Zola Mobile Accessory and Computer Maintenance
09/12/2017
ቅድመ ማስጠንቀቅያ for smart phone users
"""""""""""""""""""""""""""""
የጠፋብን ወይም የተሰረቀ ሞባይል በቀላሉ ማግኘት የምቻልበት መንገድ።
ሞባይላችን ከጠፋ ወይም ከተሰረቅን በኋላ ወደ ፖሊስ
ከመሀድ፥ እግራችን እና እጃችን ሰብስብን ከመቀመጥ፥ በሞባይላችን ያስቀመጥናቸው ኣስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች ከጥንቃቄ ጉድለት ጠፍቶብን ወኔ ከማለት የምያድነን ቀላሉ መንገድ።
የሆነ ሞባይል የተለየ የራሱ የሆነ IMEI ኣለው፡
ማለትም international mobile equipment Identity የሀንን ቁጥር በመጠቀም ሞባይላችን ያለበት ቦታ ማወቅ እንችላለን።
የምከተለው መንገድ መከተል እንችላለን።
1) * #06 # ይደውሉ
2)የሞባይላች የተለየ 15 ቁጥሮች ወይም ልዩ ኮድ IMEI
ያሳየናል።
3) የሀንን ቁጥር ማስታወሻችን ላይ ማስፈር ፡
ምክንያቱም የሀንን ቁጥር ሞባይላችን ከጠፋብን ወይም ከተሰረቅን የምንፈልግበት መንገድ ኣንዱ ዘዴ ነው ።
ሞባይላችን ከጠፋ ወይም ከተሰረቀ የሀንን ምስጥራዊ ኮድ
IMEI በ ኢሜል( e mail ) ወደ
[email protected] ከምከተለው ዝርዝር ጋር እንልካለን።
# Your name .......................
# Address .......
# Phone model ....
# Make ..........
# Last used number ,................
# E mail for comunication .........
# Missed date ....
#.IMEI number
# በ24 ሰዓታት ውስጥ በተራቀቀው GPRS system በመጠቀም ኣድራሻውን ማግኘት እንችላለን፡ ሞባይላችን ከማን እጅ ጋር እንዳለና ማን እየተጠቀመበት እንዳለ ፡ እየተጠቀመበት ያለው ግለሰብ ቁጥር በ email ይላካል ማለት ነው።
ወደ ሁሉም እንድደርስ share and like እናርግ እናካፍል።
21/08/2017
ስልክ ቻርጅ ሲደረግ መወሰድ ያለበት ጥንቃቄ
የሞባይል ስልክ ተጠቃሚዎች የመጀመሪያ ጭንቀት የሚሆነው የሚገለገሉበት ስልክ ባትሪ ጉዳይ ሳይሆን አይቀርም።
የሞባይል ባትሪ የአጠቃቀም ጉድለትን ጨምሮ በተለያዩ ምክንያቶች የታሰበውን አገልግሎት ላይሰጥ ይችላል።
በአግባቡ ቻርጅ አለማድረግን ጨምሮ የሚሰሩ ስህተቶች ለባትሪ እድሜ ማጠር ምክንያት ናቸው።
ባለሙያዎች ደግሞ የሞባይል ስልክ ቻርጅ ሲደረግ መደረግ ስላለበት ጥንቄ ያነሳሉ።
1) ለስልኩ በተዘጋጀ ቻርጀር ብቻ መጠቀም፦ ሁል ጊዜም ቢሆን ለስልኩ በተዘጋጀ እና በራሱ ቻርጀር ብቻ ቻርጅ ማድረግ የመጀመሪያው ጥንቃቄ ሊሆን ይገባል።
ይህን አለማድረጉ በባትሪው እድሜ ላይ አወንታዊ ተፅዕኖ ይፈጥራል፤ ባትሪው በጊዜ የመጎዳትና የመሞት ባህሪም ይኖረዋል።
ከዚህ ባለፈ ግን መንገድ ላይ በአጋጣሚ የሚያገኟቸውንና ከታወቀ አምራች ያልተመረቱ ቻርጀሮችን መጠቀም ቢያቆሙም ይመከራል።
እነዚህ ቻርጀሮች ከደህንነት ጋር በተያያዘ ምንም አይነት ዋስትና ያልተገባላቸው ሊሆኑ ስለሚችሉም በተቻለ መጠን አለመጠቀሙም ይመረጣል።
2) ለስልኩ መከላከያ የገጠሟቸውን ነገሮች ማስወገድ፦ ስልክ ቻርጅ ሲደረግ ቀስ እያለ መሞቁ የተለመደ ጉዳይ ነው።
ይሁን እንጅ ስልኩን ከአደጋ ለመከላከል በሚል የለጠፏቸው መከላከያዎችን ቻርጅ በሚያደርጉ ጊዜ አለመንቀል ባትሪው ከመጠን በላይ እንዲግልና በጊዜ አገልግሎት መስጠት እንዲያቆም ሊያደርገው ይችላል።
ስለዚህም በተቻለ መጠን ቻርጅ ሲያደርጉ እነዚህን መከላከያ ነገሮች ማስወገድ ይመከራል።
3) ፈጣን ቻርጀሮችን አይጠቀሙ፦ ምናልባት አንዳንድ ጊዜ ከመቸኮል የተነሳ ቶሎ ሃይል የሚሞሉ ፈጣን ቻርጀሮችን መጠቀምና እነሱኑ አማራጭ ማድረጉ አይመከርም።
ምክንያቱም እነዚህ ቻርጀሮች በፍጥነት ሃይል ስለሚለቁ ባትሪው ላይ ከፍተኛ መጠን ያለው የኤሌክትሪክ ፍሰት እንዲኖር በማድረግ ከልክ በላይ እንዲግል ያደርጉታል።
ይህም በባትሪው እድሜ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳድራል፤ ከልክ በላይ መጋሉ ባትሪውን የማቃጠል እድሉ ከፍተኛ ነው።
ምናልባት ይህን እያደረጉ ከሆነና ከልክ በላይ ከጋለ ሃይሉን አጥፍተው ስልኩ ወደቀደመበት የሙቀት መጠን እስከሚመለስ ድረስ ይጠብቁ።
4) ሌሊቱን ሙሉ ስልክዎን ቻርጅ አያድርጉ፦ ምናልባት ከቀን ውሎዎ ወደ ቤት ሲያመሩ ስልክዎ ቻርጅ ከሌለው እንዲሞላ በሚል ሌሊቱን ሙሉ ቻርጅ ሰክተው ማሳደር የለብዎትም።
ከልክ በላይ ቻርጅ ማድረጉ የስልኩን አጠቃላይ ደህንነት ይጎዳልና እንደዚያ አያድርጉ።
5) የባትሪ መተግበሪያዎችን ማጥፋት፦ ከኢንተርኔት አውርደው የሚጠቀሙባቸውን አንዳንድ “የባትሪ እድሜ ማራዘሚያ” መተግበሪያዎችን በዚህ ጊዜ መዝጋት ይመከራል።
መተግበሪያዎቹ የባትሪውን እድሜ ጥቂት ለማራዘም እዚህ ቦታ ላይ ይጫኑ በሚል ተደጋጋሚ ማስታወቂያዎችን ስክሪኑ ላይ ያመጣሉ።
ይህ ደግሞ የባትሪውን የአገልግሎት ጊዜ የማሳጠር እድሉ ከፍተኛ ነው።
ስልኩ ቻርጅ እያደረገና እየሞላ ቢሆንም እንኳን እነዚህ መተግበሪያዎች ሃይል መጠቀም ስለማያቆሙ ለባትሪው አላስፈላጊ ናቸው።
6) 100 ፐርሰንት እስከሚሆን ቻርጅ አለማድረግ፦ በተቻለ መጠን ስልክ ሙሉ በሙሉ ሙሉ እስከሚሞላ ድረስ ቻርጅ ማድረጉም አይመከርም።
ሁል ጊዜም ቢሆን ሙሉ በሙሉ 100 ፐርሰንት መሆን አለበት በማለት ቻርጅ ማድረጉ ባትሪው ረጅም እድሜ እንዳይቆይ ያደርገዋል።
7) በየጊዜው ቻርጅ አለማድረግ፦ በጣም በአጭር ጊዜ ልዩነት ቶሎ ቶሎ ቻርጅ ማድረጉ አይመከርም።
ቻርጅ ሲያደርጉ 80 በመቶ ከደረሰ በኋላም መንቀልና መጠቀም ይቻላል፥ ይህን ሲያደርጉ ባትሪው ቶሎ ቶሎ እንዳይጨርስ ይረዳዋል።
8) ቻርጅ እያደረጉ አለመጠቀም፦ በተቻለ መጠን ስልኩን ቻርጅ እያደረጉ መጠቀም የለብዎትም።
ይህን ሲያደርጉ ስልኩ ከልክ በላይ እንዲግልና እንዲሞቅ ስለሚያደርገው መጥፎ አጋጣሚም ሊፈጠር ይችላልና ከመጠቀም ይቆጠቡ።
(fbc)
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
Hawassa
Opening Hours
| Monday | 09:00 - 20:00 |
| Tuesday | 09:00 - 20:00 |
| Wednesday | 09:00 - 20:00 |
| Thursday | 09:00 - 20:00 |
| Friday | 09:00 - 20:00 |
| Saturday | 09:00 - 20:00 |