Dr Timothy

Dr  Timothy

Share

11/04/2026

🚨 ሰበር እና ልብ ሰባሪ | የሞራል ኪሳራችን ማሳያ፡ ለ35 ዓመታት ሀገር ያገለገሉት አንጋፋ ባለሙያ በአደባባይ ተደበደቡ!
ይህ የአሁኑ ትውልድ ምን ያህል የሞራል፣ የስነምግባር እና የግብረገብነት ክሳራ ውስጥ እንደገባ የሚያሳይ እጅግ አሳዛኝ እና ፀያፍ ድርጊት ተፈፅሟል። የዚህ ልብ ሰባሪ ክስተት ሰለባ የሆኑት አቶ ዋቆ ከዲር የተባሉ አንጋፋ የጤና ባለሙያ ናቸው። እኚህ የዕድሜ ባለፀጋ አገልግሎታቸውን በክብር አጠናቀው የጡረታ መብታቸውን ለማስከበር ሰነዶቻቸውን በማደራጀት ላይ እያሉ፣ በባሌ ሮቤ ከተማ መናኸሪያ ውስጥ ማንነታቸው ባልታወቁ ወጣቶች አሰቃቂ ድብደባ ተፈፅሞባቸዋል።
አቶ ዋቆ ከዲር ለ35 ተከታታይ ዓመታት በቄለም ወለጋ ሆስፒታል፣ በጎባ ሆስፒታል፣ በጊኒር ሆስፒታል እና በራይቱ ጤና ጣቢያ ህዝባቸውን ሲያገለግሉ የቆዩ ውድ የሀገር ባለውለታ ናቸው። ህይወት አድነው፣ በሽተኛ አስታመው እና ሀገርን በታማኝነት አገልግለው ለጡረታ ሲበቁ፤ የህይወት ዘመን ድካማቸው ሽልማት በአደባባይ መደብደብ እና መዋረድ መሆኑ የደረስንበትን የህሊና መሞት ፍንትው አድርጎ ያሳያል።
ይህንን ዘግናኝ ድርጊት የፈፀሙት ወጣቶች ከሌላ ፕላኔት የመጡ ሳይሆኑ፣ የዚሁ ማህበረሰብ እና ስርዓት ውጤቶች ናቸው። ህግ በማይከበርበት ማህበረሰብ ውስጥ ህግ የማያከብር ትውልድ መፈጠሩ የፀሀይ ብርሃን ያህል ግልፅ ነው። የሞራልና የስነምግባር ተቋማት የራሳቸውን ኃላፊነት መወጣት ሲያቅታቸው፤ ጨካኝ፣ ለማንም የማይገደው፣ እጅግ ራስ ወዳድ እና የሞራል ስብእና የጎደለው አመፀኛ ትውልድ መፈጠሩ የማይቀር እውነት ነው።
ለዚህ አሳሳቢ የትውልድ ውድቀት ደግሞ ቤተሰብ፣ ጎረቤት፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ የፖለቲካ መሪዎች እና የሃይማኖት አባቶች በሙሉ ተጠያቂዎች ናቸው። በጥቂት መልካም ሰዎች ብንፅናናም፣ ከአገር ጫፍ እስከ ጫፍ እየታየ እና እየተሰማ ያለው የሞራል ስብራት ግን ሀገርን ወደ ባሰ አዘቅት ከመክተቱ በፊት ሁላችንንም ሊያነቃን ይገባል።

Photos from Dr  Timothy's post 27/06/2025

አስደሳች ዜና ለሥራ ፈላጊዎች በሙሉ!!!

አርባምንጭ ሰኔ 20/2017 ዓ.ም (የአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት)

የጉምሩክ ኮሚሽን በአዲስ መልክ ከተደራጀ በኋላ ተቋማዊ አቅምን ከመገንባት፣ አገልግሎት አሰጣጥን ከማሳለጥ፣ የህግ ተገዥነትን ከማረጋገጥ እና ገቢን በብቃት ከመሰብሰብ አንጻር አበረታች ድሎችና ዉጤቶች እያስመዘገበ ይገኛል፡፡

ስለሆነም ኮሚሽኑ የተጣለበትን ከፍተኛ ኃላፊነት በብቃት ለመወጣት እንዲያስችለው በቅርቡ ሰርቶ ባጠናቀቀው ተቋማዊ አደረጃጀት ማሻሻያ ላይ ብቃት ያለው የሰው ሀይል ለማሟላት በተሰጠው ኮታ መሠረት ከክልሎች መልምሎ ለመቅጠር ዝግጅቱን አጠናቋል።

በዚህ መሠረት በኮሚሽኑ ስር በሚገኙ በማናቸውም ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ወይም መቅረጫ ወይም መቆጣጠሪያ ጣቢዎችና በየትኛውም ዓይነት የአየር ፀባይ ውስጥ 24 ሰዓት 7 ቀን (24/7) ለማገልገል ፍቃደኛ የሆነች፣

በ2014፣ 2015፣ 2016 እና 2017 የትምህርት ዘመን ከመንግስት ዩኒቨርሲቲ ወይም ህጋዊ ዕዉቅና ካላቸዉ ከግል ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቀ/ች፣

በኮሚሽኑ የሚሰጠውን መግቢያ ፈተና ማለፍ የሚችል/የሚትችል፣ በኮሚሽኑ የሚሰጡ ስልጠና መውሰድ የሚችል/የሚትችል ከዚህ በታች በተቀመጠው ዝርዝር መስፈርቶች መሠረት መመዝገብ ትችላላችሁ።

ማሳሰቢያ፦ ተመዝጋቢዎች ስመጡ የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ቀበሌ ነዋሪ ስለመሆናቸው የምገልጽ ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ መያዝ ያለባቸው ሲሆን፣ ምዝገባው ከዛሬ ጀምሮ 3 ተከታታይ የሥራ ቀናት በወረዳው አስተዳደር ጽ/ቤት መሆኑን እንገልፃለን።

Photos from Dr  Timothy's post 26/06/2025

External Vacancy annocment from Addis Ababa City of Revenue office.
[በዜሮ አመት እና በልምድ]- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ

Deadline: July 3, 2025

Photos from Dr  Timothy's post 02/06/2025

ዘማሪት የምስራች ጨጓራዋ አከባቢ ከነበረው 4ኛ ደረጃ ካንሰር ተፈውሳ ነበር፣ ከጊዜያት በኋላ ቼካፕ ስታደርግ ጀርባዋ አከባቢ ሶስተኛው አጥንት ላይ እና ሳንባዋ ላይ ካንሰር ተገኝቶባት ከባድ ሳል ታክሎበት ፅኑ ሕሙማን ክፍል እንድትገባ ተደርጎ ነበር ዛሬ የተሰማው ዘማሪት የምስራች ህይወቷ ማለፉ ነው።

ለመላው ቤተሰቦቿ ወዳጆቿ መጽናናትን እንመኛለን።

Want your practice to be the top-listed Clinic in Sodo?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Website

Address


Wolaita S**o
S**o