Alex.Com
12/04/2026
የትንሳኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ከፍኖተ ሰላም ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት!
የፍኖተ ሰላም ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አለሙ በየነ፣ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ለ2018 ዓ.ም የትንሳኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
"ትንሳኤ፤ ከሽንፈት በኋላ ለሚመጣ ድል፣ ከውድቀት በኋላ ለሚገኝ መነሳት ህያው ምስክር ነው!" ምንም ቢሆን መነሳታችን አይቀርምና ፈጣሪ ለዚህ ክብር ያብቃን።
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳም በገባው ቃል መሠረት፣ የሰውን ልጅ ከመከራ ቀንበር አውጥቶ ወደ መንግስተ ሰማያት ለመመለስ በቀራንዮ አደባባይ ተሰቅሎ፣ ለሦስት ቀናት በመቃብር ከቆየ በኋላ በታላቅ ኃይል መነሳቱን የምናስብበት ዕለት ነው። ይህ በዓል ለእኛም በቃላችን እንድንታመን፣ ለሰው ልጆች ፍቅርን እንድንሰጥና በክፉ ቀን የመጽናናትን ተስፋ እንድንይዝ ትልቅ ትምህርት የሚሰጥበት ነው።
ዛሬ ላይ በማኅበራዊ ሚዲያ አማራጮች የሚሰራጩ የተዛቡና የሐሰተኛ መረጃዎች የማኅበረሰቡን ሰላምና መረጋጋት እየፈተኑ ይገኛሉ። በመሆኑም የከተማችን ነዋሪዎች ከእንዲህ ዓይነት አደናጋሪ መረጃዎች ራሳችሁን በመጠበቅ፣ የከተማችንን ህልውና በትክክለኛ መረጃና በእውነት ላይ ተመስርተን በጋራ ልናስጠብቅ ይገባል ብለዋል።
በዓሉን ስናከብር ሃይማኖታዊና ባህላዊ እሴቶቻችንን መሠረት በማድረግ፣ በመረዳዳትና በአንድነት ሊሆን ይገባል። በተለይም በችግርና በፈተና ውስጥ ያሉ ወገኖቻችንን በማሰብ ማዕድ ማጋራትና ኢትዮጵያዊውን የመተሳሰብ እሴት ማጠናከር እንደሚገባም ኃላፊው አሳስበዋል።
የጌታችን ትንሳኤ፤ ፍቅርን በልባችን፣ በረከትን በቤታችን፣ ሰላምን በሀገራችንና በሕዝባችን ላይ እንዲያሰፍንልን ከልብ እመኛለሁ።
''ትንሳኤ የዘገየ ይመስላል እንጅ አይቀርም!''
አለሙ በየነ
የፍኖተ ሰላም ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ
መልካም የትንሳኤ በዓል!
#ፍኖተሰላም #ኢትዮጵያ #ሰላም
Finote Selam City Communications
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Bahir Dar