SNNPR prison adminstration communication
27/09/2023
ለሞላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን በሠላም ለብርሀነ መስቀሉ አደረሳችሁ !!
በሀገራችን ክርስቲያኖች ዘንድ መስቀል የድልና የፈተና ምልክት ነው።
መስቀል በአንድ በኩል እስከ ሞት የሚያደርስ መስዋዕትነትና ፈተናን የሚያንፀባርቅ በሌላ በኩል ማንም ሊያስቀረው የማይችለውን ድል አድራጊነትን የሚያሳየን ነው።
ይህም የክርስቶስ ሰላም እና ፍቅር በሁሉም የሰው ልጆች ልብ ውስጥ ስለ አንድነት በጉልህ ከፍ ብሎ ሊታይ ደግሞ ይገባል ብሎ የማረሚያ ኮሚሽናችን ያምናል።
በክልላችን በጉራጌ ዞን ከወትሮ በተለዬ መንገድ የመስቀል ዳመራ በዓል በአደባባይ በድምቀት ይከበራል።
በኮሚሽናችንም በስሩ በሚገኙ፥ ማረሚያ ተቋማት ጠያቂ ዘመዶቻቻውና በተቋማት ተዘጋጅቶ ይከበራል።
በዚህም በእስር ቆይታቸው ወቅት ቤተሰቦቻቸውን እንዳያስቦና እንዳይጨነቁ ይረዳቸዋል።
በመጨረሻም በዚህ መልዕክት ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በድጋሚ እንኳን ለዚህ ቀን እና ታላቅ በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያልን ሀገራችንን አንድ በሚያደርግ በሰላም እና በአብሮነት ጉዳይ ልዩነት ሳይኖር እንደተሻገርን ዛሬም እንደ መስቀል ደመራ ተደምረን ለክልላችን ሁሉን አቀፍ ልማት በጋራ ሁላችንም ዘብ እንድንቆም ኮሚሽናችን ጥሪ ያቀርባል።
04/09/2023
ነሐሴ 28/2015፦ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በተለያዩ የመንግስት ሥራ ኃላፊነት ቦታዎች በካብኔ ማዕረግ ለሚያገለግሉ የሥራ ኃላፊዎች ሹመት ሠጥቷል።
በዚህም መሠረት፦
1. አቶ ሰማን ሺፋ - በካብኔ ማዕረግ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት ኃላፊ
2. አቶ ንጉሴ አስረስ - በካብኔ ማዕረግ የርዕሰ መስተዳድሩ ልዩ አማካሪ
3. ረዳት ፕሮፌሰር አንተነህ መሉ - በካብኔ ማዕረግ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የፖሊስ ጥናትና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር
4. ዶክተር ፈለቀች ተክለማሪያም - በካብኔ ማዕረግ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የፖሊስ ጥናትና ምርምር ኢንስቲትዩት የዘርፍ ኃላፊ
5. አቶ ሀይረዲን ረዲ - በካብኔ ማዕረግ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የህዝብ ግንኙነትና ማህበረሰብ ንቅናቄ ዘርፍ አማካሪ
6. አቶ ኑሪዬ ሱሌ - በካብኔ ማዕረግ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የመልካም አስተዳደርና የህግ ጉዳዮች ዋና አማካሪ
7. አቶ ሰብስቤ ተካ - በካብኔ ማዕረግ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል የህዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ዘርፍ ኃላፊ፣
8. ወይዘሮ ነኢማ ሙኒር - በካብኔ ማዕረግ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ፣
9. አቶ ተስፋዬ ብላቱ - በካብኔ ማዕረግ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አመራር አካዳሚ ዋና ዳይሬክተር
10. አቶ ፀደቀ ሱጌቦ - በካብኔ ማዕረግ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ፣
11. አቶ ታረቀኝ ኃይለማሪያም - በካብኔ ማዕረግ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የመሠረተ ልማት ዘርፍ አማካሪ
12. አቶ ሙሽተባ አባድር - በካብኔ ማዕረግ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የፍትህ አካላት ስልጠና ማዕከል ኃላፊ
13. ኮምሽነር ሉባባ ጀማል - የማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ኃላፊ
14. ኮሚሽነር ሽመልስ ካሳ - የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር
15. ወ/ሮ ፋዲላ አደም - የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ዋና ኦዲተር
16. አቶ ሬድዋን ከድር - የክልሉ ቡናና ቅመማ ቅመም ባልሥልጣን ሥራ አስኪያጅ
17. ዶክተር አክመል መሀመድ - በካብኔ ማዕረግ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የፖሊስ ጥናትና ምርምር ኢንስቲትዩት ዘርፍ ኃላፊ
18. አቶ ማሞ ቴጋ - በካብኔ ማዕረግ የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኩምሽነር
19. አቶ አብዲልባሲጥ አባኮ - በካብኔ ማዕረግ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ጽህፈት ቤት ኃላፊ ልዩ ረዳት
ማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ለጋራ ተጠቃሚነት!!!!
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the practice
Telephone
Website
Address
Hwassa
Awassa