Addis Page

Addis Page

Share

Photos from Addis Page's post 23/03/2026

ኢራን የሆርሙዝን ስትሬት እንደምትዘጋ በድጋሜ አስጠነቀቀች‼

​ኢራን የኃይል ማመንጫዎቿ ላይ ጥቃት ከተሰነዘረ ስልታዊ ጠቀሜታ ያለውን የሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ሙሉ በሙሉ እንደምትዘጋና በክልሉ የኢነርጂ ተቋማት ላይ የአጸፋ ጥቃት እንደምትሰነዝር አስታወቀች።

​በሌላ በኩል፣ የእስራኤል ጦር በደቡብ ሊባኖስ የሚገኘውን የቃሲሚያ ድልድይ ማውደሙን ተከትሎ፣ የሊባኖሱ ፕሬዝዳንት ጆሴፍ አውን ድርጊቱ "ለምድር ወረራ መነሻ ነው" ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል።

ወቅታዊው ሁኔታ በቀጠናው መጠነ ሰፊ ጦርነት ሊቀሰቅስ ይችላል የሚል ከፍተኛ ዓለም አቀፍ ስጋት ፈጥሯል።

Wasu Mohammed - Mereja

23/03/2026

የምርጫ ካርድ በግድ ውሰዱ❌‼️
​የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መግለጫ፡ "ዜጎችን አስገድዶ የምርጫ ካርድ ማስወጣት ሕገ-ወጥ ነው"‼️
​በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅ ቁጥር 1394/2017 መሠረት፣ ዜጎች የምርጫ ካርድ እንዲያወጡ የመቀስቀስ ሙሉ ኃላፊነት የተሰጠው ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ብቻ መሆኑ ተገለጸ።

​የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላተወርቅ ኃይሉ መጋቢት 4 ቀን 2018 ዓ.ም. በሰጡት መግለጫ እንዳመለከቱት፣ በአንዳንድ አካባቢዎች ዜጎች መሰረታዊ አገልግሎቶችን ለማግኘት እንደ ቅድመ ሁኔታ የምርጫ ካርድ እንዲያወጡ የማስገደድ ሁኔታዎች መኖራቸውን ቦርዱ ጥቆማ ደርሶታል።

​ከመግለጫው የተወሰዱ ዋና ዋና ነጥቦች፦

​ነጻ ፈቃድ፦ ማንኛውም ዜጋ የምርጫ ካርድ የማውጣት መብት እንጂ የመገደድ ግዴታ የለበትም።

​የቅስቀሳ ገደብ፦ በሕግ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት የመራጮች ትምህርት መስጠት የሚችለው ቦርዱ ወይም እርሱ ፈቃድ የሰጣቸው የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ብቻ ናቸው።

​ሕገ-ወጥ አሰራር፦ "በየሰው ቤት እየተሄደ" የሚደረግ የካርድ ማስወጣት ቅስቀሳም ሆነ ዜጎችን በተለያዩ አገልግሎቶች አማካኝነት ተጽዕኖ መፍጠር በአዋጁ ተቀባይነት የሌለው ተግባር ነው።

​ቦርዱ ይህን መሰል ጫናዎችና ሕገ-ወጥ ቅስቀሳዎች በአስቸኳይ እንዲቆሙ ለሚመለከታቸው አካላት ማሳወቁን ሰብሳቢዋ አረጋግጠዋል።

20/03/2026

በቲክቶክና በት/ቤት የተሰራጨው ሱስ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••
ታዳጊዎችን እየበላ ያለው አዲሱ ወጥመድ⁉️
ወዳጄ... ታዳጊዎች "Drill Rap" እየሰሙ፣ በስፕራይት ኮዳ ውስጥ "ቀይ መጠጥ" ይዘው ቲክቶክ ላይ ሲያሽቃብጡ ካየሃቸው ዝም ብለህ አትለፋቸው። ነገሩ "ሊን (Lean)" ይባላል። ለሳል ተብሎ የታዘዘን ሽሮፕ (እንደ Euphon ያሉ) ከለስላሳ መጠጥ ጋር በመቀላቀል የሚዘጋጅ "የመቃብር መንገድ" ነው።

1. "ሽሮፕ" አይደለም... "መርዝ" ነው! 🧪
እነዚህ የሳል መድኃኒቶች ውስጥ Codeine (ኮዴይን) የተባለ ንጥረ ነገር አለ። ኮዴይን ደግሞ ከሄሮይን ጋር የሚመደብ Opioid የተባለ አደገኛ ዕፅ ዘር ነው። ልጆቹ እንደ ፋሽን "ሊን" እያሉ የሚጠጡት ነገር፣ ሳያውቁት በከባድ ሱስ ተተብትበው ነፍሳቸውን ለሰይጣን እንዲሸጡ እያደረጋቸው ነው።

2. የ"ሊን" መራራ ዋጋ (The Deadly Effects)፦
ይህ መጠጥ ዛሬ "ፈገግ" ቢያደርጋቸውም፣ ነገ ግን የሚከተሉትን ይዞ ይመጣል፦
• የመተንፈስ ስራ ማቆም፦ ሳንባን በማደንዘዝ መተንፈስ እስከማቆም ያደርሳል።
• የልብ አመታት መዛባት፦ የልብ ምትን በማቀዝቀዝ ለድንገተኛ ሞት ይዳርጋል።
• የአካል ውድመት፦ በሂደት ጉበትና ኩላሊትን ሙሉ በሙሉ ያከሽፋል።
• አእምሮን ማጣት፦ በየጊዜው መጀዘብ፣ ከእውነታው ዓለም መራቅና ለሱስ ጥገኛ መሆን።
• Overdose፦ መጠኑ ሲበዛ መጨረሻው በወጣትነት መቀበር ነው!

3. "ፋሽን" ወይስ "ፍጅት"? 👁️
ዛሬ በትምህርት ቤቶችና በመንደሮች ይህ ነገር እንደ ቀልድ እየተስፋፋ ነው። ልጃችሁ ወይም ታናሻችሁ ያለ ምክንያት እንቅልፍ የሚጫጫነው፣ አእምሮው የተረበሸና እንዲህ ያሉ መጠጦችን በየቦታው የሚይዝ ከሆነ ቆም ብላችሁ መርምሩ። "የልጅ ነገር" ብላችሁ ዛሬ ችላ የምትሉት፣ ነገ ጥቁር ልብስ እንዳያለብሳችሁ!
🚨ሼር ይደረግ

Want your business to be the top-listed Beauty Salon in Debre Birhan?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Address


Debre Birehan
Debre Birhan