Sadiq Mohammed
13/04/2026
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት በአክሱም የተፈፀመውን ጥቃት አወገዘ፡፡ የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ባወጣው መግለጫ ‹‹በታሪካዊቷ አክሱም ከተማ ውስጥ በሙስሊሞች ላይ የተፈፀመውን ኢሰብአዊ ጥቃት አጥብቀን እናወግዛለን›› በማለት የጀመረ ሲሆን አርብ እለት ሚያዝያ 2 ቀን 2018 የተፈጠረው አሳዛኝ ክስተት ለዘመናት ከቆየው የህዝቡ የመከባበርና አብሮ የመኖር ባህል ጋር የሚቃረን መሆኑን አስረድቷል፡፡
የችግሩ መነሻ ድንገተኛ ሳይሆን በማህበራዊ ሚዲያና በሌሎችም መድረኮች ላይ የተሰራጨው የጥላቻ ንግግር ውጤት መሆኑን የጠቀሰው መግለጫው ‹‹ለዘመናት የቆየውን የአዛን ወይንም ድምፅ ማጉያ አጠቃቀም በሀይል ለማስቆም የተወሰደው እርምጃ ህገ መንግስታዊውን የሀይማኖት ነፃነት የሚጥስ ነው›› ብሏል፡፡ መግለጫው በማስከተልም አርብ እለት በጁመአ ስግደት ላይ በነበሩ ሙስሊሞች ላይ የተፈፀመው ጥቃት ምንም አይነት ህጋዊ ምክንያት እንደሌለው ገልፆ በእለቱ በመስጅድ ውስጥ በሀይል በመግባት ቅዱስ ቁርአንን መቅደድና መሬት ላይ መበተንን ጨምሮ በመስጅድ ውስጥ የሚገኙ እቃዎችን እስከመስበር ድረስ የተፈፀሙትን ድርጊቶች ዘርዝሯል፡፡
እንዲሁም በሰላማዊ ምእመናን ላይ አካላዊ ጉዳት ጭምር እንደደረሰባቸው ገልፆ በዘፈቀደ ለተፈፀመው እስርም ተቃውሞውን አሰምቷል፡፡ ምክር ቤቱ ህዝበ ሙስሊሙ እነዚህን ችግሮች በትእግስት በመቋቋምና ተቃውሞን በሰላማዊ ተክቢራ ብቻ በመግለፅ ላሳየው ጨዋነት ምስጋናውን አቅርቧል፡፡ መግለጫው ጨምሮም መንግስት ይህንን ጥላቻ ያነሳሱና የመሩ፣ በጥቃቱ ላይ የተሳተፉ የፀጥታ ሀይሎችና ሲቪሎችን ተከታትሎ በመያዝ ለፍርድ እንዲያቀርብም ጥሪውን አቅርቧል፡፡
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Telephone
Website
Address
Ciro
Asebe Teferi
304050
Opening Hours
| 09:24 - 05:00 |