Christ message

Christ message

Share

22/05/2024

የፍርድ ምርመራው ሥራ በሚጠናቀቅበት ጊዜ የሁሉም ሰው መዳረሻ ለሞት ይሆን ለሕይወት የሚወሰን ይሆናል። በሰማይ ደመና ጌታ ከመገለጡ ከጥቂት ጊዜ በፊት የምሕረት ጊዜ ያበቃል። በራዕይ፣ ክርስቶስ ወደዚያ ጊዜ እየተመለከተ ሲናገር፦ "አመፀኛው ወደፊት ያምጽ፣ እርኩሱም ወደ ፊት ይርከስ፣ ፃድቁም ወደ ፊት ጽድቅ ያድርግ፣ ቅዱሱም ወደ ፊት ይቀደስ አለ። እነሆ እመጣለሁ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ።" [ራዕይ 22÷11፣12] ይላል።
ሰዎች፣ እያተከሉ፣ እያነፁ፣ እየበሉና እየጠጡ፣ የመጨረሻው፣ የማይቀለበሰው ውሳኔ በላይ በመቅደሱ እንደታወጀ ሳያስተውሉ፣ ፃድቃንም ኃጢአተኞችም በሟች ሁኔታቸው ሆነው በዚያን ጊዜም በምድር ላይ ይኖራሉ። ከጥፋት ውኃ በፊት፣ ኖህ ወደ መርከቡ ከገባ በኋላ እግዚአብሔር በውስጥ ዘጋበት፤ ከሃዲዎችም በውጪ ቀሩ፤ ሆኖም ጥፋታቸው እንደተወሰነባቸው ሳያውቁ፣ ልቅ፣ የደስታ- ፍቅር ያለበትን ሕይወታቸውን ለሰባት ቀናት ቀጠሉበት፤ ሊመጣ ያለውን የፍርድ ማስጠንቀቂያ ተሳለቁበት። አዳኙ ሲናገር፣ "የሰው ልጅ መምጣት ደግሞ እንዲሁ ይሆናል" አለ [ማቴ 24÷39]። ኮሽ ሳያደርግ፣ እንደ ውድቅት ሌባ ሳይስተዋል፣ የእያንዳንዱ ሰው መዳረሻ እንደተወሰነ ለኃጢአተኞችም የተዘረጋው ምሕረት እንደተወሰደ የሚያመለክተው ወሳኝ ሰዓት ይመጣል።
"….ድንገት መጥቶ ተኝታችሁ እንዳያገኛችሁ ስለዚህ ትጉ" [ማር 13÷ 35፣36]። መጠበቃቸው አዝሏቸው ወደ ዓለም መስዕቦች የሚዞሩ ሰዎች ሁኔታ እጅግ አደገኛ ነው። ነጋዴው ትርፍ ለማግኘት ተወስውሶ ሳለ፣ ደስታ (ፈንጠዝያ) አፍቃሪው እርካታ ሲያሳድድ ሳለ፣ የፋሽን ሴት ልጅ መሽቀርቀሪያዋን እያበጃጀች ሳለች — የምድር ሁሉ ፈራጅ "በሚዛን ተመዘንህ ቀልለህም ተገኘህ" ብሎ የሚያውጀው በዚያች ሰዓት ሊሆን ይችላል [ዳን 5÷27]። GCAmh 355.4

Want your place of worship to be the top-listed Place Of Worship in Shakiso?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address


Shakiso