Addis Belete Fan
24/06/2020
ኦርቶዶክስ ተዋሕዶን እንወቅ!:
ኦርቶዶክስ መልስ አላት
ክፍል_12
ቤተክርስቲያን ለምን እንሳለማለን?
ቤተክርስቲያን የሚለው ቃል #በ3 ዓይነት ፍቺ አጠቃቀም በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እናገኛለን። ሕንጻውን ቤተክርስቲያን እንለዋለን። የክርስቲያኖች ሕብረት ወይም አንድነት ቤተክርስቲያን ይባላል። እያንዳንዱ ግለሰብ ቤተክርስቲያን ይባላል። አምላካችን እግዚአብሔር አስቀድሞ ለሙሴ "በመካከላቸው አድር ዘንድ መቅደስ ሥሩልኝ " ብሏል ። (ዘጸ25:8) ይህም የሚያመለክተው መቅደሱን መሥራት ከፈቃደ እግዚአብሔር የተገኘ እንጂ ፈጠራ እንዳልሆነ ግልጽ ያደርግልናል ። ሕንፃ ቤተክርስቲያኑ ድንጋይ ነው ፣ ጭቃ ነው አይባልም ። እቃው የተሰራበት ድንጋይ ሆነ ፣ ጭቃ ሆነ ፣ ሣር ሆነ የሚከብርበት የሚመለክበት #ጌታ ነው ። በወንጌል ጌታ "ቤቴ የጸሎት ቤት ይባላል የአባቴን ቤት የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችሁት " (ዮሐ 2:13) በማለት ገርፎ ሲያስወጣቸው እናያለን ። ታዲያ ቤቱ የማይከብርበት ቢሆን ሕንጻው የማያስፈልግ ቢሆን ጌታ አምላካችን በጅራፍ ገርፎ ባላስወጣቸው ነበር ።
(እንሰግዳለን)
በህንፃ ቤተእግዚአብሔር ተገኝተን እንሳለማለን ፣ እንሰግዳለን ይኸውም ለባለቤቱ ያለንን ፍቅርና አክብሮት ለመግለጽ ነው ። የመስገዳችንም ምስጢር በቤተ እግዚአብሔር ፊት ስለሆነ የምንሰግደው ለእግዚአብሔር እንጂ ለሕንፃው አይደለም ። እስኪ መረጃ የሚሰጡንን ጥቅሶች እንመልከት ። 2ኛ ዜና መዋ 7:1 " ሰሎሞንም ጸሎቱን በፈፀመ ጊዜ እሳት ከሰማይ ወረደ የሚቃጠለውን መስዋዕትና ሌላ መስዋዕቱን በላ የእግዚአብሔርም ክብር ቤቱን ሞላ የእግዚአብሔርም ክብር ቤቱን የእግዚአብሔርን ቤት ሞልቶት ነበርና ካህናቱ ወደ እግዚአብሔር ቤት መግባት አልቻሉም ። የእስራኤልም ልጆች ሁሉ እሳቱ ሲወርድ የእግዚአብሔርም ክብር በቤቱ ላይ ሲሆን ያዩ ነበር በወለሉም ላይ በግምባራቸው ወደ ምድር ተደፍተው #ሰገዱ እርሱ መልካም ነውና ምህረቱም ለዘለዓለም ነውና ብለው እግዚአብሔርን አመሰገኑ " በማለት በግልፅ መፅሐፍ ቅዱስ የክብሩ መገለጫ የሰማይ ደጅ እንደሆነች በተለያዩ ቦታዎች ያስረዳናል ። መፅ.ሳሙ.ካል 12:20 "ዳዊትም ከምድር ተነስቶ ታጠበ ተቀባም ልብሱንም ለወጠ ወደ እግዚአብሔርም ቤት ገብቶ #ሰገደ " ይላል ። መዝ 5:7 " እኔ ግን በምሕረትህ ብዛት ወደ ቤትህ እገባለው አንተንም በመፍራት ወደ ቅድስናህ መቅደስ #እሰግዳለሁ " ። መዝ 28(29):2 "የስሙንም ክብር ለእግዚአብሔር አምጡ በቅድስናው ስፍራ ለእግዚአብሔር #ስገዱ " ይላል ።
ታዲያ ይህ የቅድስና ስፍራ ቤተክርስቲያን አይደለምን ? መዝ 131(132):7 "ወደ ማደሪያዎቹ እንገባለን እግሮቹ በሚቆሙበት ሥፍራ #እንሰግዳለን " ። ማደሪያው ቤቱና ታቦቱ እንደሆነ እና በዛ ሆኖ ሙሴን እንደሚያናግረው በዘጸ25:22 ላይ ገልፆታል ። በሐዲስ ኪዳንም ሐዋ18:22 ላይ "ወደ ቂሳርያም በደረሰ ጊዜ ወጥቶ ለቤተክርስቲያን ሰላምታ ከሰጠ ቡሃላ ወደ አንጾኪያ ወረደ " ይላል ። ይህም በሀዲስ ኪዳን ለቤተክርስቲያን መስገድ ወይም ሰላም ለኪ ብሎ መስገድ የተገባ መሆኑን ቅዱስ ጳውሎስ አስተምሮናል ።በመጨረሻም በ1ኛ ነገ. 9:3 " ...በፊቴ የጸለይከውን ጸሎትህንና ልመናህን ሰምቻለሁ ፡ ለዘላለምም ስሜ በዚያ ያድር ዘንድ ይህን የሰራኸውን ቤት ቀድሻለሁ ዓይኖቼና ልቤ በዘመኑ ሁሉ በዚያ ይሆናሉ " ። ብሎ ለሕንፃው ቤተመቅደስ እግዚአብሔር የሰጠውን ይህን ታላቅ ክብር ማስተዋል ይገባል ።
16/06/2020
ማዕዶት ዘ ኦርቶዶክስ:
addis belete:
በአዲስ አበባ ባለፉት 24ሰአታት በተደረገ ምርመራ 98 ሰዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው የአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ ገልጿል።‼️
እስከዛሬ ድረስ በተደረጉ የላብራቶሪ ምርመራዎች 2577 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።
-ዛሬ ከተገኙት ውስጥ 3ሰዎች የውጪ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው ሲሆኑ 5ሰዎች ከበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው ናቸው። 90ሰዎች ደግሞ የውጪ ሀገር ጉዞ ታሪክ እና ከበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት የሌላቸው መሆናቸው ተረጋግጧል።
በክፍለ ከተማ ደረጃ አጠቃላይ እና ዛሬ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር ስንመለከት
ክፍለ ከተማ አጠቃላይ ዛሬ
1. አዲስ ከተማ ---- 590------37
2. ቦሌ -----411------4
3. ጉለሌ ---- 286-----4
4. ልደታ ---- 265-----13
5. ኮልፌ ቀራኒዮ ---- 243-----8
6.ቂርቆስ ----155-----16
7. አራዳ ----149-----7
8.የካ ----144------2
9. ንፋስ ስልክ ላፍቶ---133 -----4
10.አቃቂ ቃሊቲ ----79 -----2
11.በመጣራት ላይ ያለ-122-----1
⏸ጠቅላላ ድምር -----2577--98
©አዲስአበባ ከተማ ጤና ቢሮ
addis Belete
👉 ጋዜጠኛ ሰላማዊት ደጀን EBS TV የቅዳሜን ከሰዓት አዘጋጅ በነበረችበት ወቅት በEBS TV ህግ መሰረት ወደ Studio ለቀረጻ ከመግባቷ በፊት አንገቷ ላይ ያለውን መስቀልም ሆነ ማህተብ እንድትፈታ ትደረግ እንደነበር ተናግራለች።
ሰላማዊት ደጀን ከEBS አስቀድሞ ከዓመታት በፊት Ebc/etv Sport ዘጋቢም ነበረች ፥ በዛን ወቅትም እንዲሁ ከአንገት ላይ ማህተብ መፍታት ግዴታ ነበር። ይሄን ጉዳይ ሌሎች ጋዜጠኞችም በተደጋጋሚ እንደቅሬታ የሚያነሱት ተግባር ነው በተለይ በመንግስት ሚዲያዎች።
ይሄ ጉዳይ ምን ታስቦ እንዲህ እየተደረገ እንዳለ ግራ ገብቶኛል። ሙስሊም ሴት አንከሮች ሂጃባቸውን እንደለበሱ ዜና ያነባሉ ቢያነቡም ችግር የለውም፤ አንድ የኦርቶዶክስ ጋዜጠኛ የግድ Studio ለመግባት ከአንገት ላይ መስቀል እንዲወልቅ የሚደረግበት ለምንድነው? ምንስ ታስቦ እንደሆነ ፈጽሞ አልገባኝም።
ሌሎች ሴት ጋዜጠኞች ተራቁተው ጡታቸውን ሳይቀር አጋልጠው እያሳዩ ሚሊየኖች በሚታደሙበት የTv ቻናሎች ላይ ሲቀርቡ ማህበረሰባዊ ና ሞራላዊ ህግና ስነስርዓት እንደተጣሰ ተቆጥሮ እርምጃ ሊወሰድ ሲገባ ሃይማኖታዊ መብትን በሚጋፋ መልኩ ከአንገት ላይ መስቀል እንዲበጥሱ ማድረግ ግን በተጻፈ ህግ ሳይቀር ፕሮግራም አስፈጻሚዎችና ዳይሬክተሮች የእለት ተዕለት ክትትል የሚያደርጉበት ተግባር ሆኖ ሲታይ የሆነ ነገር እንዳለ መረዳት አይከብድም።
ጉዳዩ ሃይማኖታዊ መለያዎችን የጋራ በሆኑ ሚዲያዎች ላይ መታየት የለበትም ከሆነ ይሄ ህግ ሁሉም የሃይማኖት ተከታዮች ላይ በእኩል ሁኔታ ስለምን አንተገበርም? ለአንዷ ሂጃብ ለብሶ መዘገብ ሲፈቀድ ለሌላዋ ከአንገቷ ላይ መስቀል እንድት በጥስ ማድረግ ምን ማለት ነው?
ሌላው ያለን ሃይማኖተኛ ህዝብ ነው ለምንድነው ህዝቡን የሚመስል ሁሉም በራሱ መለያና ማንነት ሆኖ እንዲቀርብ የማይደረገው? ያሌለን ማንነት መዋስ ለምን ያስፈልጋል።
❗️ይሄ ተግባር በመንግስትም በግልም ሚዲያዎች በተደጋጋሚ እየተፈጸመ እንዳለ ይሰማል። በቀደመው ጊዜ ሀገሪኛ ፊልሞችና ሲሰሩ እንዲሁ ተዋኖያን ከአንገታቸው ላይ መስቀላቸውን እንዲፈቱ ለማድረግ ተሞክሮ በአርቲስቶቹ ትግል እንዲቀር ሆኗል፤ ።
ተከታታይ ዓመታት የዘለቀውንና ጋዜጠኞች ላይ እየተደረገ ያለውን ማህተም የማስፈታት ተግባር ለማስቆም መደረግ ያለበት ሁሉ ሊደረግ ይገባል። ከቤተክርስቲያናችን የላይኛው አካል ጀመሮ ትኩረት ተስጥቶት እስከ ምዕመን ድረስ እየተደረገ ያለውን ሊያውቅ ይገባል።
#ሼር
share
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Telephone
Website
Address
Dessie
1234