Hawassa Polytechnic College

Hawassa Polytechnic College

Share

Photos from Hawassa Polytechnic College's post 21/04/2026

የሚመረቱ ቴክኖሎጂዎች የአከባቢን ፍላጎት መነሻ በማድረግ ለገበያዉ የማቅረብ ሥራ ላይ ትኩረት ሰጥተዉ እየሰሩ እንደሚገኙ የሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን ገለጹ።

ኮሌጁ የሰራዉን የፕላስቲክ ሪሳይክልና ፕሮሰስ ቴክኖሎጂን በሀዋሳ ከተማ ተደራጅቶ እየሰራ ለሚገኝ ዉበት ሀዋሳ ኢንተርፕራይዝ በ1.2 ሚሊየን ብር ግዢ በመፈጸም ርክክብ አድርጓል ።

የሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ መልካሙ በራሳ በኮሌጃቸዉ የሚመረቱ ቴክኖሎጂዎች የአከባቢን ፍላጎት መነሻ በማድረግ ችግር ፈቺ አዋጪ ቴክኖሎጂ በመስራት ለአብዢ ኢንተርፕራይዞች የማሸጋገርና በተቋም በማምረት ለገበያዉ የማቅረብ ሥራ ላይ ትኩረት ሰጥተዉ እየሰሩ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

በኮሌጃቸዉ ተሰርቶ በዛሬዉ ዕለት ለርክክብ የበቃዉ ቴክኖሎጂ የፕላስቲክ ሪሳይክል ፕሮሰስ ቴክኖሎጂ መሆንና የፕላስቲክ ዉጤቶችን የሚፈጭ ፣ የሚያጥብና የሚያደርቅ ቴክኖሎጂ መሆኑን የተናገሩት የኮሌጁ ዲን የሀዋሳ ከተማ ለተጀመረዉን ስማርት ሲቲ ትልቅ አስተዋፅኦ የሚያበረክት መሆኑን ተናግረዋል።

በኮሌጁ የተመረተዉ ይህ ቴክኖሎጂ ከዉጪ የሚገቡ የቴክኖሎጂ ዉጤቶች ሊተካ የሚችል ቴክኖሎጂ መሆኑን የተናገሩት የኮሌጁ ዲን ለአከባቢ ጥበቃ አበርክቶ ሚናዉ ከፍተኛ መሆንን ተናግረዋል።

የሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ምክትል ዲንና የቴክኖሎጂ ሽግግርና ኢ/ኤ ዋና አስተባባሪ ወ/ሮ ከበብሽ ተሰማ ይህ የተመረተዉ ቴክኖሎጂን እሴት ሰንሰለት ትንተናን መነሻ በማድረግ የተሰራ ቴክኖሎጂ በማንፋክቸሪንግ ዲፖርትመነት የአከባቢን ብክለት ችግር መነሻ ተደርጎ የተሰራ መሆኑንና ቴክኖሎጂውን ሰርቶ ለማጠናቀቅ የሁለት ዓመት ጊዜ መዉሰዱን ተናግረዋል።

ቴክኖሎጂው ሲሰራ አካል ጉዳተኞችን እና ሴቶችን ታሳቢ ተደርጎ መሆኑን እንዲሁም የሚሰሩ ማንኛዉም ስራዎች ከእጅ ንኪኪ ነጻ መሆኑን ከምክትል ዲኗ ገለጻ ለመረዳት ችለናል።

የዉበት ሀዋሳ ኢንተርፕራይዝ ማናጀር አቶ አልታየ የቦ በቀላሉ ሊበሰብስ የማይችል ሀይላንድዶችን የመፍጨት የማጠብ ስራዎችን የሚሰራ ቴክኖሎጂ በመሆኑ ይህንን ቴክኖሎጂ በአግባብ በመጠቀም የማህበራቸዉን የዉስጥ ገቢያቸዉን ለማሳደግ ትልቅ አበርክቶ እንዳለዉ ተናግረዋል።

11/04/2026

****** የኮሌጃችን ማህበረስብ በሙሉ*********
‎ እንኳን ለጌታችንና ለመዲኃንታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን! በዓሉን ስናከብር አቅም ያጡና አዛውንቶችን በማስታወስ፤ ጌታችን የእኛ በደል ይቅር ለማለት በመስቀል እርቃኑን ተሰቅሎ ፍቅርንና ይቅርታን እንዳስተማረን እኛም እርስ በእርሳችን ይቅር በመባባል በፍቅሩ ተዋደን አንድ ሆነን ማክበር ይኖርብናል።
‎በዓሉ የሰላም፣ የደስታ፣ የጤና እንዲሆንልን እምኛለው።
*****ሀዋሳ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ********

Photos from Hawassa Polytechnic College's post 25/10/2025

/Mastercard Foundation መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት የተማሪውን የትምህርትና አስፈላጊ ወዎችን ሙሉ በመሸፈን Scholarship_ዕድል ይዞላችሁ መተዋል ።

FAWE መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ከሀዋሳ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ጋር በመተባበር 2017 ዓ.ም ከሲዳማ ክልል ከሁሉም ወረዳዎች የተመለመሉ በርካታ ተማሪዎችን የ Scholarship ዕድል በመስጠት ለተማሪዎች
✅ የቤት ክራይ
✅ የተሟላ የቤት መገልገያ ቁሳቁስ
✅የትምርት ቤት ክፍያ
✅ ለቀለብ የሚሆን ወጪ
✅ የትራንስፖርት ወጪ
✅ የህክምና ወጪ
✅ የተማሪውን ወላጅ ይደገፋል
✅ የትምርት ቁሳቁስ እና ሌሎች ወጪዎችን ሸፍኖ ወይም አሟልቶ እያሠለጠነ የቆየ ሲሆን

ዘንድሮም በ2018 ሥልጠና ዘመን (Phase II) ለ2ኛ ዙር ሠልጣኞችን በተመሣሣይ መልኩ ለመቀበል ዝግጅቱን አጠናቀዋል ፣ በመሆኑም የዕድሉ ተጠቃሚ የሚሆኑ ሠልጣኞች ማሟላት ያለባቸው ዝቅተኛ መስፈርት
1ኛ. በ2016 እና 2017 የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በመውሰድ በቴክኒክና ሙያ ሙያ ለደረጃ 3, 4እና 5 የሚያስገባ ውጤት ያላቸው
2ኛ. በክህሎት ዘርፍ ማለትም በሙያ ነክ ስልጠና ዘርፍ የመሠልጠን ፍላጎት ያላቸው።
3ኛ. "STEM" ትምርት በጣም ጎበዚ ሆኖ ግን በኢኮኖሚ ችግር በTVET ገብቶ መሰልጠን የማይችል/ትችል
4ኛ. የአካል ጉዳት ያለባቸውም በዚህ ፕሮጀክት እንድሳተፉ የሚበረታቱ ሲሆን አካል ጉዳተኛ የሆን የአንድ ዓመት ጭማር ተደርጎ በ2015 የ12ኛ ክፍል ፈተና የወሰዱ የዛን ዓመት የደረጃ 3,4እና5 ያላቸው የዕድሉ ተጠቃሚ ይሆናሉ።
5ኛ. የዕድሉ ተጠቃሚ 80% ሴቶች ሲሆኑ 20% ወንዶች ይሆናሉ ።

በመሆኑም ፕሮጀክቱ ዜጎችን ብዙ መንገድ ተጠቃሚ የሚያደርግ ለክልላችን ታላቅ ዕድል ይዞ የመጣ በመሆኑ ተማሪዎች ከፊታችን 17-21 አርብ ድረስ ብቻ የሚሆን ሲሆን በሀዋሳ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር -2 ቀርባችሁ እንድትመዘገቡ ስንል በትህትና እናሳውቃለን ።

:-
1. በ2017 እና በ2016 ያጠናቀቃችሁ የ12 ክፍል ውጤት
2. የ10ኛ እና የ11ኛ ክፍል Transcript
3. የ 8 ክፍል ካርድ
4. አንድ 3*4 የሆነ ጉርድ ፎቶ ግራፍ
5. ለውድድሩ ይጠቅመኛል የሚትሉትን አስፈላጊ ማስረጃዎችና ሰነዶችን ኮፕ በመያዝ በአካል ቀርባችሁ መመዝገብ ትችላላችሁ ።

ሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
ጥቅምት 16/2018 ዓ.ም

Want your university to be the top-listed University in Awassa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Address


Hawassa
Awassa