Job seeker

Job seeker

Share

07/08/2022

#የ4ተኛው ቅዱስ ፓትርያርክ ሥርዓተ ቀብር ዕለት የተጻፈ
---------------------------------------------------

በእግዚአብሔር ቸርነት፤ማንም ሊመረምረው በማይቻል መንገድ እራሱ መንፈስ ቅዱስ ባሰማራቸው ሠራተኞች የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን ዳግም አንድ አድርጏታል። ይህ ይሆን ዘንድ መንፈስ ቅዱስ መሳርያው አድርጎ የተጠቀመባቸው ደግሞ እነ ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት አይነቱን ነው።ማንም ሰው አጀንዳ ብሎ በማያነሳው ወቅት ቤተ ክርስቲያን ተከፍላ እኛ ዝም ብለን መኖራችን አደጋ እንደሆነ ትውልዱን ከቀሰቀሱት ካነቁት ሐዋርያ አንዱ የመጀመሪያው እርሱ ነው። አንድ ሁሌም የማልረሳው፤ በውስጤ የሚያቃጭልብኝ ነገር፤ ቤተ ክርስቲያን በምን ምክንያት እንደተከፈለችና ወደፊትስ እንዴት አንድ መሆን እንዳለባት ሲያስተምረን፤ የማልረሳው ስለ ቅዱስ ፓትርያርኩ ሲያነሳ "በረከታቸው ይደርብንና፤ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ" ብሎ ልዩ ቃና ባለው አክብሮት ነበር የሚያነሣቸው። ስማቸውን አጠራሩ ብቻ ብዙ ጥልቅ ነገር እንድናስተውል ያደርገን ነበር። ፖለቲካውን ከሃይማኖት ለይተን እንድንረዳ ያደርገን ነበር። የቱኛው ተሀድሶ ምንፍቅና ያመጣው የትኛው ፖለቲካ ያመጣው ተግዳሮት እንደሆነ በጥናት አስደግፎ ያሰለጥነን ነበር ያስተምር ነበር። "ሲኖዶስ አትሰደድም" ብሎ አቋም መያዝ የቅዱስ አባታችንን በግፍ መሰደድ፤ የቅዱስ አባታችን ተጋድሎ መዘንጋት እንዳልሆነ ስማቸውን በተለየ ክብር ሲጠራቸው ብቻ ብዙ እንማርበትም ነበር። ከምንም በላይ በቤተ ክርስቲያን አንድነት ላይ የእኔ ብለን እንድንሠራ ያሠለጥነን ነበር። "ጸልዩ በእንተ ሰላም ቤተ ክርስቲያን አሐቲ ቅድስት ጉባዔ እንተ ሐዋርያት ርትዕት በኀበ እግዚአብሔር፤ የሐዋርያት ጉባዔ ስለሆነች፤ በእግዚአብሔር ዘንድ ስለቀናች ፤ ስለ አንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰላም ጸልዩ" የሚለውን የቅዳሴ ፀሎታችንን በየትምህርት ርዕሱ እያስገባ ያስታውሰን ነበር። ሙሐዘ ጥበባት ካለው ልዩ ስጦታዎች አንዱ፤ ወንጌልን ሲያስተምር ከወቅቱ የቤተ ክርስቲያን ፈተና ጋር አሰናስሎ የተኛው እንዲነቃ ያላወቀው እንዲረዳ አድርጎ ተጽዕኖ የሚያመጣ ንቅናቄ የመፍጠር ጸጋ አለው። ስብከቶቹ የሚያነቁ ብቻ ሳይሆን፤ አንቅቶ ወደ መንፈሳዊ ሥራዎች የሚያዘምቱ ነበሩ። በዚህ ትምህርቶቹ ከአንዳንድ አቢያተ ክርስቲያናት ሳይቅር የተባረረበት ጊዜ ነበር፤ አይምጣብን የተባለበት ከተሞች ነበሩ። እርሱ በረገጠባቸው ከተሞች ሁሉ ግን ሥራ ይሠራ ነበር። ለ አንድ ሰዓት የተሰጠች ስብከቱ ዓመት ሙሉ ያነጋግር ነበር፤ ለ45 ደቂቃ ያቀረበው ጥናታዊ ጽሁፍ ለሚቀጥሉት አምስት፤አሥርት ዓመታት
ተጽዕኖ ይፈጥሩ ነበር። ለምሳሌ ከስብከቶቹና ጥናታዊ ጽሁፎቹ አንዳንዱን ለመጥቀስ ያህል፤

+ለጥፋት የታዘዘች ከተማ ነጋሪት ቢጎሰም አትሰማ
+አንድ ሆነን ችግሩን እንፍታ ወይስ ችግሩ ሲፈታ አንድ እንሁን
+ ምንም እንኳ
+ የምትሄድበት መንገድ እሩቅ ነውና ተነሥተህ ብላ

እነዚህ በጥቂቱ በቤተ ክርስቲያን አንድነት ዙሪያና በወቅቱ ፈተናዎች የተሰጡ ትምህርቶችና ጥናታዊ ጽሑፎች ናቸው። እነዚህ በጉባዔ መልክ የተሠጡ እንጂ፤ ሦስት ሰዎችም ይኑሩ አምስትም ሰዎች፤ ምክሮቹም ተግሳጾቹም፤ ውይይቶቹም በእናት ቤተ ክርስቲያን ዙሪያ ነበሩ። ዛሬ ላይ ሆኜ ሳስበው ይህች ቀን እንደምትመጣ ቅዱስ አባታችን ሳይሞቱ በፊት በክብር ወደ መንበራቸወ እደሚመለሡ ተገልጦለት ነበር ወይ ያስብለኛል።

ዛሬ ላይ ሆኜ ሳስበው የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ ይደንቀኛል። ሙሐዘ ጥበባት ለዚህም ነው ጸሎቱን፤ ትጋቱን፤ አገልግሎቱን መድኃኔዓለም ቆጥሮለት፤ የአንድነት አጀንዳ

21/02/2021

05/12/2020

ኢትዮጵያዊቷ ዶ/ር ውለታ ለማ ዓለም አቀፉን የቴክኖሎጂ የስራ ፈጠራ ውድድር አሸነፉ!

የላሊበላ ግሎባል ኔትወርክስ ድርጅት ተባባሪ መስራችና ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ኢትዮጵያዊቷ ውለታ ለማ (ዶ/ር) ዓለም አቀፉን ቴክኖሎጂን መሠረት ያደረገ አዲስ የስራ ፈጣራ ውድድር አሸነፉ። ኢትዮጵያዊቷ በየዓመቱ የሚካሄደውን ዓለም አቀፉን ፒአይቲሲኤች (PITCH) አዲስ የስራ ፈጠራ ውድድር በትላንትናው እለት ማሸነፉቸው ይፋ ሆኗል።

በውድድሩ 2500 ስራ ፈጣሪዎች የተሳተፉ ሲሆን ወደ መጨረሻው ዙር ያለፉት ደግሞ 700 የሚሆኑ አዲስ ፈጣሪዎች ነበሩ።ከዚህ ውስጥ ኢትዮጵያዊቷ ውለታ ለማ(ዶ/ር) በጤና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ያቀረቡት አዲስ የስራ ፈጠራ በቅርበት ተፎካካሪ ከነበሩት የአሜሪካና የእንግሊዝ የስራ ፈጣሪዎችን በመብለጥ የዓመቱ ውድድር አሸናፊ ሆኗል።

ውለታ ለማ (ዶ/ር) ለውድድሩ ያቀረቡት የስራ ፈጠራ አባይ ሲ ኤች አር (ABAY CHR) የተባለ በኢትዮጵያም ሆነ በአፍሪካ ህክምና ዘርፍ ያለውን ሰፊ የወረቀት ስራ ወደ ዲጂታል በመቀየር ስራን የሚያቀልና የሚያቀላጥፍ እንዲሁም ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ወጪን የሚያስቀር የሥራ ፈጠራ ነው ተብሏል። "የአፍሪካን የጤና ዘርፍ ስርዓት ለማዘመን ለ28 ዓመታት ሰርቻለሁ ፤ እናም ውድድሩን በማሸነፌ በጣም ተደስቻለሁ" ሲሉ ውለታ ለማ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

Want your business to be the top-listed Media Company in Sodo?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Website

Address


S**o
385037