ReNathan Technology Solutions PLC

ReNathan Technology Solutions PLC

Share

22/03/2024
02/05/2018

ለቫይረስ አሪፍ መላ

በቫይረስ የተጠቃ ወይም 'corrupt' የሆነን ፍላሽ ዲስክ እንዴት ያለአንቲ ቫይረስ እንደምናጸዳውና ስንገዛው እንደነበረው አዲስ እንደምናደርገው እናያለን። አሁኑኑ ሼር አድርጉት

እባክዎ ከመጀመርዎ በፊት ፍላሹ ላይ ጠቃሚ ፍይል ካለዎት ወደ ሌላ ቦታ ኮፒ ያድርጉ።

በመጀመሪያ ኮምፒዩተራችን ላይ 'command prompt' ወይም 'cmd' እንከፍታለን። ( 'cmd'ን ለመክፈት በመፈለጊያችን ላይ cmd ብለን search እናደርጋለን. Cmd ሲመጣልን right click አድርገን run as administrator የሚለውን በመጫን cmdን እንከፍታለን)

Cmd ከከፈትን በኋላ የሚከተሉትን ትእዛዞች በቅደም ተከተል እናስገባለን። እያንዳንዱን ትእዛዝ ከጻፍን በኋላ ENTER ቁልፍን እንጫናለን

1. DISKPART
2. LIST DISK (አሁን በኮምፒውተሩ ላይ ያሉትን ዲስኮች ይዘረዝርልናል. ለማጽዳት የፈለግነውን ፍላሽ ቁጥር ከለየን በኋላ ወደ ሶስተኛው ትእዛዝ እንሄዳለን። ምሳሌ.disk 1)

3. SELECT DISK * (በኮከቡ ፋንታ ሁለተኛው ትእዛዝ ላይ የለየነውን የፍላሽ ቁጥር እናስገባለን)
4. CLEAN (በዚህ ጊዜ ፍላሹ ላይ ያለውን ማንኛውም ነገር ያጠፋዋል)
5. CREATE PARTITION PRIMARY (ለፍላሹ ይዘት ይፈጥራል)
6. SELECT PARTITION 1
7. ACTIVE (ይህ ፍላሹን ዝግጁ ያደርገዋል)
8. FORMAT FS=FAT32 (ይህ ፋላሹን በጥልቀት በመሰረዝ በውስጡ ያሉትን ማንኛውም ቫይረስ ወይም ሌላ ችግር ያጠፋል። ሂደቱ የተወሰነ ጊዜ ስለሚወስድ እስከሚጨርስ በትዕግስት እንጠብቀዋለን)

9. ASSIGN (አዲስ ለፈጠርነው ፍላሽ የፊደል ስም ይሰጥልናል)
10. EXIT (ፕሮሰሱን ይጨርስልናል)

አሁን አዲሱን ፋላሻችንን መንቀልም ሆነ መጠቀም እንችላለን። ይህንን መንገድ በመጠቀም ማንኛውንም ችግር ያለበት ፍላሽ ማስተካከል እንችላለን።

አሁኑኑ ሼር አድርጉት

source - information technology xchg

23/12/2015

We offer PC maintenance, ID card, Business card, Logo design and Photo editing services to our esteemed customers

Want your business to be the top-listed Business in Asosa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address


Asosa