Gecho_ICT
31/07/2022
የlaptop ኮምፒዩተሮች CPU ሲያሜ
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
❖አብዛኞቻችን በኮምፒዩተሮቻችን CPU ላይ ያለን እውቀት ውስን ነው፡፡
ለምሳሌ Core i3, Core i5 እና Core i7 CPU አይነቶች ስናይ እላያቸው ላይ ባለው ቁጥር ብልጫ ብቻ እናወዳድራለን፡፡ ከዛሬ በኃላ ግን በትክክለኛው ስያሜ እንገመግማለን፡፡
❖በኮምፒዩተሮቻችን CPU ላይ የምናየው ስሞች እላያቸው ላይ ፊደላት ይገኛሉ፡፡ እነሱ ለምን ተቀመጡ? እንዲሁ በዘፈቀድ የተቀመጠ ፊደላት ናቸውን?
እነዚህ ፊደላት ዝም ብለው የተቀመጡ አይደሉም የራሳቸው የሆን ትርጉም አላቸው፡፡
🖱የኮምፒዩተሮቻችን CPU ስም እነዚህም ፊደላት ከያዘ፡
“K” – Unlocked፡- ያልተቆለፈ CPU ይህ ማለት በቀላሉ Overclocked (የCPU አቅም ከነበረበተት መጠን መጨመር የሚደረግ CPU ናቸው፡፡
ለምሳሌ Core i7-6700k እና Core i7-5820k ባሉ የሞዴል ቁጥር መጨረሻ ላይ unlocked(ያልተቆለፈ) ስለሆሀን Overclocked (የCPU አቅም ከነበረበተት መጠን መጨመር) የተሠሩ ናቸው ፡፡ ይህ ማለት Unloc Processors ከፋብሪካ ዋና ፍጥነቶች በበለጠ ፍጥነት ከመጠን በላይ ሊጫኑ ይችላሉ ፡፡ የተቆለፉ ማቀነባበሪያዎች (Processors) ከመጠን በላይ Overclocked (የCPU አቅም ከነበረበተት መጠን መጨመር) አይችሉም።
ስለዚህ እላያቸው ላይ “K” የሚል ፊደል የሌለበት የCPU አይነቶች የOverclock የመደረግ ሁኔታ አምብዛም ነው፡፡
ምሳሌ፡ Intel® Core™ i5-8600K
“H” – High Performance Graphics: - እነዚህ CPU ለኮምፒዩተር ጨዋታዎች(Gaming) እና ፎቶ እና ቪዲዮ ለማቀናበር ይመረጣሉ ማለትም ብዙ ሀይል ተጠቀሚ እና የተሻለ አቅም ያላቸው CPU ናቸው።
“Q” – Quad Core:- አራት Core ወይም አንድን ስራ ለአራት አካላት የሚከፋፈል CPU ናቸው፡፡
🖱በዚህም መሰረት “HQ” ሚል ፊደላት ካሉ በጣም ውድ እና ምርጥ ከሚባሉት CPU አይነቶች ወስጥ አንዱ ነው፡፡
ምሳሌ፡ Intel® Core™ i7-7700HQ
”M” – Mobile CPU:- በተንቀሳቃሽ(Portable) ኮምፒዩተሮች ላይ የምናገኘው ሲሆን በቀላሉ ለመቀዝቀዝ ትንሽ ሀይል ይጠቀማል፡፡ በተጨማሪም ብዙ ጊዜ እንዲተኙ(Sleep mode capability) የደረጋል፡፡
“Y” - Extremely low Power
“U” – Ultra low Power
ከለይ ያሉት ሁለቱም የሚያመለክቱት ሀይል ቆጣቢ ወይም ዝቅተኛ አቅም ያላቸው CPU ናቸው፡፡
ምሳሌ፡ Intel® Core™ i5-7200U
GetachewTesera_ICT "IT" is the power of life!
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Culinary Team
Attire
Contact the business
Telephone
Website
Address
14
Bahir Dar