Gech Gm page
28/12/2025
29/08/2025
ሆዴ 'ኮ ባዶ ነው ፤
ይላል፥አንዳንድ ሰው ፤
የልቡን ተናግሮ . . .፣
ፈንጥዞ ጨፍሮ . . .፣
እንክት፥ አርጎ ስድቦ፣
እርክት፥ ብሎ ጠግቦ፤
በኋላ ሲያበቃ ፤
ይ .ቅ .ር .ታ
ይቅርታ በቃ!
ከአንገት በላይ ጥየቃ፤
ውስጤ'ኮ ባዶ ነው ፤
በእጁ እያሳየ፥ሆዱን እየደቃ፤
መታገስ አቅቶት፥ . . .
. . . ለአፍታ ለደቂቃ።
ሆዴ 'ኮ ባዶ ነው ፥ . . .
ማለትስ ምንድነው ?
ከገደለ ወዲያ፥ . . . . .ተኩሶ ጠመንጃው፤
ባዶ 'ኮ ነው ቀልሃው ፥ . .ከወጣ ከላንቃው ።
ከአፍ ከወጣ አፋፍ ፤
ከተተፋ መጥፎ ፀያፍ . . .
የሰውን ልብ እንዴ ከሰበረ፤
ከባድ ነው መመለስ፥ . . .
. . . እንደ ነበረ ።
ልብ ሆነ ኀሊና ፥ . . . . . እጅ እግር አይደለም፤
ስብራት ወለምታ ፥ . . . . . በቅቤ አይታሽም ።
አይጠገን በመረቅ ፤
ቀድሞ ነው መጠንቀቅ ።
Want your practice to be the top-listed Law Practice in Bonga?
Click here to claim your Sponsored Listing.
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the practice
Website
Address
Bonga