MesfinPage

MesfinPage

Share

30/12/2025

#የአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ የተሳሳተ ውሳኔ .....

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት ተማሪ የሆነችው ወጣት፣ በማህበራዊ ሚዲያ (ቲክቶክ) ባጋራችው ቪዲዮ ምክንያት ለአንድ ዓመት ከትምህርቷ እንድትታገድ መወሰኑ ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኗል።

ተማሪዋ በቪዲዮዋ ላይ "መምህራን ለ3ዐ ደቂቃ ያህል ካስተማሩ በኋላ የተማሪዎች የመስማትና የመረዳት አቅም ስለሚቀንስ የምታስተምሩን አይገባንም" የሚል ይዘት ያለው መልዕክት ማስተላለፏ ይታወሳል።

ይሁን እንጂ የዩኒቨርሲቲው ዲሲፕሊን ኮሚቴ ይህ ድርጊት መምህራንን የሚያንቋሽሽና የዩኒቨርሲቲውን ክብር የሚነካ ነው በሚል ተማሪዋ ለአንድ ዓመት ከትምህርት ገበታዋ እንድትታገድ ወስኗል።

ይህን ጥያቄ ለዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ላቅርብ
1ኛ) ተማሪዋ ያጋራችው ሐሳብ በሳይንስ እና በምርምር የተረጋገጠ አይደለምን????? ወይስ አታውቁትም
2ኛ) የተማሪዋ ሐሳብ የመምህራንን ክብር ዝቅ ያደረገው የቱ ጋር ነው ? እውነቱ ስለተነገረ????
3ኛ) ትምህርት አይጠቅምም ብሎ የሚያወራ ባለስልጣን (ትምህርት ሚኒስትር) ባለበት ሐገር ???? የእርሷ ጥፋት የቱ ጋር ነው?????

ስለሆነም ተማሪዋ ላይ የተወሰነው ኢፍታዊ ውሳኔ ከእንደገና በሰከነ መንፈስ ታይቶ ተማሪዋን የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ወደ ትምህርት ገበታዋ ይመልሳት ዘንድ በአንክሮ እጠይቃለሁ።
ፍትህ በግፍ ከትምህርት ገበታዋ ለታገደችው እህታችን::

21/12/2025
07/12/2025

ሰዎች ራሳቸውን እንዲወዱ ካደረክ፣ አንተንም ይወዱሃል።

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Awassa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Website

Address


Awassa