EECMY Referal Congregation Hawassa

EECMY Referal Congregation Hawassa

Share

22/05/2026

ከ1 ሺሕ በላይ ዜጎች የሚሳተፉበት የጸሎት መርሃግብር ሊካሄድ ነው
የኢትዮጵያ ሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ መጪውን ምርጫ አስመልክቶ ከ1 ሺሕ በላይ ዜጎች የሚሳተፍበት የጸሎት እና የዱአ መርሃግብር እንዳዘጋጀ አስተወቀ።
ይህ መርሃግብር በቀጣይ እሁድ ግንቦት 16 ከቀኑ 9 ሰዓት በአራዳ ፓርክ ከ7 የሃይማኖት ተቋማት የተወጣጡ የሃይማኖት አባቶች ባሉበት እንደሚከናወን ተገልጿል።
በተመሳሳይ ሰዓት በሁሉም ክልሎች የጸሎት ሥነ ሥርዓት እንደሚከናወንም የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሐፊ ቀሲስ ታጋይ ገልጸዋል።
የአደባባይ ጸሎቱ በዋናነት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ በማሰብ የሚካሄድ መሆኑም ገልፀዋል።
የአሁኑ የጸሎት መርሃግብር፤ ጉባኤው በተደጋጋሚ የሚያደርገው የጋራ የጸሎት መሆኑንም ገልፀዋል። በተለይም የኮቪድ 19 ወረርሺኝን በማስታወስ እንዲህ ዓይነት የጋራ ጉዳዮች ሲመጡም ጉባኤው በቀጣይ የፀሎት መርሐግብር እያደረገ እንደሚቀጥል ተነግሯል።

ለኢቫንጄሊካል ዜና አስጨናቂ ሀብታሙ

21/05/2026

‎ ክፍል 2
# ‎የሥላሴ ምንነት
‎የእግዚአብሔር አንድነት
‎የተዋሀደ አንድነት (ዘጸ6:4፣ ኤፌ4:3-6፣ 1ጢሞ2:5)
‎ከሁሉም በላይ መሆኑን የሚያመለክት አንድነት (ዘጸ20:3፣ ዘዳ6:4፣ 1ቆሮ8:4-6፣ ያዕ2:19)
‎የእግዚአብሔር ሶስትነት (አሐዱ ሥሉስነት) ሥላሴ
‎ሥላሴ የሚለው ቃል ሦስትነትን በአንድ ለመግለጽ የምንጠቀምበት የግዕዝ ቃል ነው:: ይህም የእግዚአብሔርን ሦስትነት ሳይሆን አንድነት ለመግለጽ ነው::

‎አዲስ ኪዳን በእግዚአብሔር ዘንድ ሦስት አካል እንዳሉና ስማቸውም አብ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ መሆኑን ይገልጻል:: እያንዳንዱ ፍጹም አካል አለው:: ይህ ማለት ግን እግዚአብሔር በሦስት አይነት መልክ ሳይሆን በባህርይና በመለኮት አንድ የሆኑ ሦስት ፍጹማን አካላት አሉ ማለት ነው:: አካል ማለት በዚህ ትርጉም ፍጹም ሙለአዊና እኔ ባይ ማለት ነው:: ለሥላሴ ትምህርት መሰረቱም፡-

‎የጌታ ኢየሱስ ጥምቀት (ማቴ3:13-17)
‎ለጥምቀት የተሰጠን ሥርአት (ማቴ28:19)
‎የሰው መፈጠርና መውደቅ (ዘፍ1:26,3-:-22)
‎ለበረከት ያላቸው ውህደት(2ቆሮ13-:-13) ናቸው፡፡
‎የሥላሴ ሥራ
‎በመፍጠር

‎አብ - ዘፍ1፡3
‎ወልድ - ዮሐ1:1
‎መንፈስ ቅዱስ - ዘፍ1:2፣ ኢዮ26:12-13
‎በጌታ መወለድ

‎አብ - ዮሐ3:16
‎ወልድ - ሉቃ2:11
‎መንፈስ ቅዱስ - ሉቃ1:35
‎በድነት

‎አብ - ሉቃ15:22
‎ወልድ - ሉቃ15:4
‎መንፈስ ቅዱስ - ኤፌ1:13
‎በሕብረት

‎አብ - ኤፌ2:18
‎ወልድ - 2ቆሮ5:19
‎መንፈስ ቅዱስ - ኤፌ2:18
‎በክብር

‎አብ - 1ቆሮ15:24
‎ወልድ - ፊል3:21
‎መንፈስ ቅዱስ - ራዕ22:17
‎የእግዚአብሔር አብ፣ የእግዚአብሔር ወልድ እና የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ግንኙነት
‎አብ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ የባሕርይ ስሞች ናቸው::

‎አብ የምክር፣ የሀሳብና የፈቃድ ምንጭ የሆነው አካል ነው:: (ኤፌ1:1፣ ሐዋ22:12-14)
‎ወልድ ከአብ የተገኘ አንድያ ልጁና ፈቃዱን፣ ምክሩንና ሀሳቡን ፈጻሚ ሆኖ የሚገለጥ መለኮታዊ አካል ነው:: (ዮሐ1-:-18,ቆላ1:15-22፣ መዝ40:7-10)
‎መንፈስ ቅዱስ ከአብና ከወልድ የሚወጣ የአብና የወልድን ፈቃድ ሞራልና ሐሳብ የሚያስፈጽም መለኮታዊ አካል ነው:: (ዮሐ15:26፣ ኤፌ1:13፣ ዘፍ1:2)
‎አብ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ አንድ አይነት መለኮታዊ ባሕርይ፣ እኩል አምላክነትና እኩል ዘላለማዊነት አላቸው:: በምክር አንድ ናቸው፤ በሕልውናቸው አይቀዳደሙም፤ በባሕርይም አይበላለጡም:: አንዱን ስንጠራ ሁሉን እየጠራን ነው፤ አንዱን ስናመልክም ሁሉን እያመለክን ነው:: አንዱ በሚሰራበት ሁሉም በአንድነት ይሰራሉ፤ አንዱ የሚያውቀውንም ሁሉም ያውቃሉ:: የማይለያይ፣ የማይከፋፈልና የማይጨፈለቅ (የማይዋጥ) አንድነት አላቸው:: አንዱ ከሌላው ሳይቀድም ለዘላለም በአድነትና በሦስትነት ይኖራሉ::

‎የእግዚአብሔር አብ፣ የእግዚአብሔር ወልድ እና የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ልዩነት
‎በአካልና በስራ ይለያያሉ:: አብን አብ የሚያሰኘው የአባትነት ባሕርይ ነው፤ ወልድን ወልድ የሚያሰኘው የልጅነት ባሕርይ ነው፤ መንፈስ ቅዱስን መንፈስ የሚያሰኘው የተልዕኮ ባሕርይ ነው:: አብ ወልድ አይደለም፤ አብ መንፈስ ቅዱስ አይደለም፤ መንፈስ ቅዱስ አብም ወልድም አይደለም::

‎ስለ ሰው ልጆች ድነት (መዳን) ኢየሱስ ክርስቶስን ወደ ዓለም የላከው አብ ነው::
‎ለሰው ልጆች ኃጢአት በመሰቀል የሞተው በግንባር ቀደምነት ወልድ ነው::
‎በበዓለ ሃምሳ ቀን ለአማኞች ኃይልና መጽናናት እንዲሆን የመጣው መንፈስ ቅዱስ ነው::
‎አብ የራሱ አካል አለው፤ ወልድ የራሱ አካል አለው፤ መንፈስ ቅዱስም የራሱ አካል አለው፡፡ ስለዚህ በአካል ሦስት ናቸው::

‎ጥንቃቄ
‎በዚህ ዓለም በአይናችን በምናያቸው ነገሮች የእግዚአብሔርን ባሕርይ ለመግለጽ ብቁ ስለማይሆኑ ምስጢረ ሥላሴን በምሳሌ ለማስረዳት ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል::

‎👉 አዳዲስ ትምህርታዊ, አስተማሪና ቁምነገር ያለውን መንፈሳዊ መረጃዎችን ለማግኘት ይህንን ( Page Like Follow share ) እያደረጋችሁ ተከታተሉን


‎የማህበር ምዕመናን ዲጂታል የወንጌል አገልግሎት ዘርፍ

‎ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ከታች ያለው Page Follow በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ
https://tr.ee/VcHXkRfRGI
‎Facebook
https://www.facebook.com/share/1BX2xBEgrx/
‎YouTube
https://www.youtube.com/
‎Telegram
https://t.me/EECMYR70








Photos from EECMY Referal Congregation Hawassa's post 19/05/2026

በBelarus ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ነው የተባለውና ከ15,000 በላይ ሰዎችን ያሳተፈ የወንጌል ምሽት ተካሄደ
በChizhovka-Arena በተካሄደው ታላቅ የወንጌል ስብሰባ 15,500 የሚሆኑ ሰዎች ተሰብስበው “የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነው፣ የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የዘላለም ሕይወት ነው” (ሮሜ 6፡23) የሚለውን የምሥራች መስማታቸውም ተገልጿል።
በዝግጅቱም አንድ ሰው ባለፈው ማክሰኞ ሕይወቱን ለማጥፋት አስቦ እንደነበር ነገር ግን እግዚአብሔር እንዳስመለጠው ምስክርነት መስጠቱም ተነግሯል። በዚህም በወንጌል ምሽቱ ስነ ሰርዓት መምጣቱን ተከትሎም የሰማው ወንጌል እየሱስ ክርስቶን አምኖ እንዲቀበል እንዳደረገውም ተገልጿል ።
በተጨማሪም በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችም ከኃጢአታቸው ተመልሰው ሕይወታቸውን ለጌታ አሳልፈው ሰጥተዋል። ይህ በBelarus ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ እና ታሪካዊ የወንጌል ስብሰባ መሆኑ ተገልጿል።
በዚህ ሥራ ውስጥ ለብዙ ዓመታት በጸሎት የተባበሩ አብያተ ክርስቲያናትና ፓስተሮች ምስጋናም የቀረበ ሲሆን ባለፈው ሳምንት በሀገሪቱ ያሉ ክርስቲያኖች 24 ሰዓት ያልተቋረጠ ጸሎት ሲያደርጉ እንደቆዩ ተጠቅሷል።
እንዲሁም ከ43 የተለያዩ ከተሞች የተውጣጡ 1,300 አባላት ያሉት መዘምራን፣ ኦርኬስትራዎች፣ ሙዚቀኞችና ሶሎቲስቶች በፕሮግራሙ ላይ በልዩ ሁኔታ ተሳትፈዋል። መረጃዉን GMM TV አገኘነዉ።
ለኢቫንጄሊካል ዜና አስጨናቂ ሀብታሙ፡፡

Want your place of worship to be the top-listed Place Of Worship in Awassa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address


Referal Mekanyesus
Awassa
REFERALMEKANYESUS