Zeagelo Page
12/02/2026
ከ18 አመት በታች ያለች ህፃን ልጅ ላይ ወንጀል ፈፅሞ ያስወለደ፣ አስወልዶም የካደ ሰው በወንጀል ሊጠየቅ ሲገባ አባትነቱ ተረጋግጦ ህፃንዋን እንዲጎበኝ የሚወሰነው በምን ህግ ነው?
የወንጀል ህግ ቁ. 626 ዕድሜዋ ከ13 ዓመት በላይ ሆኖ ግን 18 ዓመት ካልሞላት ልጃገረድ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት የፈጸመ ማንኛውም ሰው በፈቃደኝነት ቢሆን እንኳ በወንጀል ይጠየቃል። ቅጣቱ እንደ ሁኔታው ከ 5 ዓመት እስከ 15 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት ያስቀጣል።
በዚህ አንቀጽ ስር "በፈቃደኝነት ነው የተገናኘነው" የሚል መከላከያ ተቀባይነት የለውም። ሕጉ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች ለዚህ ድርጊት ብቁ የሆነ "ፈቃድ" መስጠት አይችሉም ብሎ ስለሚያምን ድርጊቱ ሁልጊዜም ወንጀል ነው።
ተከሳሹ "ዕድሜዋ 18 የሞላ መስሎኝ ነበር" ወይም "ዕድሜዋን አላውቅም ነበር" “ጉልበት ተጠቅሜ አልደፈርኳትም” በሚል ተልካሻ ምክንያት ከቅጣት አያመልጥም።
የዋንቲያ የልጇ አባት ጭራሽ የልጅቷ አባት መሆኑን አምኖ ፍ/ቤ ክስ ከመሰረተ የወንጀል ክስ የይርጋ ጊዜው ገና በመሆኑ የሚመለከተው የፖሊስ አካል ግለሰቡን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ ሊጀመር ይገባል።
ከፈለገ በፍርድ ያገኘውን የመጎብኘት መብት ከማረሚያ ቤት ሊያስፈቅድ ይችላል። በነገራችን ላይ ለህፃኗም ቢሆን እናቷን አስገድዶ የደፈረ፣ ካለ እድሜዋ አስወልዶ የካደ፣ የሰው ፊት እንዲገርፋት ያደረገ አባት አይጠቅማትም። ድንጋይም ከአፈር ተጋብቶ ትል ይወልዳል። አባትነት ለእናትየው የመከራ በትር ከሆነ ህፃናቱም በደልንና ጭቆናን አሜን ብለው የሚቀበሉ ተሸናፊ ይሆናሉ እንጂ በርግጥ ከዚህ ሰው የአባት ፍቅርን አግኝተው ጎዶሎአቸውን አይሞሉም።
እስከዛሬ ክዶ የቆየ ሰው ዛሬ ህይወት ሲሳካላት እንደ እባብ እየዳኸ ሲመጣ ልታስቆመው የሚገባው ዋንትያ አልነበረችም። ህጉ ነበር። እሷ ባትፈልግ እንኳን የተፈፀመባት ድርጊት በሁሉም ሰው ላይ የተፈፀመ ወንጀል ነው።
የወንጀል ምርመራውም በጣም ቀላል ነው። የሷ እድሜ ሲቀነስ የህፃኗ እድሜ= የሰውየው አባት መሆን አለቀ።
Via ጠበቃ Mesi Bahiru
fans
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the public figure
Telephone
Website
Address
Jimma
Jimma
1983