Mltmase

Mltmase

Share

15/09/2022
22/06/2022

የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ያላቸውን አጋርነት በተግባር እያሳዩ ነው
**************

ክልሉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያን ይደግፉ ወንድማማችነትን ያጠናክሩ በሚል መሪ ቃል የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር እያካሄደ ይገኛል።

በገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብሩ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንንን ጨምሮ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች እና ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች ተገኝተዋል።

በህዳር 14/2014 ዓ.ም የፌዴሬሽኑ 11ኛ ክልል ሆኖ የተመሰረተው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በአጭር ወራት ውስጥ በርካታ የህብረተሰቡን ጥያቄዎች መፍታት መቻሉን የተናገሩት የክልሉ ም/ር/መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በክልሉ አንጻራዊ ሰላም መፍጠር መቻሉንም አንስተዋል።

ክልሉ የአጋሮች ድጋፍን በፈለገበት በዚህ ወቅት ክልሎች ላሳዩት ቀና ምላሽም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ለክልሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 50 ሚሊዮን፣ የአማራ ክልል 50 ሚሊዮን፣ ደቡብ ክልል 30 ሚሊዮን፣ ሲዳማ 20 ሚሊዮን፣ ሶማሌ 20 ሚሊዮን፣ ቤንሻንጉል 10 ሚሊዮን፣ አፋር 10 ሚሊዮን፣ ጋምቤላ 5 ሚሊዮን፣ ሐረሪ 5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብተዋል።

ሚድሮክ ኢትዮጵያም ለክልሉ 50 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብቷል።

የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ደግሞ 60 ሚሊዮን ብር የሚገመት የቴክኖሎጂ ድጋፍ ለክልሉ እንደሚያደርግ ቃል ገብቷል።

በተጨማሪም የተለያዩ የግል ተቋማት እና የግል ድርጅቶችም ለክልሉ ድጋፍ እያደርጉ ነው።

እስካሁን ባለው መረጃ ለክልሉ ከ697 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ቃል ተገብቷል።

በአሸናፊ እንዳለ

የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/c/EBCworld/
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/EBCNEWSNOW
የተመረጡ አጫጭር የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የቲክቶክ አካውንታችንን ይከተሉ
https://www.tiktok.com/

Want your business to be the top-listed Beauty Salon in Alaba K'ulito?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Website

Address


Adiss Ababa _Alaba Kulito
Alaba K'ulito
123