Beyene B.

Beyene B.

Share

Photos from Beyene B.'s post 10/02/2026

በዳውሮ ዞን ከጪ ወረዳ ከ11 ሺህ በላይ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርገው የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ተመረቀ!

ለረጅም ጊዜ የህዝብ ጥያቄና ከፍተኛ የመልካም አስተዳደር ችግር ሆኖ የቆየውን የመጠጥ ውሃ እጥረት በዘላቂነት የሚፈታ ፕሮጀክት በክልላችን ርዕሰ መስተዳድር ክቡር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ አማካኝነት በድምቀት አስመርቀናል።

ይህ ፕሮጀክት መንግስታችን ለህዝቡ መሰረታዊ ፍላጎቶች መሟላት የሰጠውን ከፍተኛ ትኩረት በተግባር ያሳየንበት ስራችን ነው።
የፕሮጀክቱ ዋና ዋና ስራዎች:-
• የውሃ ምንጭ፡- በድምሩ 16 ሊትር በሰከንድ የሚያመነጩ ሁለት ጥልቅ የውሃ ጉድጓዶች።
• 300 ሜትር ኩዩብ ውሃ የመያዝ አቅም ያለው የኮንክሪት ማጠራቀሚያ የዉሃ ገንዳ (Reservoir)።
• 16 ኪሎ ሜትር የከተማ ውስጥ ስርጭት እና 3 ኪሎ ሜትር የዋና ግፊት መስመር ዝርጋታ።
• የኃይል አማራጭ፡- የነዳጅ ወጪን ለመቀነስ በ3 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገዛ ትራንስፎርመር እና ተጠባባቂ ጀነሬተር።
• የፕሮጀክቱ ጠቅላላ ወጪ፡- 52,568,587.13 ብር (በክልል መንግስት SDG በጀት)።
• ተጠቃሚ ህዝብ፡- በዳውሮ ዞን ከጪ ወረዳ የሚገኙ ከ11,720 በላይ ነዋሪዎች፣ ሁለት ትምህርት ቤቶች እና አንድ ጤና ጣቢያ።
ይህ ፕሮጀክት በጥራት ተጠናቆ ለፍሬ እንዲበቃ ላበረከቱት ተቋራጭ ቢንያም ሻምበል እና አማራጭ የኃይል ምንጭ (ትራንስፎርመር) በማመቻቸት አርአያነት ያለው ተግባር ላከናወኑ የወረዳ አመራሮች ምስጋናዬ የላቀ ነው።

የከጪ ከተማ ማህበረሰብ ይህን በከፍተኛ ወጪ የተገነባ የልማት ተቋም እንደ ግል ሀብቱ በመቁጠር ተንከባክቦ እንዲጠብቅና የባለቤትነት ስሜቱን እንዲያጠናክር ጥሬዬን አስተላልፋለሁ።
ንጹህ ውሃ ለጤናማና አምራች ማህበረሰብ!

Photos from Beyene B.'s post 07/02/2026

በምዕራብ ኦሞ ዞን ማጂ ወረዳ የቻይት ቀበሌ ንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት በዛሬው ዕለት ተመረቀ፣

በማጂ ወረዳ 6ሺህ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርገው የቻይት ቀበሌ የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት በዛሬው ዕለት በይፋ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል።

በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የክልልና የዞን አመራሮች ተገኝተዋል።

ለቻይት የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ግንባታ በአጠቃላይ 15,874,245.99 ብር ወጪ የተደረገ ሲሆን፣ ፕሮጀክቱ 6,000 ነዋሪዎችን (በተለይም የ3,060 ሴቶችን) የእለት ተእለት የውሃ እንግልት የሚቀንስ፣ የህጻናትን ጤንነት የሚጠብቅና የአካባቢውን ልማት የሚያፋጥን ነዉ።

በግንባታው ሂደት የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፦
• የ202 ሜትር ጥልቅ የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ፤
• የ100 ሜትር ኩብ የኮንክሪት የውሃ ማጠራቀሚያ ገንዳ ግንባታ፤
• ከ4 ኪሎ ሜትር በላይ የሚረዝም የውሃ መስመር ዝርጋታ፤
• የፓምፕና የጄነሬተር አቅርቦት፣ ተከላ እንዲሁም የቤት ግንባታ፤
• የ6 የውሃ ቦኖዎች ግንባታና ተያያዥ ስራዎች ናቸው።
ይህንን ፕሮጀክት በጥራትና በታታሪነት አጠናቆ ለምረቃ ያበቃው ወንድወሰን ታደሰ የውሃ ስራ ተቋራጭ (GWWC) ሲሆን፤ የክትትልና የጥራት ቁጥጥር ስራው በክልሉ ውሃ ቢሮና በምዕራብ ኦሞ ዞን ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ መምሪያ በጋራ በመሆን ነዉ።

Photos from Beyene B.'s post 13/01/2026

# ቢስት ባር በሚዛን አማን
እንኳን አደረሳችሁ፣ አደረሰን

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Bonga?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address


Bonga