Shagiiz.Abebe

Shagiiz.Abebe

Share

31/01/2026

ወያኔ በህዝብ ደረጃ ጠላት አድርጎ በብቸኝነት የፈረጀው የአማራን ህዝብ ነው‼
==========
ወያኔ የአማራን ህዝብ በጠላትነት የጀመረው ገና በደደቢት በረሀ ሲመሰረት ጀምሮ ነው ። ለወያኔ የአማራ ህዝብ ትምክህተኛ ነው ፤ ገዢና ጨቋኝ መደብ ነው ፤ ተስፋፊና ወራሪ ህዝብ ነው።

ወያኔ ይህንን ቋጥሮ ላለፉት ሰላሳ አመታት የአማራን ህዝብ በተለየ መልኩ የመምታት ፖሊሲና ስትራቴጂ ቀርፆ ሲተገብር ኖሯል። በዚህም እንደየትኛውም የኢትዮጵያ ህዝብ ሁሉ ከየትኛውም አገዛዝ ተጠቅሞ የማያውቀው የአማራ ህዝብ ከፍተኛ ገፈት ቀማሽ ሆኖ አልፏል። ወያኔ በፈጠረው የአማራ ህዝብ በዝባዥነት ተረክ የአማራ ህዝብ የገንጣይ ብሔርተኞች ሁሉ የጥቃት ኢላማ ሆኖ በአራቱም አቅጣጫ ተጠቅቷል። እየተጠቃም ነው!

የወያኔ በአማራ ላይ የያዘው ቂም ዘመን የማይሽረው ሁኔታ የማይለውጠው ነው። የትግል መዝሙሩን ሳይቀር አማራን ስለመምታት ስለማንበርከክ ነው ወያኔ ከአማራ ህዝብ ላይ ምላጩን ነቅሎ አያውቅም።

ወያኔ ከስልጣኑ ከተወገደ በሗላ በመከላከያ ሰራዊት ላይ በፈፀመው የክህደት ጦርነትና ከዚያ በሗላ ለደረሰው ያ ሁሉ ሰብአዊ እልቂት ዋና ተጠያቂ የሚያደርገው የአማራን ሀይል ነው። የወያኔ አመራሮች የሚሉት በትግራይ ላይ ለተፈፀመው "ጄኖሳይድ" ዋና ተጠያቂው የአማራ ሀይል ከዚያም የሸእቢያ ሰራዊት ነው። መከላከያ ሰራዊት ጄኖሳይድ ፈፀመ ሲሉ ብዙ አይሰማም። አብዛኛው የጦር ወንጀሎች የተፈፀሙት በአማራ ፋኖና በሸእቢያ ነው ብለው ነው ይፋ የሚያደርጉት። ከትግራይ ይውጣልን ሲሉ የነበሩትም የአማራ ሀይልን እና ሸእቢያን ነበር።

ለዚያም የወያኔ አመራሮች የዘወትር ዛቻ " ከአማራ ተስፋፊ ሊሂቅ ጋር ሂሳብ እናወራርዳለን" የሚል ነበር።
ይሄንን ቃል በኦሮሞውም ሆነ በየትኛውም የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ አልተጠቀሙትም።
ተገላባጩ ወያኔ የብልፅግናን የሀይል ሚዛን ለማመጣጠን ከሻእቢያ ጋር ጥምረት ከፈጠረ በሗላ ግን አማራን በወያኔ ሀይል ከመበቀል ይልቅ አማራን በአማራ መበቀልና አማራን የማይወጡበት የውድመት ቀጠና ማድረግን መረጠ። በርግጥ አዋጭ ስትራቴጂ ነው።
ክልሉን አወደመው ከየትኛውም ጦርነት በላይ አደቀቀው። ወያኔ በርግጥም የአማራን ህዝብ ተበቅሏል።
ወያኔ በመከላከያ ሰራዊትና በፋኖ ሀይል መካከል በሚደረገው ፍትጊያ ሁለቱም ከተዳቀቁና ከተዳከሙ በሗላ የአማራ ክልልን ለመውረር ነበር ሲዘጋጅ የከረመው።

እንግድህ የወያኔ ህልም ወልቃይትንና ራያን ጠቅልሎ ሀገረ ትግራይን መመስረት ነው።

የማን ህልም ይሳካል?
የምናየው ይሆናል!

Want your organization to be the top-listed Government Service in Gondar?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address


Gondar
DEBRETABOR