Peps or coca

Peps or coca

Share

Mobile uploads 24/07/2024

በቤንች ሸኮ ዞን ሰሜን ቤንች ወረዳ በደረሰ የመሬት ናዳና መሰንጠቅ 208 ሰዎች ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለዋል።

እንደ ዞን ሰሜን ቤንች ፣ ሼይ ቤንችና ሚዛን አማን በከፍተኛ አደጋ ውስጥ የሚገኙ መሆናቸውም ተገልጿል።

የቤንች ሸኮ ዞን ግብርና ፣ ደን ፣ አካባቢ ጥበቃና ህብረት ስራ መምሪያ ኃላፊ አቶ መስፍን ጉብላ ማምሻውን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የክረምቱ የዝናብ መጠን መጨመር ጋር ተያይዞ በሰሜን ቤንች ወረዳ ቃሻ ፣ ሙያ ኬላና ዋላ ቀበሌዎች ከፍተኛ የሆነ የመሬት መሰንጠቅና ናዳ መከሰቱን ገልጸዋል።

ትላንት ማምሻውንና ዛሬን ጨምሮ በ3 ቀበሌዎች ሰሞኑን በተከታታይ በጣለው ዝናብ 28 የመኖሪያ ቤቶች የመሰንጠቅና የመደርመስ አደጋ ደርሶባቸዋል ብለዋል። እንዲሁም በቀበሌዎቹ የበቆሎ ፣ እንሰት ፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ማሳዎች በናዳው መውደማቸውን ገልጸዋል። እስካሁን 208 ለአደጋ ተጋላጭ ሰዎችን ከስፍራው በማውጣት በቀሌዎች ግቢ ፣ በቤተክርስቲያንና ወደ ዘመዶቻቸው የማዘዋወር ስራ መሰራቱን ገልጸዋል።

እንደ ብሔራዊ ሜትሮሎጂ አገልግሎት መረጃ ከሆነ በቀጣይም በቀጠናው ከባድና ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ሊኖር እንደሚችል በትንበያ መግለጹን የጠቆሙት ኃላፊው የዝናብ መጠኑ የሚቀጥል ከሆኑ በወረዳው ተጨማሪ 4 ቀበሌዎች በከፍተኛ አደጋ ውስጥ እንደሚገቡ ጠቁመዋል።

ዋላ ቀበሌ አካባቢ ከዋቻ ማጂ - ማጂ በሚወስደው የአስፓልት መንገድ ላይ የመሰንጠቅና የመደርመስ አደጋ ተከስቷል ያሉት አቶ መስፍን የሚመለከታቸው አካላት በፍጥነት የጥገና ስራ ካለሰሩ የትራንስፖርት አገልግሎቱ ሊቋረጥ እንደሚችል ገልጸዋል።

ነገ ከዞኑ የተለያዩ ተቋማት የተውጣጡ የባለሙያዎች ቡድን ወደ ስፍራው እንደሚጓዝ አቶ መስፍን ጠቁመው የባለሙያዎች ሪፖርትን መሰረት አድርጎ የዞኑ መንግስት ጊዜያዊና ዘላቂ መፍትሔዎች ላይ ይመክራል ብለዋል።

እንደ ዞን ሰሜን ቤንች ፣ ሼይ ቤንችና ሚዛን አማን በቅጽበታዊ ጎርፍ መጥለቅለቅ ፣ የመሬት መሰንጠቅና የናዳ ችግር ውስጥ መሆናቸውን በመግለጫቸው የጠቆሙት አቶ መስፍን በተለይ ሚዛን አማን ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ጎርፍ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስራ ሊሰራ ይገባል ብለዋል።

እስካሁን በሰውና በእንሳት ላይ የደረሰ አደጋ አለመኖሩን ኃላፊው ጠቁመው በሰሜን ቤንች ወረዳ ተጋላጭ በሆኑ 7 ቀበሌዎች ህጻናት ወደ ማሳ እንዳይሄዱ ማድረግ ፣ አርሶ አደሩም እንስሳትን ወደ ግጦሽ ይዞ እንዳይሄድ የቅስቀሳና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ እየተሰራ መሆኑን በጋዜጣዊ መግለጫቸው ጠቁመዋል ሲል የቤንች ሸኮ ኮሙኒኬሽን ዘገባ ተመልክተናል።

Want your business to be the top-listed Food & Beverage Service in Awassa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Culinary Team

Attire

Website

Address


Hawassa
Awassa