Kemal indiris
12/11/2025
ብልፅግና "በመስከረም ወር የመንግስት ሰራተኞችን ደሞዝ እንደሚጨምር" ለምን አሳወቀ? ምክንያቱም እየመጣ ያለውን የለውጥ ደመና ስለተገነዘበ ነው።
በመስከረም፦
- የህክምና ባለሙያዎች ለሁለተኛ ዙር ተቃውሞ እየተዘጋጁ ነው፣
- መምህራን ክረምቱን ሲደራጁ ቆይተው ለተቃውሞ ትምህርት ቤት እስኪከፈት እየተጠባበቁ ናቸው፣
- ገበሬው በማዳበሪያ ዋጋ ንረት ሳቢያ እርሻውን ማረስ ስላልቻለ፣ በቁጭት ሞፈሩ ላይ ተደግፎ መልካም አጋጣሚ እየጠበቀ ነው፣
- ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተመረቁ ተማሪዎች ልብሳቸው እላያቸው ላይ እየነተበ፣ በረሃብ አለንጋ እየተገረፉ፣ በየበረንዳው እያፋሸኩ ይገኛሉ፣
- በየተራራውና ቆላው የሚቃጠለው ወታደር፣ የደሞዝ ማነስ ሳያንሰው ስንቅ በማጣቱ በሽምቅ ታጣቂዎች በየቦታው እየተበተነ ነው።
በአጠቃላይ፣ እያዝገመገመ ያለውን ደመና ዘግይተው ሲረዱ "የደመወዝ ጭማሪ መቼም አይደረግም" የሚለውን አቋማቸውን ለመቀየር ተገደዋል። የደሞዝ ጭማሪው እየመጣ ያለውን ዶፍ ያስቆም ይሆን? አይመስልም። ጠዋት የጠፋውን አህያ ማታ ላይ ጥሪ አይመልሰውም። በጣም እሚንት፣ የዘገየ እርምጃ! (Too little too late!)
ለማስታወስ ያህል:- 50% ፣ 30% ፣ 20%
ህልሜ ጠፋ ተስፋዬም ጨለመ ወይስ እኔ ብቻ ሁለችንም ነን 2011ወደ 2017
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Metu