Pharma College

Pharma College

Share

23/05/2026
Marketing isn't a Cost, It is an Investment. - Misikir Mulugeta - S13 Ep150 22/05/2026

ይህን ፓድካስት ጋብዘናችኋል ስለ ማርኬቲንግ ጥሩ ትማሩበታላችሁ

Marketing isn't a Cost, It is an Investment. - Misikir Mulugeta - S13 Ep150 Join us for this episode with Misikir Mulugeta, Commercial Strategist and Business Consultant, and one of the leading figures in Ethiopia’s marketing sector,...

Photos from Pharma College's post 22/05/2026

ፕሮፌሰር እደማሪያም ፀጋ

ፕሮፌሰር እደማሪያም ፀጋ በ1930 ዓ.ም በቀድሞ ጎንደር ክፍለ ሀገር ተወለዱ፡፡የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸው በጎንደርና በአዲስ አበባ ቀዳማዊ ሃይለስላሴ ት/ቤት ተከታትለዋል፡፡ በ1953 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ በሳይንስ የትምህርት ዘርፍ የመጀመሪያ ድግሪ እንዲሁም በ1957 የህክምና ዲግሪያቸውን ካናዳ በሚገኘው ከ McGill University አግኝተዋል ፡፡
በመቀጠልም ለትምህርት ባላቸው ፍላጎት በ1960ዓ.ም ለንደን በሚገኘው የ hygiene and tropical medicine ትምህርታቸውን የተከታተሉ ሲሆን ስዊድን ከሚገኘው የ Lund university ደግሞ የፒ ኤች(PHD) ዲግሪያቸውን ተቀብለዋል፡፡
ፕሮፌሰር እደማሪያም ፀጋ ዘመናዊ የህክምና ትምህርት በሀገራችን እንዲሰፋፋ በግንባር ቀደምትነት ያበረከቱ አንጋፋ ምሁር ሲሆኑ በአዲስ አበባ ዪንቨርስቲ የውስጥ ደዌ የድህረ ምረቃ ፕሮግራም እንዲጀመር በማደረግ ጊዜ የማይረሳው አሻራ አስቀምጠዋል ፡፡ ፕሮፌሰር እደማሪያም ጸጋ በውስጥ ደዌ የትምህርት ክፍል እና የህክምና ትምህርት ፋኩልቲ ሀላፊና በዲንነት ከአስራ አምስት አመት በላይ ያገለግሉ ሲሆን በ1974 ዓ.ም የፕሮፌሰርነት ማዕረጋቸውን አግኘተዋል፡፡
ፕሮፌሰር እደማሪያም ጸጋ በ1987 ዓ.ም ወደ ካናዳ በማቅናት Memorial University of Newfound land የህክምና ፋኩሊቲ በህክምና ፕሮፌሰርነት አግለግለዋል፡፡ 1997 ዓ.ም በኋላ ማስተማር ቢያቆሙም በፕሮፌሰርነት ማእረግ በ McMaster University በህክምና ትምህርት ክፍል ውስጥ አገልግለዋል ፡፡
ፕሮፌሰር እደማሪያም ጸጋ የሀገራቸውን የጤና ዘርፍ ለማገዝ እና ለማሻሻል በታላቅ ተነሳሽነት፣ እና ሀገር ወዳድነት የተለያዩ የትምህርት፣ የአመራርነት እንዲሁም በጤና ጥበቃ ሚኒስተር፣በከፍተኛ ተቋማትና ሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ በኢትዮጵያ ህክምና ማህበር በአስተዳደራዊ ሃላፊነትና ሊቀመንበርነት ለአርባ አመት አገልግላዋል፡፡ እንዲሁም ከሰማኒያ በላይ በሆኑ የህክምና ሳይንሳዊ ጥናት እና ምርምር ስራዎችን በማሳተም ለጤናው ዘርፍ አበርክትዋል፡፡
በተጨማሪም ዩኔስኮን ጨምሮ በተለያዩ አለማቀፍ ተቋማት ውስጥ ተሳታፊ በመሆን አስተዋፅኦ አበርክትዋል፡፡
ፕሮፌሰር እደማሪያም ጸጋ በህክምና ሲረዱ ቆይተው ኑሮአቸውን ባደረጉበት ሃሚልተን ኦንታሪዮ ካናዳ ታህሳስ 23 ቀን 2010 ዓ.ም በ80 አመታቸው ከዚህ አለም ተለይተዋል፡፡ፕሮፌሰር እደማሪያም ጸጋ በመልካም ምግባራቸው የተወደዱ፣ የተመሰገኑ፣በስራቸው የተደነቁ እና ሀገር ወዳድ በሆኑ ኢትዮጵያዊያን ዘንድ ብዙ ተከታዮችን ያፈሩ እና የሀገር ኩራት የሆኑ ታላቅ ሰው ነበሩ፡፡

Photos from Pharma College's post 21/05/2026

ዶ/ር ሙሉአለም ገሠሠ
(በሺህዎች የሚቆጠሩ አራስ ሕፃናትን በማዳን በኢትዮጵያ የጨቅላ ህፃናትን የእንክብካቤ ሥርዓት የለወጡ ታላቅ ሃኪም)

ዶ/ር ሙሉዓለም ገሠሠ ጥር 17 ቀን 1964 በአዲስ አበባ ተወለዱ። ዶ/ር ሙሉአለም ወደ ኩባ ሃቫና የመሄድ እድሉን ያገኙት በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ ጤና መኮንን የነበሩት እና ሀኪም ለመሆን አርዓያ የሆኗቸው አባታቸው በጦር ሜዳ ከተሰዉ በኋላ ነው።

ለሰባት ዓመታት ያህል በሃቫና ውስጥ ሕክምናን ተምረዋል። ከተመረቁ በኋላ ሐረር በመሄድ የጦር ሃይሎች ሆስፒታል ፣ ቢሲዲሞ ሆስፒታል እና ህይወት ፋና ሆስፒታል ውስጥ መስራት ጀመሩ። እዚያም ለአምስት ዓመታት ሰርተው ወደ አዲስ አበባ በመመለስ በየካቲት 12 ሆስፒታል ተቀጥረው ለ10 ዓመታት በጠቅላላ ሐኪምነት አገልግለዋል።

ዶ/ር ሙሉአለም በወቅቱ የነበረውን ሁኔታ ለማሻሻል በማሰብ በኩባ በኒዮናቶሎጂ ንዑስ-ስፔሻላይዜሽን የነፃ ትምህርት ዕድል አግኝተዋል። ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉትን የጨቅላ ህፃናት ሕክምና ተግዳሮቶችን በመሸከም፣ ለመፍትሄዎቹ ምርምር ለማድረግ እና ለመዘጋጀት ተጨማሪ ፈረቃዎችን ሠርተዋል።

ዶ/ር ሙሉአለም ትምህርታቸውን እንደጨረሱ የካቲት 12 ሆስፒታል በመመለስ ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሪፈራልን ለማስቆም የጨቅላ ህፃናት ህክምና ማዕከልን ጀመሩ። ማዕከሉን ያቋቋሙት 4 ነርሶችን በማሰልጠን እና የሚፈለገውን አነስተኛ መሳሪያ በመሰብሰብ ነው። በየካቲት 12 የሚገኘው ማዕከል ከተገነባ በኋላ ሁለት የጨቅላ ህፃናት ህክምና ማዕከላት ብቻ መኖራቸው በቂ እንዳልሆነ ተገነዘቡ። ተጨማሪ የጤና ባለሙያዎችን ማሰልጠን እና በአዲስ አበባ ውስጥ የጨቅላ ህፃናት ህክምና ክፍሎችን ለማስፋፋት የተለያዩ ሰነዶችን ማዘጋጀት ጀመሩ። በቅዱስ ጳውሎስ፣ ጋንዲ እና ዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታሎች እንዲሁም በክልሉ በሚገኙ ሌሎች ሆስፒታሎች ጥረታቸው ስኬታማ ሆነ።

ዶ/ር ሙሉአለም ሁሌም ከልጆች ጋር የመሥራት ፍላጎት ነበራቸው። በየካቲት 12 ሆስፒታል ጠቅላላ ሀኪም ሆነው ሲሰሩ ወደ ሀቫና ተመልሰው የህፃናት ህክምና ለማጥናት ዕድል አገኙ። ለዕረፍት ወደ አዲስ አበባ እንደተመለሱ ጊዜአቸው ሳይደርስ እና ታፍነው የተወለዱ ህጻናት የሚታከሙበት ማዕከል B6 ጥቁር አንበሳ ውስጥ ለ6 ወራት ሰሩ። በዛ ጊዜ ጨቅላ ሕፃናትን ለመንከባከብ የሚያስፈልጉ መሳሪያዎችና ባለሙያዎች እጥረት እንዳለ ተመለከቱ።

ዶ/ር ሙሉአለም በአሁኑ ወቅት እናቶች ራሳቸው አዲስ የሚወለዱ ህፃናትን እንዴት መንከባከብ እንዳለባቸው በማሰልጠን ተደራሽነታቸውን አራዝመዋል። በጨቅላ ህፃናት እንክብካቤ ላይ ተቋማት እና የጤና ባለሙያዎች ላይ የማቋቋምና የአቅም ግንባታ ሰፊ ሥራዎችን ሠርተዋል ሆኖም ሌላው ትልቁ ግንባር ቀደም የሚሰጠው ጉዳይ ሕፃናቱ ወደ ሕክምና ተቋም ከመድረሳቸው በፊት ያለው የቅድመ-መከላከል ስራ ነው። ለእናቶች እና እናት ሊሆኑ ለደረሱ ሴቶች ስልጠና ለመስጠት እና ለራሳቸውም ሆነ ለልጆቻቸው የቅድመ-መከላከል የጤና እንክብካቤ እቅድ ለማዘጋጀት የሚባል የአባልነት አገልግሎት ጀምረዋል። አሁንም የኢትዮጵያ ልጆች በሕይወታቸው ጥሩ ጅምር እንዲኖራቸው የላቀ የጤና አጠባበቅ ሥርዓት ለማቅረብ የገቡትን ቃል እንደጠበቁ ነው። በአገሯ የበቃ ኅብረተሰብ ለመፍጠር የሚያግዙት በዚህ መንገድ እንደሆነ ያምናሉ።
በ11ኛው የበጎ ሰው ሽልማት መርሀግብር በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ዶ/ር ሙሉዓለም ገሰሰ ማሸነፋቸው ይታወሳል።

ምንጭ :-ሃኪም የፌስቡክ ገፅ

Want your university to be the top-listed University in Awassa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Address


Hawassa, AddisAbeba, Shashemene, Sodo
Awassa