Bonga University
27/05/2026
የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የእስልምና እምነት ተከታይ ተማሪዎች የአረፋ በዓልን በደማቅ ሁኔታ አከበሩ።
**ግንቦት 19/2018 ዓ.ም*
የ1447ኛው የኢድ -አድሃ /አረፋ / በዓል የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በደማቅ ሁኔታ አክብረዋል።
የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች የተከበሩ አቶ ተረፈ ሀ/ማሪያም እንዲሁም መ/ር አበራ ሀይሌ የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ሀላፊ እና የተማሪዎች ዲን ተገኝተዋል።
ከፍተኛ አመራሮቹ በየተራ ባሰሙት መልዕክት ተማሪዎችን እና መላ የእምነቱ ተከታዮችን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በተጨማሪም ተማሪዎች ከቤተሰቦቻቸው ርቀው እንደማክበራቸው ዩኒቨርሲቲው እናንተን ለማስደሰት የሚችለውን ሁሉ አድርጓል ብለዋል።
ተማሪዎችም ዩኒቨርሲቲው እንደቤተሰብ ሆኖ ላደረገላቸው ልዩ የበዓል ዝግጅት ምስጋናቸውን ገልጸዋል።
በተማሪዎች የተዘጋጁ መንፈሳዊ እና ሌሎች ዝግጅቶችም የበዓሉ ድምቀቶች ነበሩ።
ዒድ -ሙባረክ!
በጋራ እንችላለን!
25/05/2026
የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የችግኝ ሽያጭ እና ተቋማዊ አሰራር ሁኔታዎች።
ግንቦት 17/2018 ዓ.ም**
ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ከመንግስት የተሰጡትን የመማር ማስተማር ፣ ምርምር እና የማህበረሰብ አገልግሎት ተግባራት በአግባቡ እየከወነ ይገኛል።
በዚህም እስካሁን በተጓዘባቸው መንገዶች ሁሉ ከመማር ማስተማር እና ምርምር ተግባራቱ በተጓዳኝ ለህብረተሰቡ በሚሰጣቸው ሁለንተናዊ አገልግሎት አንቱታን ከማትረፍ አልፎ የሕዝብ ወገንተኝነቱን አሳይቷል።
ዩኒቨርሲቲው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከራሱ አልፎ ለህብረተሰቡ በምርምር የለሙ በርካታ ችግኞችን ሲያስተላልፍ ቆይቷል እያስተላለፈም ይገኛል።
ለአብነትም ባለፈው ዓመት በ2017ዓ.ም ክረምት ወቅት በርካታ የቡና ችግኞችን አማራ ክልል መሸጣችን ይታወቃል።
ይህንን ስናደርግ በግቢያችን ባሉ ሰፊ ሄክታር መሬት የአናናስ መትከያ ስፍራዎች ተዘጋጅተው የተረፉ ችግኞች መሆናቸውንም ለመግለጽ እንወዳለን።
በዚሁ መሠረት የሽያጭ ማስታወቂያችንም ቢሆን ግልፀኝነትን በተከተለ እና በማህበራዊ ሚዲያ ገፁም፣ በማህበረሰብ ሬድዮ ጣብያውም ኤፍ .ኤም 92.1 በማሳወቅ ነው።
በቅርቡም ለማህበረሰብ አገልግሎት እና ለሽያጭ ያለማናቸውን የቡና ፣ የአናናስ ፣ የሮዝመሪ/ጥብስ ቅጠል/ የብርቱኳን ፣ የአቮካዶ ችግኝ ሽያጭ ማስታወቂያ ስናስነግር ግልጽ የሆኑ አካሄዶችን ተከትለናል።
የችግኝ ሽያጮቹን ማስታወቂያ ስናወጣም ቅድሚያ ለማህበረሰባችን በመስጠት ነው። ይህንንም ስናደርግ በስጦታ እና በተመጣጣኝ ዋጋ ሽያጭ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን።
ከዚህ ጋር ተያይዞ በቅርቡ ዩኒቨርሲቲያችን የተደራሽነት አድማሱን በማስፋት ተቋማዊ የሆነ አሰራርን በተከተለ መልኩ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ግብርና ቢሮ የአናናስ ችግኝ ሽያጭ ጥያቄ አቅርቦልናል።
ይህም የግዥ ጥያቄ የመንግስት የፋይናንስ አሰራርን በተከተለ መልኩ ተፈጽሟል።
ነገር ግን ይህንን ተግባር በበጎ ህሊና ባለማየት ወዳልተፈለገ አቅጣጫ በመውሰድ ህብረተሰባችንን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በሚለቀቅ አሉባልታ፣ መሠረተ ቢስና እውነትነት የጎደለው መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን።
አሁንም ቢሆን የአናናስም ሆነ ሌሎች ችግኞችን መግዛት የሚፈለግ የትኛውም የህብረተሰብ ክፍል በማስታወቂያው መሠረት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን እንደምትችሉ ማሳወቅ አንወዳለን።
በጋራ እንችላለን!
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Telephone
Website
Address
Bonga
334