PenCom Computer Cener

PenCom Computer Cener

Share

01/11/2021

ሰላም የተወደዳችሁ ወዳጆቼ እና የፊልም አፍቃሪያን እንደምን አረፈዳችሁ? ዛሬም እጅ ከምን ካላችሁን የሴት ልጅን ክብር ፤የፍቅርን ፍሬ በ" ፍትህ መንገድ" ልንጠቁም ወደን #"የፍትህ #መንገድ" የተሰኘ የአማርኛ ፊልም ይዘን ቀርበናል። ይህንን ፊልም ጎዶ ሲፅፈው፣ በረከት ይሄይስ አዘጋጅቶት ዮሴፍ አበበ ፕሮዲዩስ አድርጎታል።

እርሶም #በጥቅምት #28 የምረቃ መርሀግብር ላይ #በፒያሳ #ሌዊ #ሲኒማ ከቀኑ #10:00 ላይ በመገኘት የደስታችን ተካፋይ ፣ የድምቀታችን አካል እና የልፋታችን ውጤት ባለቤት ይሆኑ ዘንድ በቤተሰባዊ ጥሪ ተጋብዘዋል።

Photos from Yeshua print and Advert's post 13/01/2020
26/10/2014

አንዳንዴ በስራ ቦታችን ጠገጠሙንን ገጠመኞች እናወጋችኋለን፡፡ እናንተም ልታካፍሉን ትችላላችሁ፡፡

በቅርብ ቀን አንድ ባለጉዳይ መጣና ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ሰበር ችሎት ጽፎ ያመጣውን ማመልከቻ ፃፍልኝ አለኝ፡፡ ፃፍኩለት፡፡ አጠቃላይ ሃሳቡ ሚስቱ ፍታኝ ብላው የሱ አካባቢ ፍርድ ቤትም ለሷ ፈርዶላት እሱ ግን ፍቺውን ተቃውሞ ይግባኝ እየጠየቀ ነው፡፡ እና የሱን አቤቱታ እየፃፍኩለት…ሌሎች ገጠመኞቼንም ደማምሬ የሚከተለውን ሃሳብ….ከሶስት ቀን በኋላ እንደሚከተለው አሰፈርኩት፡ …….
…….
መፋታትን ፈታሁ

ልቤ ላይ አርማሞ ቅሬታና ምሬት
መራራ ከራራ ሰላም የሌለበት
እሾህ አሜኬላ ስትተክይ ኖረሽ
ክፋት መናገሬን ቃላቶችን ቆጥረሽ
ፍታኝ አልሽን ኋላ ለታዛቢ ነግረሽ
እኔስ አልፈታሽም አልፈርምም ከቶ
የዘራሽውን ሁሉ አጭደሽ ከኔ ወጥቶ
ሰንኮፉ ከውስጤ እስኪነቀል ድረስ
እስከሞት ያልነውም መሃላችን ሳይፈርስ
እንዘልቃለን እቱ አጋም እሾህ ሆኜ
የጎነጎንሽኝን ሁሉ ተጎንጉኜ
በሰው ይብቃ ፍቺ እኔ ቤት አይግባ
ፈትቼሽ ያገባሽ ከቶ እንዳያነባ!
እኔው ልሁን ክፉ ክፋትሽን ውጬ
ሌላው በኔ ይዳን በሰጠሽን ስለት እግርሽን ቆርጬ
አልፈታሽም ከቶ ጋግረሽ እንድትበዪ
የዘራሽውን ሁሉ አንዲቷን ሳትጥዪ!


3፡02PM 23/10/2014 home…

Photos 24/10/2014
Want your business to be the top-listed Computer & Electronics Service in Hawassa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Address


SNNPR
Hawassa
88

Opening Hours

Monday 07:00 - 20:45
Tuesday 07:00 - 20:45
Wednesday 07:00 - 20:45
Thursday 07:00 - 20:45
Friday 07:00 - 20:45
Saturday 07:00 - 20:45
Sunday 07:00 - 20:45