Loma Bossa Woreda Communications
06/07/2026
በመሬት አያያዝ አስተዳደር የአየር ንብረት ማስተካከያ ፕሮግራም (CALM PforR) ውጤታማ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ሥራዎች መከናወናቸው ተገለጸ።
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል፣ የግብርና ቢሮ በመሬት አያያዝ አስተዳደር የአየር ንብረት ማስተካከያ ፕሮግራም (CALM PforR) የተከናወኑ ተግባራት የአርሶአደሮች የመስክ ጉብኝትና የልምምድ ለውጥ በዳውሮ ዞን ተካሂዷል።
በዞኑ ሎማ ቦሳ ወረዳ፣ ዚማ ዋሩማ ቀበሌ በማሻ ደንምባ ንዑስ ተፋሰስ በፕሮግራሙ ድጋፍ የተከናወኑ ውጤታማ የአፈርና ውሃ ጥበቃ እንዲሁም የኑሮ ማሻሻያ ሥራዎችን ከዳውሮ እና ከኮንታ ዞኖች የተወጣጡ አርሶአደሮች የመስክ ጉብኝት አድርገዋል።
በፕሮግራሙ በማሻ ደምባ ንዑስ ተፋሰስ የተከናወኑ የአፈርና የውህ ጥበቃ እና ሌሎች ዘላቂ የተፈጥሮ ሀብት አስተዳደር ሥራዎች ለሎች ተሞክሮ የሚሆን መኾኑን ነው በመርሐግብሩ መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪና የፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ባህሩ በላቸው የገለጹት።
የዞኑ ግብሮና አከባቢ ጥበቃ ኅብረት ሥራ መምሪያ ምክትልና ተፈጥሮ ሀብት አከባቢ ጥበቃ ዘርፍ ኃላፍ አቶ ምትኩ ለይኩን በበኩላቸው፤ በቀጣይም በለማው ንዑስ ተፋሰስ ሌሎች የኑሮ ማሻሻያ ተግባራትን አጠናከረው ማስቀጠል እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
ለተገኘው ውጤት የአርሶአደሮች ጠንካራ ተሳትፎ እንዲሁም የማኅበረሰብ ቁርጠኝነት ትልቁ ድርሻ እንደሚይዝ የገለጹት በክልሉ ግብርና ቢሮ የካልም ፕሮግራም ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ካይሮ ከበደ የተገኘውን መልካም ተሞክሮ በማስፋት ተጠቃሚነት ማሳደግ ይገባል ብለዋል።
በንዑስ ተፋሰሱ የተከናወኑ ውጤታማ ተግባራት ማስፋፋት እና የተጀመሩ ሥራዎችን በባለቤትነት በመጠበቅ የተፈጥሮ ሀብት በመጠበቅ ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ የሁሉም ኃላፊነት መኾኑንም አቶ ካይሮ ጨምሮ ገልጸዋል።
የማህበሩ አባላት በበኩላቸው ከ150 ሄክታር መሬት ላይ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራዎች መከናወናቸውን በመግለፅ በኑሮ ማሻሻያ ሥራዎችም ውጤታማ እንደኾኑ ተናግረዋል።
በቀጣይ የአከባቢው መሠረታዊ ችግሮች የኾነውን የኤሌክትሪክ ወፍጮ በማቋቋም የኅብረተሰቡን ችግር ለመፍታት ማህበሩ ዕቅድ አስቀምጦ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
የመስክ ጉብኝቱ በማህበር አደረጃጀት ውጤታማነት፣ በፕሮግራሙ ድጋፍ የተከናወነው ውጤታማ ተግባራት እንዲሁም ከአባላት የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት አኳያ ያሉ መልካም ተሞክሮዎችን ለማስፋት መኾኑን ተጠቁሟል።
በመስክ ምልከታው በፕሮግራሙ ከታቀፉ የኮንታ እና የዳውሮ ዞን የተወጣጡ አርሶአደሮች እንዲሁም ሌሎች የባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይከታተሉን 👇
Follows us via👇
page https://www.facebook.com/profile.php?id=100064822177806
Telegram channel https://t.me/lomabosaworedgovtcomnctnaffairs/email [email protected]//
https://www.youtube.com/
http://twitter.com/
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the organization
Telephone
Website
Address
Awassa