Adege abirham

Adege abirham

Share

Photos from Adege abirham's post 15/03/2026

የክብር መታሰቢያ ለወንጌል አርበኛው አባታችን አብርሃም ርቄ
‎ == ===== ==== ===== ==== ==== ====
‎"በጌታ የሚሞቱ ከአሁን ጀምሮ ብፁዓን ናቸው።" (ራእይ 14:13)
‎ በታላቅ ትጋትና በእምነት ጽናት የብዙዎችን ሕይወት ያበሩት አባታችን አቶ አብርሃም ርቄ የድካም ዋጋቸውን ለመቀበል ወደ ጌታቸው እቅፍ ተጠርተዋል።
‎አባታችን በምድራዊ ቆይታቸው፦
‎የጥረትና የትጋት ተምሳሌት፦
‎በትምህርት ማቋረጥና በችግር ሳይበገሩ፣ በጠንካራ የሥራ ባህል ለባለሀብትነት የበቁ የጽናት ሰው ነበሩ።

‎የወንጌል አርበኛ፦ ከ1981 ዓ.ም ጀምሮ "ኢየሱስ ጌታ ነው" በማለት የመሰከሩ፣ ወንጌላዊ ቀጥረው የሚያገለግሉና ለእምነታቸው የታመኑ አባት ነበሩ።
‎የቸርነት አምድ፦ ለድሆች የሚራሩ፣ ያዘኑትን የሚያጽናኑና ለብዙዎች መትረፍ የቻሉ ደግ ሰው ነበሩ።
‎በሀዘናችን ጊዜ ከጎናችን የነበራችሁ ከቅርብም ከርቀት ሆናችሁ ያጽናናችሁን ሁሉ እግዚአብሔር ከክፉ ይጠብቃጥሁ 🙏
‎ከቤተሰቦቻቸው !

13/09/2024

Romans 12 (KJV) - ሮሜ
9: Let love be without dissimulation. Abhor that which is evil; cleave to that which is good.

26/09/2023

Manchi beetti duucha dancha giddo mitte busha kule ba'anno kaaliiqi kayiinni duucha busha giddo mitte dancha lae gatisanno
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯

09/12/2022

መውጫ ፈተና በመጪው ሰኔ ወር በተመሳሳይ ጊዜ ይሰጣል :- ትምህርት ሚኒስቴር

200, 000 ተመራቂ ተማሪዎች ፈተናውን ይወስዳሉ ተብሏል..............................................................................

ህዳር 30/1015ዓም . (ትምህርት ሚኒስቴር) መውጫ ፈተና በሁሉም ዩኒቨርስቲዎች ለሚገኙ ተመራቂ ተማሪዎች በአንድ ጊዜ እንደሚሰጥ የከፍተኛ ትምህርት የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ገልጸዋል ።

መሪ ስራ አስፈጻሚው ኤባ ሚጀና ( ዶ/ር ) በጉዳዩ ዙሪያ በተዘጋጀ አውደጥናት ላይ እንደገለጹት መውጫ ፈተና በመጪው ሰኔ ወር ለሁሉም ቅድመ መደበኛ ተመራቂ ተማሪዎች በአንድ ጊዜ ይሰጣል።

የመጀመሪያው ፈተና በሰኔ ወር ከተሰጠ በኋላ ቀጣዩ የመውጫ ፈተና ከ6 ወራት በኋላ እንደሚሰጥም ዶክተር ኤባ አስረድተዋል።

የከፍተኛ ትምህርት ጥራትና ብቃት ዴስክ ኃላፊ አቶ ሰይድ መሀመድ በበኩላቸው ፈተናውን ለ200, 000 የመንግስትና የግል ዩኒቨርስቲ ተመራቂ ተማሪዎች ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

ፈተናው ለሁሉም ተማሪዎች በኦንላይን እንደሚሰጥ የጠቀሱት አቶ ሰይድ ይህም የፈተና ስርቆትን ለመከላከል የተሻለ አማራጭ በመሆኑ ነው ብለዋል።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱም ሆኑ ተፈታኝ ተማሪዎች ፈተናው በተመሳሳይ ጊዜ በኦንላይን እንደሚሰጥ አውቀው ከወዲሁ ዝግጅት እንዲያደርጉም አቶ ሰይድ አሳስበዋል።

በመውጫ ፈተና ብቃትና የፈተና ኮርሶች ልየታና የተገቢነት ማረጋገጥ ዙሪያ በተዘጋጀው አውደጥናት ከሁሉም ዩኒቨርስቲዎች የተውጣጡ ጉዳዩ የሚመለከታቸው መምህራን ተሳታፊ ሆነዋል።

Want your practice to be the top-listed Clinic in Awassa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address