Witness Hospitality

Witness Hospitality

Share

29/08/2025

ለዘመናት የሰነቁትን የቱሪዝምና የሆስፒታሊቲ ልምድ እና እውቀት ሊያጋሩን የተዘጋጁ ከዋክብት

09/07/2025

A New Era for Ethiopian Tourism, The Digital Ecosystem Begins

The Ministry of Tourism of Ethiopia thrilled to unveil VisitEthiopia.et—the official digital gateway to Ethiopian tourism.

This integrated, user-friendly portal marks the beginning of a connected ecosystem, simplifying travel planning and enhancing accessibility to Ethiopia's most compelling destinations. With just a few clicks, visitors can:
• Explore stunning natural and cultural sites
• Reserve top-tier accommodations
• Engage trusted local guides
• Access authentic cultural insights and curated experiences
Now fully digitized, Ethiopia—the Land of Origins—welcomes travelers from across the globe with confidence and connectivity.



Selamawit Kassa

02/12/2024

Ethiopian Event Industry Key Players!!

በአለም አቀፍ ደረጃ የኹነት ኢንዱስትሪ ከፍተኛ ገቢ ከማስገኘትም በላይ ሀገራት ምርትና አገልግሎታቸውን እንዲሁም የእድገት ደረጃቸውን የሚያሳዩበት ዋነኛው መንገድ ሆኗል፡፡

ኢትዮጵያም በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ትልልቅ ዓለምአቀፍ፣አህጉር አቀፍና ሀገራዊ ኹነቶችን በማሰናዳት ላይ ትገኛለች፡፡ ምንም እንኳን ዘርፉ እምቅ የገቢ ምንጭ ያለው ቢሆንም በተለያየ ምክንያት መጠቀም አልተቻለም፡፡ በመንግስት በኩል ከሚመጡ ትልልቅ ስብሰባዎችና ጉባዔዎች ባሻገር አሁን አሁን የግሉ ዘርፍ ተዋንያን በአለም አቀፍ ተወዳደሪ በሆነ መልኩ እጅግ ዘመናዊና ፈጠራ የታከለበት የኹነት ዝግጅቶችን ከሀገር አልፈው በጎረቤት እንዲሁም በአለምአቀፍ መድረክ ላይ በሚገባ እየተገበሩ ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህ የግሉ ዘርፍ አንቀሳቃሾች ውስጥ ጥቂቶቹንና በዘርፉ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች መሀከል ፡-

ኦዚ ሆስፒታሊቲ ቢዝነስ ግሩፕ ፡- OZZIE International - Hotel & Resort Project Consultancy

ይህ ዘርፍ አንዱ የቱሪዝም አንቀሳቃሽ ሞተር እንደመሆኑ በሀገራችን የሆስፒታሊቲና ቱሪዝም ኢንዱስትሪ ፈር ቀዳጅ በሚያስብል ሁኔታ ከሀገር አልፎ አፍሪካውያን እንዲሁም ከተለያዩ ሀገራት በናፍቆት ጠብቀው እንዲገናኙ ያስቻለ፣ የሀገር ውስጥ አገልግሎት ሰጪዎች በልዩነት የዘርፉን ነባራዊ ሁኔታ በሚገባ ለአለም እንዲያሳዩ መንገዱን የጠረገ፣ የዘርፍ ባለድርሻዎችንና ባለሙያዎችን በአንድነት እንዲገናኙ በማድረግ፣ በአለምና በአህጉረ አፍሪካ የዘርፉ እጅግ ተፅዕኖ ፈጣሪ ግልሰቦችን፣ተቋማትን እንዲሁም ገዢዎችን በአንድነት እንዲሰበሰቡና የገበያ ትስስር እንዲፈጠር( በሀገራችን ይህ አይነቱ ትስስር በቱሪዝም ዘርፍ ብዙም አልተለመደም ነበር) በማድረግ፣ የተለያዩ አለምአቀፍ ስምና ብራንድ ያላቸው አግልግሎት ሰጪዎች በተለይ ሆቴሎች በሀገራችን እንዲመጡ በማድረግ፣ የአለም የቱሪዝም እንቅስቃሴን በተለይ የቢዝነስ ቱሪዝምን( ማይስ) በልዩነት በማስተዋወቅ ብሎም ከተለያዩ ሀገራት ዘርፉን ጠንቅቀው የሚያውቁ ባለሙያዎች ልምድና ምልከታቸውን በአካል ተገኝተው በመድረክ ንግግር እንዲያደርጉና ኔትወርክ እንዲፈጠር ፕላትፎርሞችን በመፍጠር ረገድ ኦዚ የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳል፡፡

ስለ ሆቴል ሾው አፍሪካ፣ስለ ምስራቅ አፍሪካ የማይስ (MICE)እንቅስቃሴ እንዲሁም ስለ አጠቃላይ የአፍሪካ ሆቴልና ቱሪዝም ነባራዊ ሁኔታ ሁሉም በአንድ ቃል እንዲያወራ ያደረገ ፕላትፎርም ነበር፡፡ በቅርቡም እንደተለመደው የ 2025 ሆቴል ሾው አውደርዕይ በድምቀት ለማከናወን ዝግጅቱን እያደረገ ይገኛል፡፡

በኢትዮጵያ የኹነት ኢንዱሰትሪ ዘርፍ ተኮር በሆነ ሁኔታ በልዩነት ከሚሰሩ አንቀሳቃሾች ውስጥ ኦዚ በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል፡፡ በአጭር ጊዜ ውስጥ የማይስ ቱሪዝም እንቅስቃሴ ከምስራቅ አፍሪካ አልፎ የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት አጀንዳ እንዲሆን ያስቻለ በተደጋጋሚ የሀገራችን የዘርፉ ባለሞያዎች መድረክ እንዲያገኙ አይን የከፈተ እንቅስቃሴ አድርጓል፡፡ Kudos 🙏 Kumneger Teketel WG

Flawless Events-

እንደስሙ ልክ የሆነ የኢትዮጵያ የኹነት ኢንዱስትሪ ከፍ ባለ ሁኔታ እንዲሄድ ብሎም ሀገሪቱ ከሌሎች ተመራጭ እንድትሆን በፈጠራ፣ በኢኖቬሽን፣በፍጥነትና በጥራት የተለያዩ ኹነቶችን) የኮርፖሬት ስብሰባዎችን፣ትልልቅ ጉባዔዎችንና የማነቃቂያ ጉዞ ዝግጅቶችን ከንድፈ ሀሳብ -እስከ መጨረሻ (End to End) ያሉትን ኹነቶች እጅግ በሚያምርና በደመቀ ሁኔታ በማሰናዳት ይታወቃል፡፡

የከዚህ ቀደሙ እንዳለ ሆኖ እንኳን በቅርቡ በሀገራችን ከተካሄዱት ትልልቅ አህጉርና አለም አቀፍ ኹነቶች( 3rd Pan African AI Confrenece, World Without Hunger Adwa Museum,46th CAF Annual Ordinary Assembly, African Refines & Distribution Association, Heineken Leadership Summit, እንዲሁም ከሀገር ውጪ በኬንያ ናይሮቢ African Fintech Summit) ስብሰባዎችና ጉባዔዎች ጀርባ ከ ጅምር እስከፍጻሜ ይህ ኢትዮጵያዊው Women owned Even Company አለ፡፡

በትልልቅ ኹነቶች ላይ የመገኘት አጋጣሚ አለኝ እናም ሁሌም የሚገርመኝ ለስራው ያላቸው ተነሳሽነት፣ወቅቱን የዋጀ አዳዲስ ፈጠራዎች፣ ለሁሉም ዝግጅቶች አዘጋጁን የሚመስል Ambience የመፍጠር ጥረታቸው እንዲሁም ስራን ጥንቅቅ አድርጎ የመስራትና ሆኖ የመገኘት ዲሲፕሊናቸው በሌሎች ሀገራትም የኹነት ዝግጅቶች ላይ እንዲጋበዙ ምክንያት ነው ብዬ አስባለው፡፡

እናም የኢትዮጵያ የቢዝነስ ቱሪዝም እንዲያድግና በርከት ያሉ አለምአቀፍ ይዘት ያላቸው ኹነቶች ወደ ሀገራችን እንዲመጡ የፍሎወልስ አይነት Destination Marketing Companies በብዛትና በጥራት መኖር አለባቸው በሶስተኛ ወገን ዝግጅት ከማሰናዳት( BPO) ባሻገር በራሳቸው አለምአቀፍ የኹነት ገበያ ላይ እየተሳተፉ፣እየተወዳዳሩ ትልልቅ በተለይ የኮርፖሬት ስብሳባዎችን፣የማነቃቂያ ጉዞዎችን፣የማህበራት ኮንፍራንሶችንና አውደርዕይዎችን እያመጡ መስራት ይኖርባቸዋል፡፡ በአመት አምስት ትልልቅ አለም አቀፍ ኹነቶችን በፍሎወለስ በኩል ቢመጣ ከራስ አልፎ የሀገር ኢኮኖሚ ላይ ያለው በጎ ተፅዕኖ የጥምር ሀገራዊ ምርት (GDP) መጠን እስከመቀየር የሚደርስ ነው፡፡

🙏
Prana Events :-

ከላይ እንደተጠቀሱት ሁሉ በሀገራችን የኹነት ዘርፍ በተለይ በትልልቅ የንግድ፣ዘርፍ ተኮር ባዛር እንዲሁም የሙያና የተለየ አውደርዕይ በማዘጋጀት ስማቸው ከሚጠቀሱ አሰናጆች በግንባር ቀደምትነት ከሚጠቀሱ መሀከል ነው ፕራና ኢቬንትስ. በሀገራችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተለመደው የአውደርዕይ ዝግጅት ዲጂታል የመግቢያና መውጫ ምዝገባ ስርዓት እንዲኖረው፣እጅግ የተዋቡ ቀላልና ዘመናዊ ስታንዶች እንዲሁም የተለያዩ ድርጅቶችን ኮርፖሬት ስብሰባዎችንና ጉባዔዎችን በማሰናዳት ይታወቃል፡፡ Nebeyu Lemma 🙏

በዚህም በዘርፉ ያለውን ልምድና ተሞክሮ ይበልጥ በማስፋት በአለምአቀፍ የዘርፉ ገበያ ላይ ተወዳዳሪ በመሆን ተመሳሳይ ኹነቶችን በማምጣት የግሉ ዘርፍ እድል ከተሰጠው ዘርፉን መቀየር እንደሚችል ማሳየት ይኖርባቸዋል፡፡

በመዝናኛው ዘርፍ ጆርካ ኢቬንትስ የሚጠቀስ ነው ይሁንና ከኢኮኖሚዊያዊና ማህበራዊ ተፅዕኖ አንጻር ከሌሎች የሚወዳዳር ባይሆንም ወደፊት ለመዝናኛው ዘርፍ ኹነቶች የሚሆኑ መሰረተ ልማቶችና የዝግጅት ቦታዎች እየተሰሩ መሆናቸውን በማሰብ ኢትዮጵያ ከዚህ የኹነት ዘርፍ ከፍተኛ ገቢ የምታገኝበት ይሆናል፡፡

#መውጫ

የኹነት ዘርፍ(ቢዝነስ ቱሪዝም) በኢትጵያ አይደለም ገና በአፍሪካም ብዙ ያልተነካ በዓለም አቀፍ በየአመቱ ከሚካሄዱ ኹነቶች እጅግ በጣም ጥቂቶቹ ብቻ በአፍሪካ የሚሰናዱ መሆናቸውን ከግምት በማስገባት በሚገባ ከተሰራበት የአፍሪካ አውራ መዳረሻ የመሆን እድሎች አሉን፡፡ አሁን አሁን በሀገራችን እየተሰሩ ያሉት የስብሰባ ማዕከላት፣የተለያዩ መሰረተ ልማቶች፣ለማነቃቂያ ጉዞ የሚሆኑ የማረፊያና መዝናኛ ስፍራዎች እንዲሁም የአፍሪካ የነፃ ንግድ ቀጠና እንቅስቃሴ እውን ሲሆን አንዱና ዋናኛው የገበያ ምንጫችን መሆኑን እየታሰበ መንቀሳቀስ ማለፊያ ይሆናል፡፡

Want your business to be the top-listed Media Company in Awassa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address


Piassa
Awassa