረስ የሚሰጡ ክትባቶችን በተሳካ ሁኔታ መከተብ ችለናል።

ሁሌም ለላቀ የሕክምና አገልግሎት እንተጋለን!
ሶዶ ክርስቲያን አጠቃላይ ሆስፒታል
አድራሻችን፦ ወ/ሶዶ ከጉታራ በስተጀርባ እንገኛለን
ለበለጠ መረጃ: 0465511164 ይደውሉ
ጤና ነክ የሆኑ መረጃዎችን በየጊዜው ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይከታተሉ
https://t.me/soddochristiangeneralhospital
በጤና ይቆዩ

14/04/2026

ተሻሽሎ የወጣ ማስታወቂያ

ቀን፡ 05/08/2018 ዓ.ም
የሶዶ ክርስቲያን ሆስፒታል ኃላ.የተ.የግ.ማህበር የጥበቃ ሠራተኞችን አወዳድሮ ለመቅጠር ባለው ፍላጎት በቁጥር SCH-16/265/18 በቀን 10/07/2018 ዓ.ም እና በቁጥር SCH-187-10-18 በቀን 2/7/2018 ዓ.ም ባወጣው ማስታወቂያ መሠረት ቀርባችሁ የተመዘገባችሁና የጽሑፍ ፈተና ተፈተናችሁ 27.5 ከዚያ በላይያመጣችሁ ለቃለ-መጠይቅ ፈተና እንድትቀርቡ በሚል ማስታወቂያ ያወጣን ቢሆንም ማሻሻያ እንዲደረግ ስለተወሰነ ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሠረት ማሻሻያ ተደርጎ ማለትም፡-

የጽሑፍ ፈተና ውጤት 24.5 እና ከዚያ በላይ ያመጣችሁ ተወዳዳሪዎች በቀን 08/08/2018 ዓ.ም ከጧቱ 3፡00 ሰዓት ላይ ለቃለ-መጠይቅ ፈተና ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያና ቀደም ሲል ያቀረባችሁትን ዶክሜንት original copy በመያዝ ወደ ሆስፒታሉ አስተዳደር ሕንፃ እንድትቀርቡ ማስፈለጉን እያስታወቅን መታወቂያ ሳይዝ የሚቀርብ ተወዳዳሪ ለፈተና መቅረብ የማይችል መሆኑን ጭምር በጥብቅ እናስታውቃለን፡፡

ሁሌም ለላቀ የሕክምና አገልግሎት እንተጋለን!
ሶዶ ክርስቲያን አጠቃላይ ሆስፒታል
አድራሻችን፦ ወ/ሶዶ ከጉታራ በስተጀርባ እንገኛለን
ለበለጠ መረጃ: 0465511164 ይደውሉ
ጤና ነክ የሆኑ መረጃዎችን በየጊዜው ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይከታተሉ
https://t.me/soddochristiangeneralhospital
በጤና ይቆዩ!

13/04/2026

ማስታወቂያ
ቀን፡ 05/8/2018 ዓ.ም
የሶዶ ክርስቲያን ሆስፒታል ኃላ.የተ.የግ.ማህበር የጥበቃ ሠራተኞችን አወዳድሮ ለመቅጠርባለው ፍላጎት በቁጥር SCH-16/265/18 በቀን 10/07/2018 ዓ.ም እና በቁጥር SCH-187-10-18 በቀን 2-7-2018 ዓ.ም ባወጣው ማስታወቂያ መሠረት ቀርባችሁ የተመዘገባችሁና የጽሑፍ ፈተና የተፈተናችሁ፡-

የጽሑፍ ፈተና ውጤት 27.5 እና ከዚያ በላይ ያመጣችሁ ተወዳዳሪዎች በቀን 08/08/2018 ዓ.ም ከጧቱ 3፡00 ሰዓት ላይ ለቃለ-መጠይቅ ፈተና ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያና ቀደም ሲል ያቀረባችሁትን ዶክሜንት original copy በመያዝ ወደ ሆስፒታሉ አስተዳደር ሕንፃ እንድትቀርቡ ማስፈለጉን እያስታወቅን መታወቂያ ሳይዝ የሚቀርብ ተወዳዳሪ ለፈተና መቅረብ የማይችል መሆኑን ጭምር በጥብቅ እናስታውቃለን፡፡

ሁሌም ለላቀ የሕክምና አገልግሎት እንተጋለን!
ሶዶ ክርስቲያን አጠቃላይ ሆስፒታል
አድራሻችን፦ ወ/ሶዶ ከጉታራ በስተጀርባ እንገኛለን
ለበለጠ መረጃ: 0465511164 ይደውሉ
ጤና ነክ የሆኑ መረጃዎችን በየጊዜው ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይከታተሉ
https://t.me/soddochristiangeneralhospital
በጤና ይቆዩ

Want your organization to be the top-listed Non Profit Organization in Sodo?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Address


Christian Hospital Street
Sodo