Harari Regional State Innovation and Technology Agency

Harari Regional State Innovation and Technology Agency

Share

Photos from Abiy Ahmed Ali's post 16/05/2026
15/05/2026

📣 ተራዘመ!

በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ለስታርታፖች የቀረበው ታላቅ እድል የምዝገባ ጊዜ እስከ ግንቦት 21፣2018 ዓ.ም ተራዘመ!

በበርካታ የእድሉ ፈላጊዎች ጥያቄ መሰረት የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የስታርታፕ ድጋፍ ሁለተኛ ዙር መርሓ-ግብር የምዝገባ ጥያቄ ተራዝሟል፡፡

በመጀመሪያው ዙር ሁሉን አቀፍ የድጋፍ መርሓ-ግብር ከ200 በላይ የቴክኖሎጂ አፍላቂዎች፣ ተመራማሪዎች እና የዘርፉ ባለሙያዎች የእድሉ ተጠቃሚ ሆነዋል። እነዚህ ወጣቶች በነበራቸው ቆይታ ድንቅ የፈጠራ ሃሳቦቻቸውን ወደ ተግባራዊ የንግድ ሞዴል እና ምርት በመቀየር ረገድ ከፍተኛ ስኬት አስመዝግበዋል። ኢንስቲትዩቱ ይህንን ተሞክሮ መሰረት በማድረግ አሁን ደግሞ ይበልጥ ሰፊ እና አዳዲስ ድጋፎችን በማካተት ሁለተኛ ዙር ዕድል አመቻችቷል።

🎯በግብርና፣ በጤና፣ በደህንነት፣ በትምህርት፣ በፋይናንስ፣ በሮቦቲክስ፣ በኤ.አይ ኤጀንት፣ በቨርችዋል እና ኦግመንትድ ሪያሊቲ ዘርፎች ላይ የፈጠራ ሀሳብ ያላቸው ሁሉ መሳተፍ ይችላሉ፡፡

⏰ የምዝገባ ጊዜ፡- እስከ ግንቦት 21፣ 2018 ዓ.ም

🔗ለማመልከት፡- aistartup.aii.et ይጠቀሙ!

📌በዚህ ታላቅ እድል የፈጠራ ሃሳብዎን ወደ ተጨባጭ ምርት እና አገልግሎት፤ ህልምዎን ወደ እውነታ እንዲቀይሩ ተጋብዘዋል!

Want your organization to be the top-listed Government Service in Harar?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Address


Harar