AfricVid.com
17/03/2022
አሜሪካንና ቡችሎቿን የNATO አገራት ማን ይቅጣቸው? ለነሱስ ማእቀብ ይኖር ይሆን? የስታንፎርድ ዩኒቨርስቲ ያደረገው አስደንጋጭ ጥናት መሰረት ፤ ግማሹ የአሜሪካ ህዝብ የዘር ማጥፋትንም ሆነ የጦር ወንጀልን በአገሪቱ ወታደሮች እስከተፈፀመ ድረስ ፈቃደኛ ናቸው።
* በ1999 አመት ጅማሬ ምክኒያት የሚፈበርከው NATO ታላቋን አገር ዩጎዝላቪያን ለ78 ቀናት 28,000 ሚሳኤልና ቦንብ አዘነበባት። ተቋማት ፈረሱ ታላቅ የነበረችው ዩጎዝላቪያም በብሄር ተከፋፍላ ወደ 9 ብጥስጣሽ አገራት ተለወጠች። በወቅቱ ዢኑዋ እንደዘገበው 2500 ንፁሃን ሲገደሉ 79ኙ ህፃናት ነበሩ። ኔቶ ግን አንድም ሰው አልሞተበትም ነበር።
* ብዙ የተወራለትና አሜሪካና ኔቶ በሽንፈት ለቀው የወጡበት የአፍጋኒስታን ወረራ እስከ 71,000 የንፁሃንን ሂወት እንደቀጠፈ ተዘግቧል።
* በ Abu ghraib የኢራቁ ማሰቃያ ማጎሪያ ምን ይደረግ ነበር? በቃላት ሊገለፅ በማይችል መልኩ የአሜሪካ ወታደሮች እስረኞችን እስከሞት ያሰቃዩ ነበር። በሙስሊሙ ማህበረሰብ ፀያፍ የሆኑ ድርጊቶችን በመፈፀም ስነልቦናቸውላይ ይጫወቱ ነበር። (ከታች ፎቶዎችን ይመልከቱ)
* በ2019 በዩ.ኤስ አየር ሃይል Abu Kamal ሶሪያ ጥቃት ደርሶ ነበር። በአከባቢው የሽብርተኛ እንቅስቃሴ እንዳለ ያመነው ኳታር የሚገኘው የአሜሪካ ጦር ኮማንድ ሴንተር በቦታው ንፁሃን ሰዎች እንደነበሩ ቢያውቅም ጥቃቱን አዘዘ። 2 ግዙፍ ቦንቦች ከአየር ተጣሉ ከ80 ሰዎች በላይ ሲሞቱ 16ቱ ብቻ ታጣቂዎች ነበሩ የቀሩት ህፃናት እናሴቶች ነበሩ።
- [ ] ይህን ለምሳሌ ይሆን ዘንድ አነሳሁ እንጂ አሜሪካ ከሁለተኛው አለምጦርነት በኋላ ከ80 በላይ አገራት በጦር መምዝ አልያም በመበጥበጥ ተሳትፋለች። የሚገርመው እነዚህ በሰው ፍጡር ላይ የሚደረጉ ወንጀሎችን የሚፈፅሙት አብዛኛው Secret Americans Death Squad አባላት ሲሆኑ በወንጀልም አይጠየቁም ነበር።
- [ ] በዩክሬን እየተደረገ ያለውንጦርነት በቀጥታ በመቀስቀስ NATO ተጠያቂ ነው። የUSSR መፍረስን እንዲሁም የምዕራብ እና ምስራቅ ጀርመንን መቀላቀል ተከትሎ ኔቶ ወደ ምስራቅ ወደ ሩሲያ ድንበር እንደማይስፋፋ በእንግሊዝ ፣ አሜሪካ ፣ ፈረንሳይ ፣ ጀርመንና ሩሲያ የተደረገውን ስምምነት NATO 14 ጊዜ የጣሰ ሲሆን። በቅርብ በማንአለብኝነት ዩክሬንን ለመቀላቀል ከ2008ጀምሮ እንቅስቃሴ አደረገ። ይሄም የኔቶ ኒውክለር ሚሳኤሎች ሩሲያ ድንበር ላይ ለማጥመድ የተደረገ ጥረት በመሆኑ ሩሲያ ራስን መከላከል ነው በሚል ወረራውን አድርጋለች። አይዞሽ ከጎንሽ ነን ሲሉ የነበሩ የኔቶ አባላትም ዩክሬንን ካዷት። ተንታኞች እንደሚሉት ቀድሞውንም በጅ አዙር ጦርነት ሩሲያን ለመጉዳትና ከአለም ለማግለል የተጠቀሙበት ነው። ዩክሬንም ብትፈርስ ግድ አይሰጣቸውም ይላሉ።
- [ ] ታዲያ የሩሲያና የዩክሬን ጦርነት አፍሪካን ይጎዳ ይሆን? ስንዴ፣ ማዳበሪያ፣ ዘይት . . . በሌላ ፅሁፍእንገናኝ! ሰላም!
22/06/2020
ለኤርትራ መገንጠል ከኤርትራውያን የበለጠ ሲለፉ የነበሩት ፦
፨ ግብፃዊው የ UN ሴክሬታሪ ጄነራል ቡትሮስ ቡትሮስ ጋሊ
፨ ሱዳን ፥ ግብፅ እራሷ እና
፨ በትህነግ የሚመራው ኢህአዴግ ነበሩ
ያኔ የትኛውምንም ኢትዮጵያዊ ትስማማለህ ወይስ ምን ይሻላል ብሎ ያማከረው አልነበረም ። ተማክረው የወሰኑትም ቢሆኑ በህዝብ ድምፅ ይሁንታን ያገኙ አልነበሩም ።
ጠቢባን እና ዘመኑ ያፈራቸው ታላቅ የፖለቲካ መሪዎች ተብለው ፎቷቸው በየጎዳናው ፥ በየቁልፍ መያዣው ፥ በየቤቱ እና በየግድግዳው የተለጠፈላቸው፤ ህይወታቸው ሲያልፍ የደጀ ሰላም ግድግዳዎች በምስላቸው ያሸበረቀላቸው ፥ ድንኳን በየቀበሌው ተጥሎ የተለቀሰላቸው እናም ሞተው እንኳ "ራእያቸው" ሲመራን የነበሩት እነዛ መሪዎቻችን ስለ አሰብ ሲጠየቁ ,,," ግመል ያጠጡበት" ነበር ያሉን።
እርግጥ ነው ዛሬ የኤርትራ የባህር በሮች እና በነዚ አገራት ፥ ተቋማትና ግለሰቦች በግፍ ተነጥቀን ለኤርትራ የተሰጠብን አሰብ ከግመል ማጠጫነት የተሻለ ጥቅም አይሰጥም። እኛ ግን ደማችንን ለጅቡቲ እያጠጣን /እየለገስን እንገኛለን። ይባስ ብሎ በአለም ካሉት የባህር ሃይል ጥንካሬ ካላቸው ምርጥ አስር አገራት አንዷ ከሆነችው ከግብፅ ጋር የጦርነት እሰጥ አገባ ውስጥ ነን። ስለ ጅቡቲ ካነሳን አይቀር የባህር በሯን ለቻይና ፥ ጃፓን ፥ አሜሪካ ፥ ፈረንሳይ እና ለመሳሰሉት ሃያላን አገራት የጦር መንደሮችን (military base ) እያከራየች ትገኛለች። ሱማሊያ ለኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላት ለሆነችው ቱርክ ፤ ሱማሊላንድም ወዳጅ ይሁኑ ጠላት በቅጡ ለማናውቃቸው ነገር ግን ሁሌም የግብፅ አንጀት ለሆኑት ኤምሬትስ እና ሳኡዲ አረቢያ አጎብዳጅ ሆናለች። ሱዳንም ኢትዮጵያ በታሪክ ካሏት ታሪካዊ ጠላቶች ሁሉ አቋሟ ማይታወቅ እና አቅፎ አሳልፎ እንደሚሰጥ አይነት ወዳጅ ነች።
በአለም ላይ ከመቶ ሚሊዮን በላይ ህዝብ ይዛ እና ለዘመናት ከጠላት ጋር ስትታገል የኖረች የባህር በር የሌላት አገር ኢትዮጵያ ብቻ ናት። የኛን ገማሽ ህዝብ ይዞ እንኳ የባህር በር የሌለው ሌላ አገር የለም።
ስለዚህም ስለባህር በር የምንነጋገርበት ከዚህ የተሻለ ግዜ የለም ። ምንም ጥያቄው እንዳይነሳ በፖለቲካው መንደር ባይፈልግም ፤ ምንም መፍትሄ አልባ አድርገው ብዙዎች ቢተውትም ነገር ግን የማንሸሸው ugly truth ነው።
ይህን ፅሁፍ ስጀምር ዋናው ጉዳዬ አባይ ነበር። ግብፅ ያንን ሁሉ ሴራ ስትሰራብን ጎረቤቶቼ ብላ አላዘነችልንም። ወደብ አልባ እንድንሆን ጥራም ተሳክቶላታል። እኛ ግን ሃላፊነት የሚሰማን ህዝቦች ነን። ማንም ኢትዮጵያዊ ፤ ጨፍጫፊ መሪ እንኳን ዙፋን ላይ ቢቀመጥ አባይን ጨርሶ የማቆም ህልም እንኳ ኖሮት አያውቅም ወደፊትም አይኖርም ። ይሁንና አባይን ለማልማት ለመጠቀም የማንንም ይሁንታ እና ፊርማ ማግኘት አይጠበቅብንም ። እንደውም ግደቡ ማለቁ ላይቀር ፖለቲከኞቻችን የከፋፈሉንን ግብፅ አንድነታችንን እንድናጠናክር ውለታ እየዋለችልን ነው።
, ቸር እንሰንብት!
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Ethiopian
Addis Ababa