Horn Insight
11/07/2026
ሀዋሳ ከተማ ያስመዘገበችው ተጨባጭ ውጤት በአጋጣሚ የመጣ ሳይሆን አስተዳደሩ በትኩረት የሰራባቸው ቁልፍ ስልቶች ያመጡት ውጤት መሆኑን ከንቲባው አቶ ጥራቱ በየነ ገለጹ
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ባካሄደበት ወቅት፣ በልማትና በለውጥ ሥራዎች የተመዘገቡት ስኬቶችና በቀጣይ ትኩረት የሚሰታቸው አቅጣጫዎች በሰፊው ተገምግመዋል።
የከተማዋ ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ በመድረኩ ላይ እንደገለጹት፣ ሀዋሳ በተለያዩ ዘርፎች ያስመዘገበችው ተጨባጭ ውጤት በአጋጣሚ የመጣ ሳይሆን አስተዳደሩ በትኩረት የሰራባቸው አምስት ቁልፍ ስልቶች ያመጡት ውጤት ነው።
የመጀመሪያውና ዋናው የስኬት ሚስጥር የሕዝብ ተሳትፎ መሆኑን የጠቀሱት ከንቲባው፣ ነዋሪዎች ከዕቅድ አወጣጥ ጀምሮ እስከ ክትትልና ግምገማ ባሉት የልማት ሂደቶች ላይ በንቃት እንዲሳተፉ መደረጉ የጋራ ባለቤትነትን በመፍጠር ረገድ ከፍተኛ ሚና ማበርከቱን አስረድተዋል።
ከዚህ በተጨማሪም፣ የገቢ አሰባሰብ ሥርዓቱን በቴክኖሎጂ በማዘመንና የንግድ ከባቢን በማሻሻል የከተማዋን የፋይናንስ አቅም ማሳደግ እንደተቻለና ያለውን ውስን ሀብት በአግባቡ በመጠቀም፣ ብክነትን በማስወገድና በታቀደለት ዓላማ ላይ ብቻ በማዋል የወጪ ቁጠባ ሥራዎች በስኬት መተግበራቸውን ገልጸዋል።
በሌላ በኩል፣ የታቀዱ ሥራዎችን ወደ ተጨባጭ ውጤት ለመቀየር የአስፈጻሚ አካላትን የመፈጸም አቅም በሥልጠናና በቴክኖሎጂ ማብቃት ሌላኛው ስትራቴጂካዊ እርምጃ እንደነበር ተጠቁሟል።
ከሁሉም በላይ ደግሞ የሕዝብ አገልጋይ ነኝ የሚል ስሜት ሰርጾበት ሙስናና ብልሹ አሠራርን የሚጸየፍ፣ ችግሮችን በፈጠራና በአዲስ አስተሳሰብ የሚፈታ አዲስ የሥራ ባህል በሰው ኃይሉ ውስጥ መገንባቱ ለከተማዋ ዕድገት ዋስትና መሆኑ ተረጋግጧል።
በቀጣይም በእነዚህ አምስት መሠረታዊ ምሰሶዎችና ሌሎች አዋጭ ሥራዎች ላይ ይበልጥ በትኩረት እንደሚሠራ ከንቲባው አረጋግጠዋል።
"የባሰ አለና ሀገርህን አትልቀቅ" ይላል ያገር ሰው።
ይህ መንፈሳዊ ትንቢት ነው?
ፖለቲካዊ አቅጣጫ? ወይስ
ባህላዊ ጥንቆላ ነው?»
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
Hawassa