Bonga Town Communications
01/06/2026
ምርጫው ለአንድ ሀገር የሚኖረው ፋይዳ የጎላ በመሆኑ ዜጎች በተሰጣቸው ዲሞክራሲያዊ መብታቸውን ተጠቅሞ የሚጠቅማቸውን መንግስት መምረጥ አለባቸው፦ አቶ ታከለ ታምሩ!
የአዲያ-ካካ ምርጫ ክልል የብልጽግና ፓርቲ የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት እጩ ተወካይ አቶ ታከለ ታምሩ ምርጫ ለአንድ ሀገር የሚኖረው ሁለንተናዊ ፋይዳ የጎላ በመሆኑ ዜጎች የተሰጣቸውን ህገመንግስታዊ መብት ተጠቅሞ ነገ የሚመራቸውን መንግስት መምረጥ እንዳለባቸው ጥሪ አቅርበዋል።
የብልጽግና ፓርቲ የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት እጩ ተወካይ የተከበሩ አቶ ታከለ ታምሩ በተወዳደሩበት ምርጫ ክልል ላይ ተገኝተው ድምፅ በሰጡበት ወቅት እንዳሉት ምርጫ በመንግስት ምስረታ ላይ የሚኖረው ፋይዳ የጎላ በመሆኑ ዜጎች በተሰጣቸው ዲሞክራሲያዊ መብት መሰረት የሚበጃቸውን መንግስት መምረጥ እንዳለባቸው አሳስበዋል።
በምርጫ ክልሉ በሁሉም ምርጫ ጣቢያዎች ላይ እየተከናወነ እንዳለ ያነሱት አቶ ታከለ ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ መራጩ ህዝብ ከፀጥታ አካላት ጎን በመቆም የሚጠበቅባቸውን ሀገራዊ ግዴታ እንዲወጡ ጠይቀዋል።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Telephone
Website
Address
Bonga Town
Bonga