Mereja Plus
10/07/2025
አሜሪካ ለኢትዮጵያውን በምትሰጠው የመግቢያ ቪዛ ላይ ቁጥጥሯን አጠናከረች
_____________
በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ስደተኛ ላልሆኑ እና ወደ ዩናይትድ ስቴት መጓዝ ለሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን የሚሰጠው ጊዜያዊ ቪዛ የሶስት ወራት ብቻ እንደሚሆን አስታወቀ። በዚህ የአጭር ጊዜ ቪዛ ኢትዮጵያውያን ወደ አሜሪካ መግባት የሚችሉት አንድ ጊዜ ብቻ እንደሚሆን ኤምባሲው ዛሬ ሐሙስ ባወጣው መግለጫ ይፋ አድርጓል።
እርምጃው ከሐምሌ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ መሆኑን የገለጸው የአሜሪካ ኤምባሲ ውሳኔው ከዚያ በፊት የተሰጡ ቪዛዎች ላይ ተጽዕኖ እንደማያሳድር አረጋግጧል።
ስደተኛ ላልሆኑ ሰዎች የሚሰጥ ቪዛ የሌሎች ሀገራት ዜጎች ለቱሪዝም፣ ለንግድ፣ ለሕክምና እና የተወሰኑ ቋሚ ያልሆኑ ሥራዎች በጊዜያዊነት ወደ አሜሪካ እንዲገቡ የሚፈቅድ ነው።
እስካሁን ድረስ ኢትዮጵያውያን የሚያገኙት ቪዛ ወደ አሜሪካ በተደጋጋሚ እንዲገቡ የሚፈቅድ (multiple-entry) እና እስከ አንድ አመት የሚቆይ ነበር። አዲሱ ገደብ በተለይ ተማሪዎች ፣ ነጋዴዎች፣ ባለሙያዎች እና ከቤተሰብ ጋር ለመገናኘት የሚጓዙ ሰዎች ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል።
በጎርጎሮሳዊው 2024 ብቻ በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ 23,270 ቪዛ ስደተኛ ላልሆኑ ሰዎች እንደሰጠዩናይትድ ስቴትስውጪ ጉዳይ መሥሪያ ቤት መረጃ ያሳያል።
በዶናልድ ትራምፕ የሚመራው የዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ኢትዮጵያ እና ናይጄሪያን ጨምሮ በ36 ሀገራት ላይ የጉዞ ዕቀባ የመጣል ዕቅድ እንዳለው ባለፈው ሰኔ የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን ዘግበው ነበር።
Telegram: https://t.me/Mereja_Plus
YouTube: https://www.youtube.com/
Tiktok: mereja.plus
09/07/2025
ፒኤስጂ ሪያል ማድሪድን 4 ለ 0 በማሸነፍ ለፍፃሜው አለፈ።
__________
በክለቦች ዓለም ዋንጫ ግማሽ ፍጻሜ ፒኤስጂ ሪያል ማድሪድን 4 ለ 0 በማሸነፍ ለፍፃሜው አለፈ።
በሚትላይፍ ስቴዲየም በተደረገው ጨዋታ ፋቢያን ሪዩዝ ለፒኤስጂ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ኡስማን ዴምቤሌ እና ራሞስ አንድ፣ አንድ ግብ አስቆጥረዋል።
ፒኤስጂ የዘንድሮውን የክለቦች ዓለም ዋንጫ ለማንሣት ከቼልሲ ጋር ይፋለማል።
Telegram: https://t.me/Mereja_Plus
YouTube: https://www.youtube.com/
Tiktok: mereja.plus
Click here to claim your Sponsored Listing.
Website
Address
Awassa