Raya Vision
07/06/2026
በቲቤት ሰማይ ላይ የታየው አስደናቂውና አስፈሪው የደመቀ ቀይ ብርሃን
ከሰማይ ወደ መሬት ሳይሆን ከመሬት ወደ ጠፈር የሚተኮሰው ያልተለመደው መብረቅ
ቲቤት በደቡብ ምዕራብ ቻይና የምትገኝ፣ ከኔፓል፣ ህንድ እና ቡታን ጋር የምትካለልና እጅግ ሰፊ በሆነው የኪንግሃይ-ቲቤት እምብርት ላይ ያለች ከፍተኛ ተራራማ ቀጠና ናት። በአማካይ ከባህር ጠለል በላይ ከ4,000 እስከ 5,000 ሜትር ከፍታ ላይ በመገኘቷ "የዓለም ጣሪያ" (Roof of the World) በሚል ስያሜ ትታወቃለች።
ይህ ልዩና እጅግ ከፍተኛ መልክዓ-ምድር አየሩ ቀጭን፣ ሰማዩ ደግሞ እጅግ ንጹህ እንዲሆን ስለሚያደርገው ከምድር በላይ የሚከሰቱ ብርቅዬ የጠፈርና የከባቢ አየር ክስተቶችን ለመመልከት በዓለም ላይ ካሉ ምርጥ ስፍራዎች አንዷ ያደርጋታል::
በዚሁ ልዩ ስፍራ በቅርቡ በቲቤት ሻናን ክልል በሚገኘውና ከባህር ጠለል በላይ ከ5,000 ሜትር በላይ ከፍታ ባለው ፑማ ዩምኮ ሐይቅ (Lake Puma Yumco) አቅራቢያ በተከሰተ ኃይለኛ የነጎድጓድ ማዕበል ላይ እጅግ አስደናቂ እና አስፈሪ የሆነ የበራ ቀይ የብርሃን ምሰሶ ብልጭታ በቪዲዮ ተቀርጾ ወጥቷል።
የሳይንስ ልብ-ወለድ ፊልም የሚመስለውና "ሬድ ስፕራይትስ" (Red Sprites) በመባል የሚታወቀው ይህ ክስተት፣ ልክ እንደ ግዙፍ የባህር እንስሳ ቅርፅ ያላቸው የብርሃን ዘንጎች ታይተዋል።
02/06/2026
#አላማጣ አዝናለች
በአባታችን በበርሄ ትኩየ ህልፈት የተሰማኝ ሃዘን ጥልቅ ነው። የታጣቂዎች እጅ ንጹሃን ዜጎችን መቅጠፉን ቀጥሏል፤ ይህ ድርጊት በእጅጉ ያሳዝናል። ለአባታችን ነፍስ እረፍትን፣ ለቤተሰብም ጥንካሬን እመኛለሁ!!
ኣላማጣ💔
01/06/2026
#ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Mekelle