Ethio Press

Ethio Press

Share

Photos from Ethio Press's post 09/05/2022

ምዕራባውያን ለሩሲያ ስጋት ሆነው ቀጥለዋል " - ፕሬዜዳንት ቭላድሚር ፑቲን

እኤአ ሜይ 9 ሩሲያውያን በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማብቂያ ላይ ሶቪዬት ሕብረት በናዚ ጀርመን ላይ የተቀዳጀችውን ድል አስበው ይውላሉ።

ይህ የድል በዓል ቭላድሚር ፑቲን ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ትልቅ ትርጉም ተሰጥቶት ነው የሚከበረው።

በዕለቱ ሩሲያ ያላትን ዘመን አፈራሽ ጦር መሳሪያ ለዓለም የምታሳይበት ቀን አድርገውታል።

ከዩክሬን ጋር ጦርነት ላይ ያሉት የሩስያው መሪ የዛሬውን የድል ቀን ምክንያት በማድረግ ከዩክሬን ጋር እየተደረገ ያለውን ጦርነቱ የተመለከተ አዲስ ውሳኔ ያስተላልፋሉ ተብሎ ተጠብቆ ነበር።

ፑቲን በዛሬው በዓል ላይ ጦርነቱ ማብቃቱን አልያም በዩክሬን ላይ አዲስ የተጠናከረ ወታደራዊ እርምጃ ይወሰዳል ብለው ይናገራሉ ተብሎ ሲጠበቅ ነበር።

ነገር ግን " ምዕራባውያን ለሩሲያ ስጋት ሆነው ቀጥለዋል " ከማለት ውጪ ፑቲን ያሉት ነገር የለም።

ፑቲን በዩክሬን እየተፋለሙ ላሉት ወታደሮቻቸው "እየተዋጋችሁ ያላችሁት ለሩስያ ደኅንነት ነው” በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል።

Photos from Ethio Press's post 06/05/2022

ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ኅብረት ዓመታዊ የፖለቲካ ምክክር አካሄዱ

ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ኅብረት ዓመታዊ የፖለቲካ ውይይታቸውን ዛሬ በአዲስ አበባ አካሄደዋል።

ውይይቱ የተካሄደው በአውሮፓ ኅብረት እና በአፍሪካ፣ በካሪቢያን እና በፓሲፊክ ሀገራት መካከል በተደረሰው የኮቶኑ አጋርነት ስምምነት አንቀጽ 8 መሠረት መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የኢትዮጵያን የልዑካን ቡድን በመወከል እንዲሁም በኢትዮጵያ የአውሮፓ ኅብረትን በመወከል አምባሳደር ሮላንድ ኮቢያ የምክክር መድረኩን መርተዋል።

ሁለቱ ወገኖች በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን ግጭት እና የአውሮፓ ኅብረት እና የኢትዮጵያ ግንኙነትን በሚመለከት የተወሰዱ የሰብአዊ እና የተጠያቂነት እርምጃዎችን ጨምሮ የተለያዩ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ከግምት ውስጥ በማስገባት የጋራ ተጠቃሚነትን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

አቶ ደመቀ በመክፈቻ ንግግራቸው የኢትዮጵያ መንግሥት በሰሜን ያለውን ግጭት ለማስቆም እና የሀገሪቱን ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ እያከናወናቸው ያሉ የተለያዩ እርምጃዎችን ዳሰሳ አቅርበዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የሰብአዊ ድጋፍ ተደራሽነትን ማስፋት፣ በቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሉሴጎን ኦባሳንጆ የአፍሪካ ኅብረት ማዕቀፍ ስር የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ በመሆን የሰላም ተነሳሽነትን መደገፉን እና ሁሉንም ያሳተፈ ሀገራዊ ውይይትን ጠቅሰዋል።

የፍትሕ ሚኒስትሩ ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ በሰሜኑ ግጭት ወቅት በሁሉም አካላት የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እና ጾታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶችን ጨምሮ መንግሥት የወሰደውን የተጠያቂነት እርምጃ በተመለከተ አብራርተዋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች ግብረ-ኃይል በማዋቀር የጥሰት ተግባራትን፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የጋራ ምርመራ እና ምክረ-ሐሳቦቹን ተግባራዊ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት እንዲሁም ወንጀለኞችን ወደ ሕግ እንዲቀርቡ እየተሠራ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ፣ ለትግራይ ክልል ያልተቋረጠ ሰብአዊ ድጋፍን ለማረጋገጥ እስካሁን የተወሰዱ እርምጃዎችን በቪዛ አሰጣጥ፣ ዕርዳታ ሰጭዎች ወደ ትግራይ ይዘውት የሚገቡት መጠን፣ ኬላዎችን በመቀነስ እና ሰብአዊነት ድጋፎች መጨመርን በመጥቀስ አብራርተዋል።

አቶ ምትኩ በኢትዮጵያ በድርቅ እና በግጭት ለተጎዱ ወገኖች ለሚደረገው ድጋፍ የሰብአዊ አጋሮች ምስጋናቸውን አቅርበው፣ የአማራ እና አፋርን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የድጋፍ መሠረቱን ማስፋት እና ለዘላቂ ልማት እና መልሶ ማቋቋም ሥራዎች ተገቢውን ትኩረት መስጠት እንደሚገባ አሳስበዋል። .

በምክክር መድረኩ ንግግር ያደረጉት በኢትዮጵያ የአውሮፓ ኅብረት አምባሳደር ሮላንድ ኮቢያ ለሁለቱም ወገኖች አሁን ካጋጠሟቸው ፈታኝ ሁኔታዎች አንፃር ወቅታዊ መሆኑን ገልጸው በኢትዮጵያ ስላለው ግጭት እና ድርቅ እንዲሁም በአውሮፓ የሩስያ እና የዩክሬን ግጭት አንስተዋል።

ኢትዮጵያ የሩሲያ እና ዩክሬንን ግጭት በተመለከተ ሁለቱ ሀገራት ችግራቸውን በሰላማዊ መንገድ፣ በድርድር እንዲፈቱ የያዘችውን አቋም በምክክር መድረኩ ላይ በድጋሚ አሳውቃለች።

ውይይቱ ከሰብአዊ መብት ጥሰት እና ከተጠያቂነት እርምጃዎች በተጨማሪ በኢትዮጵያ ስላለው የንግድ ሁኔታ ከአውሮፓ ባለሃብቶች አንፃር የሚፈጠሩ ችግሮችን ለመፍታት እና የዳበረ ኢኮኖሚ ለመገንባት ስለሚያስችለው ጉዳይ ተወያይተዋል።

የአውሮፓ ኅብረ

26/04/2022

የአሜሪካ ኤምባሲ ፤ የ Diversity Visa (ዲቪ) ን ጨምሮ ሁሉንም የስደተኛ እና ስደተኛ ያልሆኑ የቪዛ ሂደቶች እያስቀጠለ መሆኑን ገልጿል።

ኤምባሲው አገልግሎቱን እየተጠባበቁ ያሉ ሁሉ ፤ በዓለም አቀፉ ወረርሽኝ ኮቪድ-19 እና በኢትዮጵያ ታውጆ በነበረው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወደኃላ የቀሩ ስራዎችን ለመስራት በሚደረገው ሂደት በትዕግስት እንዲጠብቁ መልዕክቱ አስተላልፏል።

የቪዛ ቃለመጠይቆች ሂደት ሚከናወነው በስቴት ዲፓርትመንት ቅድሚያ በሚሰጣቸው ጉዳዮች ላይ በመመስረት መሆኑን የገለፀው ኤምባሲው ፤ አሜሪካውያንና ኢትዮጵያውያን ሰራተኞች በሁሉም የቪዛ መደቦች ላይ በተቻለ መጠን ብዙ ቃለ መጠይቆችን ለማድረግ በማቀድ በትጋት ስራቸውን እያከናወኑ ነው ብሏል።

በዚህም ሂደት ላይ ፤ የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች ሁሉንም አስፈላጊ ሰነዶች ይዘው ለቃለ መጠይቅ ዝግጁ ሆኖ በመምጣት የሁሉንም ሰው የጥበቃ ጊዜ እንዲቀንስ ለማድረግ ማገዝ ይችላሉ ሲል መልዕክቱን አስተላልፏል።

Want your business to be the top-listed Media Company in Awassa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address


Piasa
Awassa